መተከል ጎጃም ነው – አማራ ግን ይንገላታበታል፤ ይፈናቀልበታል!

Print Friendly, PDF & Email
(አቻምየለህ ታምሩ)

ወያኔ ከጎጃም ወስዶ በፈጠረው «ቤንሻንጉል ጉሙዝ» ክልል ውስጥ መተከል ዞን ሰፊው ዞን ነው። በዚህ የወያኔ ክልል ውስጥ ዛሬም ድረስ አብዛኛው ባላገር አማራ ነው። መተከል አውራጃ [ዛሬ ዞን ተብሏል] ጎጃም ውስጥ ከነበሩ አውራጃዎች አንዱ ነበር። ጎጃም እንደመሆኑ መጠን በአብዛኛው አማራ የሚኖርበት ምድር ነው። በተጨማሪም አገው፣ ሽናሻ፣ ጉምዝና ኦሮሞም ይኖርበታል።

ወያኔ የጎጃሙን መተከል አውራጃ ለሁለት ክልሎች ሰነጠቀው። አንዱን ስንጣቂ «አዊ ዞን» የሚባል ፈጠረና ወደ «አማራ ክልል» ሲካተተው የተቀረውን ስንጣቂ ደግሞ «መተከል ዞን» ብሎ «ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል» ብሎ በፈጠረው ክልል ውስጥ አካተተው። ሆኖም ግን አዊም ሆነ መተከል ዞን ውስጥ ዛሬም ድረስ በብዛት የሚኖረው አማራና አገው ነው።

ከቅርብ ጊዜ ወዲስ ከመተከል ዞን ውስጥ አማራዎች በስፋት «ወደ አገራችሁ ሂዱ» እየተባሉ እየተፈናቀሉ ይገኛሉ። አሁንም ልብ በሉ — ጎጃምን ከፍለው ቤኒሻንጉል ክልል አደረጉት እንጂ መተከል ጎጃም ነው። ከዚያም አማራዎችን «ወደ አገራችሁ ሂዱ» ብለው አፈናቀሏቸው። አማራው በአገሩ አገር እንደሌለው ጎጃም መተከል ውስጥ ከተፈጠረው ሁኔታ በላይ ሊያሳየው የሚችል ነገር ያለ አይመስለኝም።

መተከል ዞን ውስጥ ሰባት ወረዳዎች አሉ። ድባጤ፣ ቡለን፣ ወንበራ፣ ማንዱራ፣ ግልገል በለስ፣ ፓዌ፣ ማንቡክና ማንኩሽ ይባላሉ። መተከል ከጥንትም ጎጃም ነው፤ አሁንም አብዛኛው አማራ ነው። በተለይ ግልገል በለስ፣ ፓዌ፣ ማንቡክና ማንኩሽ ከሌላው ጎጃም በሁለም ነገር ተመሳሳይ ነው። ክልል መፈጠር ካለበት ለምን ሌላ ክልል እንደሆነ ቢያስረዷችሁም የሚገባችሁ አይመስለኝም።

ሁለት ምክንያት ግን አሉ። አንደኛው አማራው አማራን ለማዳከም ሆን ተብሎ የጎነጎነ ሴራ ሲሆን ሁለኛው ደግሞ ቦታው ለም ስለሆነ መሬቱ ለትግራይ ባለሀብቶች ተፈልጎ ነው። ለዚህም ሲባል በተለያየ ጊዜ ምክንያት እየተፈለገ አማራ እንዲንገላታ፣ እንዲታሰር፣ እንዲገደል እና እንዲባረር ይደረጋል።

ከሰሞኑ ቤንሻንጉል ክልል ከሚባለው የወያኔ ፍጡር ሰበብ ተፈልጎ አማራ እየተንገላታ፣ ስቃይ እየደረሰበት፣ ሰቆቃ እየተፈጸመበትና «ወደ አገርህ ሂድ» እየተባለ ነው። አላማው አንድና አንድ ነው። ባለፈው ሰሞን «ጋንቤላ ክልል» መሬት ተወደደብን ያሉ የትግራይ ባለሀብቶች የተንጣለለ መሬት በነጻ የሚታደሉበት አካባቢ ያስፈልጋቸዋል። ለዚህ ደግሞ አማራ ያለ ገደብ የሚፈናቀልበት ለሙ ቤንሻንጉል ክልል አለላቸው። አገሪቷ የእነሱ ስለሆነች ባላገሮቹን አማሮች አፈናቅሎ ያሻቸውን መሬት የሚሰጥ አገዛዝ አላቸው። ዛሬ ቤንሻንጉል ውስጥ አማሮች እየተንገላቱ «አገራችሁ ሂዱ» እየተባሉ ያሉት የጋምቤላ ክልል መሬት ተወደድብን ላሉ የትግራይ ባለሃብቶች ሰፋፊ መሬቶችን ለመስጠት ሲባል ነው።

የጋምቤላ መሬት ተወደድብን ያሉ የትግራይ ባለሀብቶች ትራክተሮቻቸውን ወደ መተከል እያጓዙ ነው። የሚፈልጉት ያህል መሬት አማራው ተነቅሎ እስኪመቻችላቸው ድረስ ትራክተሮቻቸው ቻግኒ ካምፕ በሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት እንዲጠበቁ ታዝዟል። ካለፈው ሳምንት ወዲህ መተከል በሙሉ ትራክተር ይዘው በገቡ የትግራይ ባለሀብቶች ተወሯል። ዛሬ መቀሌና መተከልን መለየት አይቻልም። ከትንሽ እስከ ትልቅ ምግብ ቤቶች የሚወራው ትግርኛ ነው። ሰሞኑን ደግሞ ጋምቤላ ሲዝቁ የከረሙት የትግራይ ጄኔራሎችና ዘመዶቻቸው ጠቅልለው ትራክተሮቻቸውን ይዘው መተከል ዘምተዋል። መተከል ካፍ እስከ ደገፉ ትራክተር ይዘው በገቡ የትግራይ ጀኔራሎች ጢም ብላለች። አማራውን የሚፈናቀልበትን ያን ለም የጎጃም መሬት ለማረስ ተዘጋጅተዋል።

ክልሉን እንዲያስተዳደር የተሰየመው ምስለኔው አሻድሊ ሀሰን «አማራዎችን ከአገራችሁ አስወጡ» ተብሎ ትዕዛዝ ተላልፎለታል። ማፈናቀሉ በአንድ ዙር እንዳይካሄድ በጥብቅ ታዝዟል። እቅዳቸው አማራን ተራ በተራ በማፈናቀል ያን ለም መሬት ለትግራይ ባለሃብቶች ለመስጠት ነው። ትናንትም ሆነ ዛሬ እየሆነ ያለው ይህ ነው። ዛሬም ተጨማሪ የትግራይ ባለሀብቶች ከአውሮፓና ከአሜሪካ እየተጠሩ ከልማት ባንክ ያሻቸውን ገንዘብ በመዛቅ ትራክተር ከኤፌርት ገዝተው መተከል እየገቡ እንዲያለሙ እየተለመኑ ነው።

ጎጃም-መተከል አማራው ተፈናቅሎ የትግራይ ባለሀብቶች ሰፋፊ እርሻ የሚሰጥበት ምድር!

እንዲህ ዳምኖ ዳምኖ የዘነበ እንደሆን
እንዴት ያሉ በሮች ይጠመዱ ይሆን?
እንዲህ ጭሶ ጭሶ የነደደ እንደሆን፣
የአመዱ መጣያ ስፍራዉ ወዴት ይሆን?
ንገሯት ጎጆዬን አቃጥላታለሁ፣
ሲያጨሱ እየጬሰች ያለኝ እመስላለሁ፤
ለምስለኔው ሙክት ለጭቃው ወጠጤ፣
እንዲህ ሁኜ ነው ወይ ባገር መቀመጤ፤
ያንተ ልጅ ሲበላ የኔ ልጅ አልቅሶ፣
ያንተ ቤት ሲታደስ የኔ ጎጆ ፈርሶ፣
ለኔም መሄጃዬ ላንተም መጥፊያህ ደርሶ።