አስቸኳይ ጥሪ ለአማራ ተወላጆች በሙሉ!!

Print Friendly, PDF & Email

(ይህ ከዚህ በታች የምታነቡት የመረጃ ጽሁፍ በአንድ ለህዝብ ተቆርቋሪ በሆነ ወገናችን የተጻፈ፣ ጠቃሚ መረጃዎች የያዘንና ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በተለይም ደግሞ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲያነቡት እና እንዲሰራጭ በመቀጠልም አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ለማሳሰብ የተዘጋጀ ጠቃሚ ጽሁፍ ነው።)

መረጃ መለዋወጥ የሰለጠነብን ልማድ አይደለም። እባክዎን ይህን መረጃ ቢያንስ ለሚያውቋቸው አምስት ሰዎች ያስተላልፉ ወይም ያሰረጩ!!!

ወያኔ በአማራ ላይ ያለው ጥላቻው ፍርሃት ላይ የተመረኮዘ ነው። አማራው በኢኮኖሚና በድርጅት ተጠናክሮ መገኘት የልበትም የሚል ጠንካራ አቋም አለው። ለዚህም የአማራውን ግዛት በመበጣጠስ የተረፈውን ደግሞ በአገውና በኦሮሞ ዞኖች በመክፈል በውስጡ የርስበርስ ግጭት እንዲያናጋው በማድረግ አማራውን ማድከም ወሳኝ መሆኑን አምኖበታል። ከመጀመሪያው ስልጣን ሲይዝ አማራውን መሳሪያ አስፈትቷል። በበሌሎቹ የዘር ክልሎች አማራውን አስመትቷል። እስካሁን ድረስ ካገራችን ውጣ ወደ መጣህበት ተመለስ በመባል መግቢያ መውጫ አጥቶ ደሙን ባፈሰሰላት አጥንቱን በከሰከሰላት ኢትዮጵያ ነፃነቱን ተገፎ ስደተኛና 2ኛ ዜጋ እንዲሆን ተገዷል። ወያኔ/ኢህአዴግ በአማራው ላይ ካደርሳቸው በደሎች በጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፤-

፩ኛ –
የዕደገትና ልማት ተቋሞች ዝርጋት ከሌሎች ክልሎች ባነሰ እንዲካሄድበት ማደረግ ዋነኛ አቋሙ ነው።

፪ኛ –  ጎንደርን ለማጥፋት

– ታች አርማጭሆን፣ ሳንጃን፣ የመተማንና ቋራ ለም የሆኑና ነዳጅ ዘይት ያለባቸው መሬቶችን ለሱዳን አስረክቧል። አቀናባሪዎቹ   ስዮም መስፈን፣ ዶ/ር ተቀዳ አለሙ፣ ፍስሀ ይመር፣ አዲሱ ለገሰ፣ ደመቀ መኮንንና በርከት ስሞን ሲሆኑ የታዘዙትም በመለስ ዜናዊ ነው።

–  ሁመራን፣ ወልቃይትንና ጠገዴን ለም መሬቶች ከመቀላቀሉ በተጨማሪ ትግራይ ከነዚህ የአማራ መሬቶች ከፍተኛ የወርቅ ማዕድን ባለቤት ሆናለች። የራስዳሽን ተራራና አብደራፊን ለመውሰድ ጣሊያን ከሰራው በደል በከፋ በአማራው ላይ ካስቀመጣቸው የብአዴን ጉዳይ አስፈጻሚዎቹና ወኪሎቹ ጋር ሕጋዊነት ባለው ሁኔታ የተሰጠው እንደሆነ የሚያመለክት ሰነድ ለመፈራረም ሽርጉድ ማለት ጀምሯል። አማራው ሳያውቅ ደመቀ መኮነን ጉዳዩ በምስጢር እንዲያዝ ትዛዝ ሰጥቷል። ይኼው ግልሰብ በት/ት ሚኒስትርነት ስልጣኑ ተጠቅሞ በ፮ኛ ክፍል መማሪያ መጽሃፍ ራስ ዳሽን ትግራይ ውስጥ እንዳለ ተደረጎ እንዲዘጋጅም አድርጓል። “በቡሀ ላይ ቆርቆር” በሆነ ወንጀል አማራው ባደባባይ ሲዘረፍ ካብራኩ የተገኛችሁ ምሁራን እስከ መቸ ደርስ በምን አለብኝነት ርቃችሁ መኖር ትችላላችሁ።

– በጣና በልስ በሚለማው የስኳር ፋብሪካ ግንባታ በአለፋ ወራዳ ቢሆንም ንብረትነቱ የኤፈርት በመሆኑ ከጎንደር ከመቶ ሺህ በላይ ሄክታር ተቆርጦ አዲስና ጃዊ ወራዳ በሚል በ፪ሺ፪ በማቋቋም ወደፊት ከአማራው አውጥቶ እንደ አገር ሊፈጥረው በሚያሰጋጀው አዊ ዞን ውስጥ አካቶታል። በዚህ ሽፍጥ ከጎንደር ሀያ ሰባት ቀበሌዎች ተወስደዋል። አቀናባሪዎቹ ወያኔው አባይ፣ ወልዱና የብአዴኑ ወኪላቸው ደመቀ መኮንን መሆናቸው ታውቋል። ለመሆኑ ቆጋ በሚባለው የመስኖ ልማት ከ፯ሺ ሄክታር ፭ሺው በኤፈርት ለትግራይ ሀብት ማፍሪያ ተይዞ በመታረስ ላይ እንደሆነ ስንታችሁ ታውቃላችሁ።

፫ኛ –

አላማጣን ከወሎ ገንጥሎ ትግራይ ጓዳ ውስጥ ያስገባው በጥጥ ምርት ወዘተ. አማራውን ለም መሬት ለማሳጣት ነው። ወደፊትም ካሳ  ተ/ብርሀን በተባለው ወያኔ የብ አዴን ካድሬ ዋግን ጠቅሎ ለትግራይ ለመስጠት “የአፄ ካሌብ ልጆችና  የአሸንዳ/ ሻዴይ” ባህል ከአማራው ሳይሆን ከትግሬዎች ጋር ያቀራርበናል የሚል አቋም ይዞ መንቀሳቀስ ጀምሯል።

፬ኛ

በተከዜ፣ በከሰም፣ በጃሞ አማራው እንዳይጠቀም በውሀና ግብርና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶቹ በኩል ለሀይልና መስኖ ወንዞቹ በትግራይ፣ በኦሮሞና በአፋር ተገድበው ባለንብረቱ አማራ መና ቀርቷል።

፭ኛ –

አባይም ቢሆን ግድቦቹ የሚገነቡት በቤንሻንጉልና በነቀምት አካባቢ ኦሮሞ ውስጥ ነው። ወደፊት አገሪቱን መገንጠል የሚሻው ወያኔ አማራው በአባይ እንዳይጠቀም በቅጥረኞቹ ምህረት ደበበና አለማየሁ ተገኑ የኦህዴድ ቀንደኛ ፀረ አማራ ወኪሎቹ ያስነደፈው ዕቅድ ነው። ሰዎቹ ኦሮሞ ውስጥ ቤካ አቦ የሚባለው ሁለገብ ፕሮጀክት ጥናት ተጠናቆ በወያኔ ተጨማሪ ግድብ ስለሚሰራ አይዞህ ባይ አልባ አማራው “አፍንጫህን ላስ” መባሉ አንጀታቸውን እንዳራሰው በኦህዴድ ስብሰባ ላይም መናገራቸው የቆሙት አማራውን በስልጣናቸው ተጠቅመው ለማውደም እንደሆነ ተረጋግጧል። በአሽከርነት የሚታወቁት ጥቂት አማራ ነን ባዮችም በዝምታ ወይም በተባባሪነት አብረው ተፈርጀዋል። በመሰራት ላይ ያሉት የሬብኛ መገጭ ግድቦችም ከሚያለሙት ግመሹ ከአስር ሽህ ሄክታር በላይ ለኤፈርት መመደቡን፣ ከጢስ አባይ የሚገኘው ሰማንያ በመቶው …….    (ቀሪውን ከዚህ ላይ ያንብቡ pdf)