ዳግማዊ የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት እና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ አንድ ላይ ለመስራት ተጣመሩ

Print Friendly, PDF & Email

aapo2nd-and-admf-merger(ምስጋነው አንዱአለም )

ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች የግድ መስማት ያለባቸው አንድ ድምጽ አለ፡፡ የህዝብ ጥያቄ፡፡ የአማራ ህዝብ የወቅቱ ዋና ጥያቄ ለማናቸውም ነገር ጠበቃ የሚሆን የአማራ ድርጅት ፍጠሩልኝ ነው፤ ለዛም በቅድሚያ በስሜ የምትንቀሳቀሱ አካላት አንድ ላይ መሆናችሁን ንገሩኝ ነው፡፡ ይሄንን የህዝብ ድምጽ ዋጋ የሰጡት ዳግማዊ የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት እና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ አንድ ላይ ለመስራት በዛሬው እለት ተጣምረዋል፡፡ ለበርካታ ቀናት ሲካሄድ የቆየው ይሄ ድርድር በስምምነት ሲቋጭ ሌሎች በአማራ ስም የሚንቀሳቀሱ አካላትም እንዲቀላቀሉት እና የወገናቸውን የአማራን ጥሪ እንዲመልሱ አጽንኦት በመስጠት ነው፡፡ መርሃችሁ ቅድሚያ አማራ የሆነው የሁለቱ ድርጅቶች አመራሮች እንደገናም የጥምረቱን ሂደት የሰመረ ለማድረግ ፍቅር፣ ትህትናና ቅንነት በተመላበት ሁኔታ የሰራችሁት የሁለቱ ድርጅቶች ተወካዮች ላቅ ያለ ምስጋና ይገባችኋል፡፡ ዝርዝር መግለጫው በቀጣዮቹ ቀናት ይቀርባል፡፡

ድል ለአማራ ሕዝብ!
አማራ ያሸንፋል!

(የግርጌ ማስታወሻ፡-

ይሄ ስኬት ለእኔ ደግሞ እንደ አንድ አማራ ልዩ ስሜት እንደሚሰጥ ከወራት በፊት የተፈጠረውነን ክስተት የምታስታውሱ ታውቁታላችሁ፡፡ ዛሬ እንደገና ልቤ ስለ አማራ ሕዝብ ሀሴትን አደረገች፡፡ እወዳችኋለሁ ወገኖቸ፡፡ እናሸንፋለን፡፡ ወያኔ በሌለበት ሰማይና ምድርም እንኖራለን፡፡)