ግልድ ደብዳቤ ለትምህርት ሚኒስቴር አዲስ አበባ – ከዳግማዊ የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (ዳግማዊ መዐሕድ)

Print Friendly, PDF & Email

aapo2

ግልድ ደብዳቤ ለትምህርት ሚኒስቴር አዲስ አበባ – ከዳግማዊ የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (ዳግማዊ መዐሕድ)

ጉዳዩ፡ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ውጤት ይመለከታል

በሁለት ሺህ ስምንት ዓመተ ምሕረት የሀገር አቀፍ ፈተና ከወሰዱ የ10ኛ ክፍል የዐማራ ተማሪዎች መካክል ለከፍተኛ ትምህርት ማዘጋጃ (Preparatory) ትምህርት የሚያስገባ ውጤት ያስመዘገቡት 32 ከመቶ (32%) ብቻ ሲሆኑ ይህ ቁጥር ከሁልም አካባቢዎች ሲነጻፀር እጅግ አነስተኛ መሆኑን መግለፃችሁ ይታወቃል። ለነገሩ “አብዮታዊ ዲሞክራሲ” በሚለው ፀረ ዐማራ ስሌት የወጣቱን የአዕምሮ ዕድገት ለመቅጨት የምትወስዱት እርምጃ መሆኑን እናንተም አትስቱትም።

ለዚህ ነው ተማሪዎች ግልጽነት የጎደለው አሠራር መሆኑን ለሚመለከተው ክፍል በተደጋጋሚ ቢያሳውቁም ምንም አይነት የምርመራም ሆነ የማስተካከያ እርምጃ ያልተወሰደው። አድራጎቱ በዐማራው ላይ የሚፈጸም በደል ብቻ ሳይሆን ወንጀል ጭምር ነው። በትምህርት ተቋም ውስጥ ለትምህርት በቀረቡ ወጣቶች ላይ የዚህ ዓይነቱ በደል ሲፈጸም የህሊና መጉደል ብቻ ሳይሆን የሚያስጠይቅ ወንጀል ነው። በደሉን ተማሪዎቹም አልሳቱትም። ሆን ተብሎ የዐማራውን ሕዝብ ለመበደልና እንደተለመደው ለማግለል የተፈፀመ ሴራ ነው የሚል መርጃ እያደርሱን ይገኛሉ። ለመላው ዐማራ ሕዝብ ማንነት፣ ጥቅም፣ ታሪክና ልዕልና መከበር የሚታገለው ዳግማዊ መዐሕድ ይህን በደል ይኮንናል፣ እንዲሁም ያወግዛል። ላለፉት 41 ዓመታት የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር ዐማራውን በሁሉም መንገድ ለማጥፋት ከያዘው እኩይ ተግባር መካከል አንዱ አድርጎ ይመለከተዋል።

ስለሆነም ትምህርት ሚንስቴር በአስቸኳይ የተማሪዎችን ውጤት በድጋሜ በግልጽ መርምሮ ችግሩን እንዲቀርፍ አጥብቀን እንጠይቃለን። በተጨማሪም ይህን የትምህርት አቋም የሕሊና ሚዛን እንዲኖረው ስለሚጠበቅ የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር በዐማራው ወጣት ላይ ያቀደውን የጥፋት ዘመቻ ማስፈጸሚያ እግረኛ ወታደርነቱን እንዲያቆም በአንክሮ እንጠይቃለን። ችግሩን መቅረፍ ካልተቻለ ግን በዐማራው ላይ የሚፈጸሙት ስልታዊ ጥቃቶች እያየሉ ቢመጡም የጀመርነው የህልውና ትግል እየተጠናከረ እንጅ እየተዳከመ አንዳማይሄድ እናረጋግጣለን።

በተያያዘም ተማሪዎች፣ ወላጆችና ጉዳዩ ያገባናል የሚሉ ሌሎች ወገኖችም ጭምር ሕጋዊ መብታቸውን ተጠቅመው ያዋጣል በሚሉት መንገድ ሁሉ እንዲጠይቁና ውጤት በድጋሜ እንዲመረመርላቸው ድምፃቸውን እንዲያሰሙ እናበረታታለን፣ እንዲሁም እንገፋለን። ዳግማዊ መዐሕድ ችግሩ እስኪፈታና ዐማራውን ከትምህርት ተቋም ለማፅዳት የሚደረገውን መረባረብ እስኪቆም ድረስ ከጎናቸው እንደማይለ በአፅኦት ይገልጻል።

ድል ለአማራ ሕዝብ!

የዳግማዊ መዐሕድ ሊቀ መንበር

ቸርነት ተፈሪ

aapo2nd-pr-p1 aapo2nd-pr-p2