አዲስ መጽሃፍ “ምጽአተ ዐማራ፤ ተገድሎና ተገዳድሎ የማያልቅ፣ ተነቅሎ የማይደርቅ” – በሞረሽ ወገኔ የተዘጋጅ

Print Friendly, PDF & Email

ማስታዎቂያ

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት፣ በዘረኛው የትግሬ ወያኔ አገዛዝ፣ በዐማራው ነገድ ላይ፣ የፈጸመውን የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ዓለም አቀፋዊ ወንጀል፣ በተጨባጭ መረጃዎች ለማጋለጥና ወንጀሉን የፈጸሙት ቡድኖችና ግለሰቦች፣ በየትኛውም ዘመንና ጊዜ፣ በሚኖሩበት በየትኛውም አገር ለፍትሕ እንዲቀርቡ ለማድረግ የሚያስችል መረጃ አሰባስቧል። ይህንና ዐማራው በኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ተጠብቆ መዝለቅ የከፈለውን ውድ ዋጋ የቱን ያህል እንደሆነ፣በአንፃሩ፣ ካለፉት 50 እና 60 ዓመታት ወዲህ፣ ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ዐማራ የሆኑ ቡድኖችና ግለሰቦች ዐማራውን እየቀቡት ያለውን ጥላሸትና እያደረሱበት ያለውን የማንነት ነጠቃ፣ ግድያ፣ እሥራት፣ ሥቃይና መሳደድ ምን ያህል የሠፋና የጠለቀ እንደሆን በተጨባጭ የሚያሳይ “ምጽአተ ዐማራ፤ ተገድሎና ተገዳድሎ የማያልቅ፣ ተነቅሎ የማይደርቅ” በተሰኘ ርዕስ ያሳተመው መጽሐፍ ከጥቅምት ፲፪፣ ፪ሺ፱ [October 22/ 2016] ጀምሮ በገበያ ላይ ይውላል።

ይህን መጽሐፍ እያንዳንዱ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን እወዳለሁ የሚል፤ ከሁሉም በላይ ዐማራ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ሰው ሊኖሩት ከሚገቡት የዕውቀት ምንጮች እንደ አንዱ ሊቆጥረው የሚገባ ነው። ስለሆነም በየአገሩ የሚገኙ የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት አባላትን በማነጋገር መጽሐፉን ማግኘት ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ መጽሐፉን በሚከተሉት አድራሻዎች መጠየቅ ይቻላላል።

1. ሥልክ ቁጥር፦ (202) 677-0094
2. ኢሜይል፦ gaintarbgebia@gmail.com

new-book-by-moresh-wogenie-sept-2016