የትግል አንድነት ጥሪ በአማራ ስም ለምትንቀሳቀሱ ድርጅቶች!

Print Friendly, PDF & Email

aapo2

ጉዳዩ᎓– የትግል አንድነት ጥሪ በአማራ ስም ለምትንቀሳቀሱ ድርጅቶች!

የዐማራ ሕዝብ ከባድ የህልውና አደጋ ተደቅኖበት መቆየቱ እና ይሄም አደጋ ከቀን ቀን እየከፋ መጥቶ ግልጽ የሆነ ጦርነት የተከፈተበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሕዝባችን በትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግንባር (ትህነግ፡ ህወሓት) የወረራ አገዛዝ ቀንበር ስር ከወደቀ ወዲህ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ዘራቸው እንዲጠፋ ተደርጓል፣ ንብረታቸው ወድሟል፣ ለዘመናት ከኖሩበት ቀየ ተፈናቅለዋል፣ በትምህርታቸው ላቂያነት ካገኙት የስራ ገበታ ተፈናቅለዋል፣ ያካበቱትን ዕውቀት ተጠቅመው ራሳቸውን፡ ወገናቸውንና አገራቸውን እንዳይጠቅሙ ከቅጥር ሲታገዱ ቆይተዋል፤ ሕዝቡም እንደ ሕዝብ ሲሰደብ፣ ሲዘበትበት እና ታሪኩ ሲንቋሸሽበት እንዲሁም ቅርሶቹ በጠራራ ፀሀይ በስርቆት ሲዘረፉበት እና በእሳት ሲወድሙበት ቆይተዋል፡፡ ህወሓት ራሱ በፊታውራሪነት በሚመራው የወረራ አገዛዝ ሌሎች ብሄረሰቦችን በከፍተኛ ጥላቻ እየመረዘ በዐማራ ላይ እንዲነሳሱ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በልዩ ልዩ ስፍራዎችም ከላይ የተዘረዘረውን መከራ በግልጽ በሕዝባችን ላይ እንዲደርሱ አድርጓል፡፡ ህወሓት ገና “ሀ” ብሎ ለትግል በተከዜ ደደቢት ከመሸገበት ጊዜ ጀምሮ በግልጽ አማራን ማጥፋት አለብኝ ብሎ በትግል ሠነዱ ጽፎ፡ ያንንም እቅዱን በትግል ላይ እያለ እና በኋላም አገሪቱ እጁ ላይ ከወደቀችለት ወዲህ ፀረ ዐማራ ፖሊሲውን በቻለው አቅም ሁሉ ሲፈጽም ቆይቷል፡፡ ዐማራውን ከምድረ ገፅ ለማጥፋትም መሬቶቹን ለራሱ በጉልበት ከልሏል፣ ለጎረቤት ክልሎች አድሏል፣ እንደሱዳን ላሉ የጎረቤት አገራት ሽጧል፡፡ ዐማራውን አጥፍቶ የትግራይን መንግስት ለመመስረት የተነሳው ይህ ኃይል በአሁኑ ጊዜ የጥንት ዕቅዱን ለመፈጸም በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ በከባድ ድህነት፣ ሰቆቃ እና የህልውና ስጋት ውስጥ ወድቆ የቆየው የዐማራ ሕዝብ በመጨረሻም የሚደረግበት በደል ሁሉ ከአቅሙ በላይ ሲሆንበት በይፋ ተቃውሞውን ለመግለጽ አደባባይ ወጥቷል፡፡ ይህንን ተከትሎም ይሄ ወራሪ ኃይል አለ የተባለውን ኃይሉን አሰልፎ ግልጽ ጦርነት በሕዝቡ ላይ ከከፈተ ወራት ተቆጠሩ፡፡ ሽህዎች ተገድለዋል፣ በማጎሪያና ማሰቃያ ካምፖች ታጉረዋል፣ ቆስለዋል፣ ንብረታቸው ወድሟል፣ ቤተሰባቸው ፈርሷል፡፡ አሁንም ይህ ወራሪ አገዛዝ በግፍ ላይ ግፍን እየጨመረ በመሆኑ፣ የሕዝባችን ሰቆቃና ዋይታ ከዕለት ወደ ዕለት እየከፋ ህልውናው አደገኛ ሁኔታ ላይ ወድቆ ይገኛል፡፡

ስለሆነም የዐማራ ሕዝብ ልጆች የሆንን ሁሉ ለወገናችን ለመድረስ ከዚህ የከፋ ጊዜ ስለሌለ በቻልነው አቅም ሁሉ እንድንረባረብ እና አንድ ወጥ ታግሎ አታጋይ የፖለቲካ ድርጅት እንዲፈጠር እና አስቸኳይ አለማቀፍና አገራቀፍ ትግል አድርጎ ወገናችንን ከጥፋት እንድንታደግ ዳግማዊ የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት በተለያየ አጋጣሚና ጊዜ ለተለያዩ ዐማራውን ትኩረት አድርገው ለሚንቀሳቀሱ ወገኖች ጥሪ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ዳግማዊ መዐህድ ይህንን ይዋል ይደር የማይባል አስቸኳይ ጥሪ አሁንም ሁሉም ግለሰቦች፣ ድርጅቶች እና ማህበራት እንዲቀበሉት በድጋሚ ያሳስባል፡፡ ከዚህ ጋር አያይዞ ከዚህ በፊት በተደረገው ጥረት ከተወሰኑ የዐማራ ድርጅቶችና አካላት ጋር አብሮ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ለእነዚህ ድርጅቶች ከፍተኛ ምስጋና ማቅረብ እንወዳለን፡፡ ስለሆነም፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) እና የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ላደረጋችሁት ቀና ዐማራዊ ትብብር በሕዝባችን ስም እናመሰግናለን፡፡

ከዚህም በጎ ጅምር በመነሳት የሚከተሉት ድርጅቶች ለተመሣሳይ ዓላማ በአንድነት እንድንሠለፍ ስንል ጥሪ እናቀርባለን፡፡
ጥሪ የቀረበላችሁ ድርጅቶችም ቤተ ዐማራና ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ናችሁ፡፡

ይህንን ቀና ህዝባዊ ጥሪ በወገናዊነት ተመልክታችሁ እየተሰባሰበ ያለውን ኃይል እንድትቀላቀሉ ስንል በትህትና ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

በተባበረ ክንድ የዐማራ ህልውና ይከበራል!
ድል ለዐማራ ህዝብ!