ወልቃይት ላለፉት ሺህ ዓመታት በትግራይ ስር ተዳድራ አታውቅም – የ700 ዓመት የታሪክ ማስረጃዎች ሰነዶች

Print Friendly, PDF & Email

welkaiyt(Ze Addis)

በህ.ወ.ሀ.ት የሚዘወረው የኢትዮጵያ መንግስት (ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ) አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ከወሰዳቸው ዓብይ ኩነታት አንዱ፣ የሀገሪቱን የፖለቲካን የአስተዳደር ካርታን መቀየሩ እንደሆነ ይታወቃል።

የጥንቱ የኢትዮጵያ ክፍላተ ሀገራት ካርታ በ1994 ዓ.ም ቢቀየርም፣ አዲሱ ካርታ ብዙ የማንነት ጥያቄዎችንና እሮሮዎችን አስነስቷል። ይህ የማንነት መጨፍለቅና የዳግም መካለል ጥያቄ ከሚነሳባቸው ቦታዎች ውስጥ ከጎንደር ተቆርሶ ወደ ትግራይ የተካለለው የወልቃይት ጸገዴና አላማጣ -ዋጃ ሕዝብ አንዱ ነው።

የወልቃይት – ጠገዴም ሆነ የአልማጣ – ዋጃ ሕዝብ ላለፉት 24 ዓመታት ያለማቋረጥ ወደ ትግራይ መካለላቸውን በመቃወም አቤቱት ሲያሰሙ ከረመዋል። ጥያቄውን ለማስቆምና ለመጨፍለቅ ብርቱና ሀግናኝ እርምጃዎች በህ.ወ.ሀ.ት. መራሹ መንግስቱ ቢካሄድም፣ እምቢታው እስካሁን አልቆመም። ይልቁንም የማነት ጥያቄው እየተጋጋለ መጥቷል። በተለይ ላለፉት ስድስት ዓመታት በርካታና ጠንካራ እንቅስቃሴዎች እየታዩ ነው። ይህንን የሚያስተባብሩት የሕዝብ ተወካይ ኮሚቴዎችም የሃምሳ ሺህ ሰው ፊርማ በማሰባሰብ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በመድረስ ሰላማዊ ጥያቄያቸውን እያሰሙ ነው።  ……………   ( ሙሉውን ከዚህ ላይ ያንብቡ, pdf )