የተጨነገፈው ማዕቀብ —H.Res.128

Print Friendly, PDF & Email

(By Mikael Arage)

የሰይጣን ተላላኪው ፣ ሽብርተኛው ፣ ትህምክተኛውና ጠባቡ የህወሃት ስርዐት እሚያከናውነው ዘርፈ-ብዙ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በዓለማቀፍ ሚዲያ ( FOX, REUTERS, BBC, CNN and etc) በተደጋጋሚና በትክክለኛው መንገድ እንዲዘገብ ፣ እንዲታወቅና በስተመጨረሻም የምዕራባውያን ውሳኔ ሰጪ አካላት ጠንካራ ፀረ ወያኔ ማዕቀብ በተገቢው መልኩ እንዲወስኑ ማድረግ አልቻልንም። ሁሉም እዛው በዛው ፣ ከንቱና <እኛው ለኛው> ሆኖ ብቻ ነው የቀረው። ፎክስ ላይ ስለ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሁኔታ በተደጋጋሚ ቢሰራጭ ሪፐብሊካኖች በጠቅላላ ያዩታል። ኤምኤስኤንቢሲ ላይ ስለ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሁኔታ በተደጋጋሚ ቢሰራጭ ዲሞክራቶች በጠቅላላ ያዩታል። የአለም የፖለቲካ ማህደረመረጃ ስርአተ ምህዳር የገባን አይመስለኝም። ስለዚህም የሚዲያ ስልት የለንም። ጠባብና ትናንሽ ነገሮች ላይ አሁንም እየተተኮረ ነው። ሆን ተብሎ ይሁን ወይም ባለማወቅ የተዛነፈ ስልት እየተተገበረ ፣ ዳግም ውድቀት እያመጣ ነው።

እውነቱን ተናግሮ የመሸበት ማደር ! H.Res.128ን ህወሃት በደምብ አድርጎ ጠልፎ አንገዳግዶታል። እሚገርመው ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት አንፃር የረቀቀው እርምጃ እጅግ በጣም አናሳ ነው።

በአሜሪካ ያሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለምን< የረቀቀው እርምጃ በጣም አናሳ ነው!> ብለው በአሜሪካ ሚዲያ ኮንግረስን አያስጠብሱም ስል ፤ መታገል አቅቷቸው ይሁን ወይም የሆነ ጨዋታ እየተጫወቱ ፣ ወያኔ እርምጃውን አስቀጭጮና አራዝሞ ለ ፩ ዓመት አንከባለለው። ይባስ ብሎም በፎክስ ፣ ሮይተርስና ወዘተ የፋናን ዜና አመቱን ሙሉ ሲያሰራጭብን አለፈ።

አሜሪካ ያሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ይህን ለመቀየር ምንም አላደረጉም። አውቆ ቸል ለሚባሉ ወሳኝ ጉዳዮች ነው አሜሪካ ባለው የትውልደ ኢትዮጵያውያን የተቃዉሞ ፖለቲካ — የተዓማኒነትና ሃላፊነትን በብቃት የመወጣት ብቃት — ሙሉ እምነት የለኝም እምለው። በH.Res.128 ህወሃት አሽንፏል። መነጋገር ያለብን <ስለምን የቀጨጨው እርምጃ በዓንድ አመት ውስጥ አላለፈም> ስለሚለው ጉዳይ ነው። ለቬኑዙዌላ ወፍረም እርምጃ በቀናት ውስጥ ነው ያለፈው።

በአሜሪካ ሚዲያ የንፅፅር ግድፈቱን( Double standard) በማሳየት ኮንግረስ ላይ ግፊት ማድረግ ይቻል ነበር። ደባ ተሰርቶብን ፣ ተቆምሮብን ፣ ፋውል እየተጫወቱብንና ዓመቱን ሙሉ አሸንፈውን ፤ ድል አድርገናል ብሎ መጨፈር የጤና አይመስለኝም። ዳሩ ግን ቢዘገይም አሁንም ማረም ይቻላል። ታዋቂ ቢጯ የምዕራባዉያን አውታሮች ላይ ተከታታይ ሰልፍ ማድረግ። በትክክልና በቀጣይነት እንዲዘግቡ ማድረግ። በዚህ መልኩ ብራንድና በዝ ማድረግ ከተቻለ በሶስት ቀን የምዕራባዉያን ሃይሎች ተከታትለው እርምጃ ይወስዳሉ።

he content was originally posted on  https://www.facebook.com/AmharaNetwork/photos/a.493074601074592.1073741829.482849415430444/524263907955661/?type=3&theater