በአማራነታቸው ብቻ በየማጎሪያ ቤቶች የሚገኙ መቶ ሽህ የሚገመቱ የአማራ ወጣቶች ይፈቱ!

Print Friendly, PDF & Email

(ሙሉቀን ተስፋው)

እንደ ብአዴን ታማኝ የህወሃት ሎሌ የትም አይገኝም!

የተጋድሏችን መሠረቶች የወልቃይት ዐማራ የማንነት ጥያቄ አስተባባሪዎች ሕወሓት ስላልፈቀደች አልተፈቱም፤ ኮ/ል ደመቀ አሁንም የአንገረብ ወኅኒ አጥር ውስጥ ነው፤ ንግሥት ይርጋ አሁን ቃሊቲ ናት፤ እነ አታላይ ዛፌ፣ እነ ክንዱ ዱቤ፣ እነ ለገሠ ወ/ሃና አሁንም አልተፈቱም፡፡ እነ መምህር ጌታቸው አዱኛ አሁንም በትግሬዎች እየተሰቃዩ ነው፡፡ ከጎንደርና ከወልዲያ የተወሰዱት ብዙ ሺህ ወጣቶች የትግሬ ጭካኔ መለማመጃ ከሆኑ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡

ይህን ሎሌው ብአዴን ያስፈጽማል ብለን አናምንም፡፡ ብአዴን እንኳ አዲስ አበባና ዝዋይ ያሉትን በባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ወልዲያና ሸዋ ሮቢት ማስፈታት የማይችል የጌቱቹን ዐይን በማየት የሚቅለሰለስ በድን ነው፡፡ እኛ እንዲህ ያለውን ክብር ከብአዴን አንጠብቅም፤ እኛው ራሳችን በራሳችን ላይ እንወስናለን፡፡ በሞታችን አርነት እንወጣለን፡፡

*******

ምስጋናው አንዱአለም

ያለ ቅድመ ይፈቱ

ሀ) በአማራነታቸው ብቻ በየማጎሪያ ቤቶች የሚገኙ መቶ ሽህ የሚገመቱ የአማራ ወጣቶች፡

ለ) በአማራነታቸው ብቻ በትግራይ ባለስልጣኖች እነዚህ ከታች የተዘረዘሩት የወልቃይት ጠገዴ ወንድሞቻችን

1. ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ
2. አቶ አታላይ ዛፌ
3. ጌታቸው አደመ
4. መብራቱ ጌታሁን
5. ተሻገር ወ/ሚካኤል
6. ተስፋሁን ማንዴ
7. ፈጠነ ገብርዬ
8. ነጋ የኔሁን
9. ብርሃኑ ፈረደ
10. መከተ መብራቱ
11. አዱኛ ደምቃ
12. መላኩ ራደ
13. ጎይትኦም ርስቀይ
14. አስቻለው አብርሃ
15. ይመር ዋኘው
16. ግደይ አሰፋ
17. ደርሶ ተስፋሁን
18. ላቀው ብርሃኑ
19. ሲሳይ ዳኘው
20. ሃጎስ በላይ
21. ማሙዬ አርኮ
22. ገብሬ አባይ እንዲሁም በስም ያልተዘረሰርፉ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ወገኖች

ሐ) አማራ ነን በማለታቸው ብቻ በግፍ እየተሰቃዩ የሚገኙት:-

23. ንግስት ይርጋ
24. አግባው ሰጠኝ
25. ጄ/ል አሳምነው ፅጌ
26. ጄ/ል ተፈራ ማሞ
27. ኮ/ል አንተነህ ደምስ እና ሌሎችም

መ) የዋልድባ መነኳሳትና እነ ሌሎች በርካቶች

ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ!!!