ህወሃት በግፍ ያሰራቸውን የአማራ ልጆች በተመለከተ ከአማራ ተጋድሎ የተላለፈ ማስጠንቀቂያ

Print Friendly, PDF & Email

ህወሃት በግፍ ያሰራቸውን የአማራ ልጆች በተመለከተ ከአማራ ተጋድሎ የተላለፈ ማስጠንቀቂያ: –

ከአማራ ተጋድሎ የተላለፈ ማስጠንቀቂያ: –

የህወሃት አገዛዝ በግፍ ያሰራቸውን የአማራ ልጆች በጥቂት ቀናት ውስጥ ሁሉንም ካልለቀቀ በመላው አማራ ምድር ላይ ከፍተኛ የሆነ አመፅ እና አድማ እንደምናካሂድ በጥብቅ እናስጠነቅቃለን!!

በተለይም በእነ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ፣ በንግስት ይርጋና በእነ ጀነራል አሳምነው ፅጌ የክስ መዝገብ እንዲሁም በሌሎች አማራዎች ላይ የተከፈተው ክስ በአስቸኳይ ተቋርጦ ያለምንም ማስረጃ የታሰሩ ወገኖች ሳይውል ሳያድር ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሊፈቱ ይገባል።

ይህ ሳይሆን ቢቀር የሚያስከፍለው ዋጋ እጅግ ከባድ ነው። ስለሆነም ይህ ከመሆኑ በፊት በጊዜያዊነት ከተያዙ አጀንዳዎች ውስጥ የግፍ እስረኞችን መፍታት ሳይውል ሳያድር ሊተገበር ይገባል እንላለን።

ድል ለአማራ ህዝብ!!!