የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ ( አዴኃን ) በጎንደር ጯሂት ወታደራዊ ጥቃት ሰነዘረ!

Print Friendly, PDF & Email

 

በጎንደር ክፍለ ሀገር ጯሂት ወረዳ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ ( አዴኃን ) በወረዳው በአስተዳደር ፅህፈት ቤት ላይ እና በከተማዋ የሚንቀሳቀሱ የፌደራል ፓሊስ እና ፀረ ሽምቅ ግብረ ሃይል ላይ የማያዳግም እርምጃ ወስዷል።

በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የፌደራል ፓሊሶች እና ፀረ ሽምቆች የምሽት አሰሳ የሚያደርጉበትን ቦታና ማረፊያቸውን የአዴኃን ታጋዮች በማጥናት በትላንትናው ምሽት ማለት የካቲት 4 2010 ዓ.ም ሌሊት 9 ሰዓት ላይ በወረዳው አስተዳደር ፅህፈት ቤት ግቢ የሰዓቱን የጥበቃ ተረኛ በማፈን በግቢው በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይገኙ የነበሩት 4 ፌደራል ፓሊሶችና 7 ፀረ ሽምቆች ላይ የቦንብ ጥቃት ሲፈፀም ፅህፈት ቤቱ ላይም በእሳት ጥቃት ተፈፅሞበታል።

በተወሰደው ጥቃትም 8 ቱ ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ 3 በከባድ ቆስለው ለህክምና እርዳታ ወደ ጎንደር ሪፈራል ሆስፒታል ተወስደዋል።

ትግላችን የ አማራ ህዝብ እየደረሰበት ካለው ልዩ የሆነ የፖለቲካ፤ የኢኮኖሚ፤ የማህበራዊ፤ የስነ – ልቦናና የዘር ጥቃት ነፃ ወጦ የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የተከበሩባትና ለዚህም የሚቆሙ ነፃና ገለልተኛ የዴሞክራሲ ተቋማት ዕውን የሚሆኑባት፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት፤ የህዝብ አንድነት፤ ፍቅርና እኩልነት የጠነከረባት፤ ጠንካራና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ዕውን ሆና ማየት።ለዚህም የማንከፍ ለው መስዋዕትነት አይኖርም።

በቁርጥ ቀን ልጆች አጥንትና ደም ወያኔ ይደመሰሳል!!

አማራው ከታወጀበት የዘር ማጥፋትና ማፅዳት እራሱን ይታደጋል!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!