ሁለት ተጻጻሪ የሽግግር አይነቶች! – መቅደላ – የዐኅኢአድ ልሳን

Print Friendly, PDF & Email

ሁለት ተጻጻሪ የሽግግር አይነቶች!

መቅደላ – የዐኅኢአድ ልሳን

የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት በቅርብ ለህዝብ የሽግግር ሰነድ ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው። የዚህን ሰነድ ውስጠ ፍልስፍና ምንነት በሚገባ መተንተንና ለህዝባችን ብቸኛው አማራጭ መሆኑን የማሳየት በድርጅቱ ላይ የወደቀ ሀላፊነት መሆኑን ይገነዘባል። በዚህ አኳያ ህዝባዊ የሽግግር ጊዜ ስንል የህዝባችንን ህይወት ከመቀየሩ አኳያ ስለሚጫወተው ሚና በዝርዝር ማሳየት አስፈላጊ ነው። እናም በተጓዳኝ ከዚህ የድርጅታችን የሽግግር ሰነድ በተጻራሪ የቆመውን የሽግግር አስተሳሰብን ምንነት ማሳየትም ተገቢ ነው። የሚስማማውን መርጦ የመውሰድ የህዝብ ይሆናል።

በቀጥታ የድርጅታችንን የሽግግር ሰነድ ምንነት ከማውሳታችን በፊት ባገራችን ከዚህ በፊት የነበሩ አጥፊ የሽግግር ታሪኮቻችንን ባጭሩ መዳሰስ አስፈላጊ ነው።

የመጀመሪያው ከእምዬ ምንሊክ ህልፈት በኋላ በተፈሪ መኮንንና በአልጋወራሹ በልጅ ኢያሱ ምንሊክ መሀል የተነሳው አስቸጋሪ የሽግግር ታሪክ ነው። የዚህ የሽግግር ጊዜ ዋና መገለጫዎች ተብለው ሊገለጡ የሚችሉት ሶስት ኩነቶች ናቸው።

አንደኛው ዘመናዊነትን በሚደግፉት በተፈሪ መኮንንና በወግ አጥባቂው በኢያሱ ምንሊክ መሀል የነበር በሀሳብ ተፍታቶ ያልተገለጠ ግጪት፣ ሁለተኛው በወቅቱ የተነሳው የአንደኛው የዓለም ጦርነት ላይ ሁለቱ ሰዎች የነበራቸው አቋም መለያየት ነበሩ። ሶስተኛው ከነዚህ የስልጣን ተፋላሚዎች በስተኋላ የቆሙት የውጭ ተጸኖ ፈጣሪ የሆኑ የወቅቱ አቅኚዎች አፍራሽ ሚና ነበር። እነዚህ አፍራሽ ሀይሎችም ከተፈሪ መኮንን ኋላ የተባበረው የእንግሊዝ መንግስት፣ ፈረንሳይና ተባባሪዎቻቸው የቆሙ ሲሆኑ ከአልጋ ወራሹ በስተኋላ የቆመው የዘመኑ የአካባቢው ሀይል ቱርክና የጦር ቃልኪዳን ተባባሪው ጀርመን ነበር። ….. (Read more, pdf)