የዋልድባ መነኮሳት የምንኩስና ቄባቸውን አውልቀው የእስረኛ ዩኒፎርም እንዲለብሱ ታዘዙ፤

Print Friendly, PDF & Email

(ሙሉቀን ተስፋው)

በእስር ላይ የሚገኙ የዋልድባ መነኮሳት

በእነ ተሻገር ወልደሚካኤል ክስ መዝገብ ጥር 30 ቀጠሮ ነበራቸው። ፍ/ቤት ግን አልቀረቡም። ያልቀረቡበት ምክንያት ደግሞ በክስ መዝገቡ የተከሰሱት ሁለቱ የዋልድባ መናኝ መነኮሳት ማለትም አባ ገ/እየሱሰ ኪዳነ ማርያም እና አባ ገ/ሥላሴ ወልደ ሃይማኖት የምንኩስና ልብሳቸውንና አስኬማቸውን አቅልቀው ዪኒፎርም እንዲለብሱ ሲጠየቁ እምቢ በማለታቸው እንደሆነ ታውቋል። በመሆኑም ልብሳቸውን አውልቀው ዩኒፎርም እንዲለብሱ እየተገደዱ ነው ተብሏል።

በኢትዮጵያ ቤ/ክርስቲያን አንድ ሰው ከመነኮሰ በኋላ የምንኩስና ቆብ የሚወልቀው በሃይማኖት ሕጸጽ ተወግዞ የተለየ ሰው ብቻ እንደሆነ ልብ ይሏል።