አቻ የሌለዉ በወሳኝ ወቅት የተገኘ አማራዊ ወጣት ፖለቲከኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች! – ቴዎድሮስ ትርፌ

Print Friendly, PDF & Email

አቻ የሌለዉ በወሳኝ ወቅት የተገኘ አማራዊ ወጣት ፖለቲከኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች! – ቴዎድሮስ ትርፌ

በዉስጡ የሚያቃጥል ቁጭት እና የታመቀ ግፍ ተቀባይነት የወለደዉ እልህ ሲብላላ ይስተዋላል። የተወለደዉ ዛሬ ወያኔ በጉልበት ከጎንደር ቆርሶ ወደ ትግራይ በጠቀለላት የአማራ ከተማ በሞቃታማዋ ሑመራ ነዉ። ገና በልጅነት እድሜዉ ከቤተሠቡ ጋር ወደ አሜሪካ በመሠደዱ ምክንያት ከአማርኛ ይልቅ እንግሊዘኛዉን ዘና ብሎ መናገር ይችላል። ይህ ወጣት ፖለቲከኛ ቴዎድሮስ ትርፌ ይባላል።

ዛሬ ተመልካች እና አይዞህ ባይ ለአጣዉ የአማራ ህዝብ አንደበት ለመሆን ሌት እና ቀን ይተጋል፣ በርካታ የስጋ ዘመዶቹ ተገድለዋል ፣ የቅርብ ቤተሠብ አባላቱ በማዕከላዊ በቶርች ይሠቃያሉ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ሒዎታቼዉን ለማትረፍ በመላዉ አለም ተበታትነዉ በስደት ይኖራሉ። ይህ ከውስጥ የሚንጥ ግፍ ቴዎድሮስን እቅልፍ አልባ አድርጎታል። በአማራ ህዝብ የሚፈፀመዉን ግፍ ለአሜሪካዉያን እዉነቱን ለማሳዎቅ የሚያደርገዉን በብስለት የተመላ ጥረት ስመለከት ታዲያ ቴዲን የወለደች ማህፀን ትባረክ ማለት ወደድኩ።

የአማራ ዘር እየታደነ ሲገደል ለሟቹ ቀርቶ ለገዳዮች የሚቆጨዉ በበዛበት ዘመን እንዲህ አይነት ትንታግ ወጣት ከምድረ አሜሪካ ዳላስ ቴክሳሰ ብቅ ሲል ከማየት የበለጠ ምን ትልቅ የምስራች ይኖረኛል።

ሰው ማለት ሰው የሚሆን ነው ሰው የጠፋ እለት!

ክብር እና ሞገስ ለአማራ ህዝብ አንደበት ቴዎድሮስ ትርፌ ይሁን !
ልያ ፋንታ