የኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት ላይ የፀና አቋም መያዝ ማለት ምን ማለት ነው?

Print Friendly, PDF & Email

የኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት ላይ የፀና አቋም መያዝ ማለት ምን ማለት ነው? ለድርድርም አይቀርብም ሲባል ምን ለማለት ታስቦ ነው?

ዐኅኢአድ ልሣን – መቅደላ ልዩ ዕትም ፯ ጥር ፳፫ ፪ሽ ዓ.ም

በቅርቡ ኅልውናውን ይፋ ያደረገው፣ የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት በፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት ላይ የፀና አቋም አለው፤ በዚህ ጉዳይ ለድርድር አይቀርብም የሚል የጠነከ አቋም እንዳለው ገልጿል። ይህ ሲባል ምን ማለት ነው? የሚሉ ሀሳቦች ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሲሰነዘሩ ይደመጣሉ። ሀሳቦቹን ግልጽ ማድረግም ተገቢ በመሆኑ እንደሚከተለው ይብራራል። ዛሬ በዓለም ዙሪያ ያሉ ሕዝቦች፣ የትም ይኑሩ የት፣ የኛ ብለው ተመልሰው የሚገቡበት መግቢያ ሀገር አላቸው። እነዚህ ሀገሮች እንደየ ታሪካቸው ሕዝቦቹ የተራመዱባቸው የወል ዕሴቶች ባለቤቶች እንዲሆን አድርጓቸዋል። በመሆኑም እነዚህን የጋራ ዕድድገታቸው ውጤቶች የሆኑትን ዕሴቶቻቸውን እንደ ዓይን ብሌኖቻቸው የሚጠበቁ የኅልውና ቅርሶቻቸው ናቸው ። የሁሉም ቤቶቻቸው ናቸው። እነዚህም ከትውልድ ትውልድ ሲወርድ ሲዋረድ የመጡ፣ትውልዱ ከወሪሪ ጠላት እየተከላከለና እየጠበቀ ለተከታዩ ትውልድ ሲያወርስና፣ተረካቢው ትውልድም በተራው ያን ሀገርን ጠብቆ ለተከታዩ ትውልድ የማስተላለፍን አደራ ተግባራዊ ሲያደርግ የመጣ እንደሆነ የኅብረሰብ ዕድገት ታሪካ ያሳያል። ይህ የሰው ልጅ ታሪክ ነው። …. (Read more)