ስዮም መስፍን በመቀሌው ስብሰባ “ከፍተኛና እጅግ በጣም አሳሳቢ አደጋ ተጋጦብናል” አለ!

Print Friendly, PDF & Email

“ጓዶች ከፊታችን የተጋረጠው አደጋ እጅግ፣ በጣም አሳሳቢ ነው” ስዮም መስፍን መቀሌ

ስዮም መስፍን በቅርቡ በመቀሌ በተካሄደው የህወሃት ግምገማ ላይ ከተናጋረው የትግረኛ መልዕክት የተቀነጨበ የሚከተለው ይገኝበታል፡- (ምንጭ፡- www.ethiomedia.com)

“ጓዶች፣ ከፊታችን የተጋረጠው አደጋ እጅግ፣ እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው። ፀሐይ ሳትጠልቅብን በሩጫ፣ ያውም በፈጣን ሩጫ ደረሰን ካልመከትነው ቀጣይነታችን ያጠያይቃል። ያ ሰላም፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ያመጡልኛል ብሎ አምኖ፣ ድሮ ደም እንባ አልቅሶ፣ ልጆቹን የገበረው የትግራይ ህዝብ ከከዳነው ረዥም፣ በጣም ረዥም ግዜ ሆኖናል። ድሮ የከዳነው ህዝብ ዛሬ ሁለት ግዜ እንደሞተ ሆኖ ይሰማዋል። ወዴት እንደሚሄድም ግራ ገብቶታል። ያ የእኛን ቅርስ ወርሶ ወደፊት ይኖራል ያልነው ወጣትም እንዲሁ መሪ ደርጅቱን ከድቶ ግራ ተጋብቶ ይኖራል። ይቅርታ አድርጉል ማለትኮ ጭምትነት ነው። ይቅርታ መጠየቅ ብልህነትና ለሥራ ዝግጁነትን ያመለክታል። ስለዚህ ያ ያስቀመጥነውን ህዝብ ተንበርክከን ይቅርታ መጠየቅ አለብን። ግዜ የለንም። ጓዶች ፈጽሞ የምንዘናጋበት ጊዜ አይደልም።” – ስዮም መስፍን መቀሌ በተካሄደው የህወሃት ግምግማ ላይ ከተናገረው የተወሰደ።

 

 
(ምንጭ፡- www.ethiomedia.com)