የማያባራውን ስርዓት ወለድ የእልቂት ዘመቻ በህብረት እንቅረፈው!

Print Friendly, PDF & Email

አክሎግ ቢራራ (ዶር)

እረጋ ብለን ብናጤነው፤ እኛ ኢትዮጵያዊያን ከሚለያዩን ሁኔታዎች በላቀ ደረጃ የምንጋራቸው ጥሪቶች፤ የታሪክ ሂደቶች፤ ልምዶች፤ የጋራ መነሻዎችና ብናውቅበት፤ የጋራ መድረሻዎች አሉን። ብናውቅበት፤ የተፈጥሮ ኃብታችን ለአገራችን ሕዝብ ፍላጎት ይበቃል፤ ለሌችም ሊተርፍ ይችላል። በዚህ ወር ብቻ ኢትዮጵያ በዓለም ደረጃ ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኝ የወርቅ ኃብት ሊመረትባት የምትችል አገር መሆኗ በሰፊው ተወርቷል። የውሃ ኃብቷ ዝነኛና አኩሪ መሆኑ ከተወራ ቆይቷል። የተፈጥሮ ኃብት እርግማን ወይንም ምርቃን ሊሆን ይችላል። ጥያቄው፤ እነዚህንና ሌሎችን የተፈጥሮ ኃብቶች ማን ይጠቀምባቸው ይሆን? የሚለው ነው።

ቢያንስ ቢያንስ፤ የኢትዮጵያ ህጻናት በቋንቋና በጎሳ ልዩነቶች ላይ በተመሰረተው የህወሕት/ኢህአዴግ አገዛዝ ሊጨፈጨፉ አይገባም ነበር;፡ እነዚህ ለጋውዎችና ጮርቃዎች ምን ወንጀል ሰርተው ነው በዚህ አገዛዝ በተደጋጋሚ፤ በጭካኔና ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ደረጃ የሚጨፈጨፉት? በቆቦ የሰባት ዓመት ልጅ፤ በወልድያ የአስራ ሶስት ዓመት ወጣት፤ ቀደም ሲል በቡኖ በደሌ የሶስት ወር ህጻን ሴት ልጅ ተረሸነች፤ የስድስት ወር ሕጻን ሴት ልጅ ወደ ጉድጓድ ተወርውራ ተገደለች። ይህን ጭካኔ የሚፈጽመው የህወሓት አጋዚና በህወሓት የሚመሩ የፌደራልና ሌሎች ኃሎች ናቸው። ከመቀሌ የበረረው “የትግራይ” ሄሊኮፕተር በንጹሃን አማራዎች ላይ ጭካኔ ሲፈጽም ከዚህ የባሰ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ሊጠበቅ አይችልም። የተቀነባበረው የአማራን ብሄር የማጥፋት እርምጃው ዛሬ ሳይሆን የተጀመረው ህወሓት ሥልጣን ከመያዙ በፊት ነው—ወልቃይት-ጠገዴ። የአማራው ብሄር ተተኪ መሪዎችና ተተኪ ትውልድ እንዳይኖረው የአማራ ህጻናትም ጭምር እየተጨፈጨፉ ነው።

ይህ በቋንቋና በጎሳ ለይቶ ህጻናትን ጭምር የመረሸን በሽታ ከየትና ለምን ተከሰተ? የሚለውን፤ እርህራሄ የሌለው የተደጋገመ ወንጀል መጠየቅና ለዚህ ኢ-ስብአዊ ወንጀል መፍትሄ መፈለግ ያለበት ለሂሊኖው የሚገዛ ግለሰብ ሁሉ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ራሱን ከዚህ እልቂት ማዳን ያለበት አማራውና ኦሮሞው ነው። ኢትዮጵያ ህጻናቶቿንና ሌሎች ልጆቿን እያስጨፈጨፈች ልትቀጥል አትችልም። የህወሓት ኢላማ የሆነው የኦሮሞውን የአማራው ሕዝብ በተለይ፤ ራሱን ከጭፍጨፋና ከውርደት ለማዳን ቆርጦና ተባብሮ ጨካኙን የህወሓትን ነፍሰ-ገዳይ ቡድን በጋራ መታገል አለበት። ይህ ግዙፍና እምቅ ኃይል ያለው ሕዝብ፤ ከአሁን በኋላ ህወሕት ህጻናትን እንዲጨፈጭፍና ኢትዮጵያን እንዲገዛ መፍቀድ የለበትም። ….. (Read more)