“እንቁላል በውጪ ኃይል ከተሰበረ ህይወት ይጠፋል (ይፈጸማል።)”

Print Friendly, PDF & Email

(ከታምራት ይገዙ)

የአገራችን የፖለቲካ ቀውስ በየሴኮንዱ እየተለዋወጠ መሆኑን ሁላችንም እየተመለከትነው ነው ትላንትና ወዲያ ኢትዮጵያዊነት ያንገሸግሻቸው የነበሩት አቶ አባ ዱላ ቡዙዎቻችን ኢትዮጵያኖች ዘንድ ተጠልተው ነበር ትላንትና የዘመኑ አርበኞች ቄሮዎችና ፋኖዎች ባስነሱትና ባቀጣጠሉት ኢትዮጵያዊነት አቶ አባ ዱላም በተወሰነ ደረጃ ከህወሀት ነጻ ወጥተው ታይተው ነበር ዛሬ ደሞ ከወጡበት ከህወሀት ብብት ተመልሰው ሲገቡ እየተሰተዋለ ነው እኔ ለአቶ አባ ዱላ የምላቸው ነገር ቢኖር እናቶቻችን “አውቀሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ” የሚለውን አባባል ነው።

በሌላ በኩል ደሞ የዘመኑ አርበኞች ቄሮዎችና ፋኖዎች መፈክራቸው “ለአገራችን ለኢትዮጵያ ነጻነት የምንታገላውና መሰዋትነትን የምንከፍላው እኛ ድሉ የእግዚአብሔር ነው” ብለውና ተማምለው ትግላቸውን ሲያፋፍሙ ሁኔታው ያላማራቸው አሊያም ከሶስት ወረ በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደሳለኝ ሀ/ማርያም ከህወሀት ድህነቶች በተሰጣቸው ትእዛዝ ከሃያ የሚበልጡትን ባለ ስልጣኖች በሙስና ሊከሱ ነው የምባለውን ወሬ የሰሙት አፈ ጉባዪ አቶ አባ ዱላ ገመዳ በድንገት ተነስተው” የሕዝቤ ክብር በመነካቱ አሁን ባለሁበት ደረጃ ሥራዬን ለመቀጠል የማያስችሉኝ ሁኔታዎች ስለሌሉና ፍላጎቱም ስለሌለኝ በማለት” ከአፈ ጉባዔነታቸው ለመነሳት ለኢሕአዴግና ለኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) መልቀቂያ አስገቡ። …… (Read more, pdf)