ከደብረዘይቱ (ቢሾፍቱ) ኢሬቻ እስከ ወልድያው ጥምቀት በዓል የዘለቀውና ዛሬ ደግሞ ወደ ለየለት የዘር ማጥፋት …

Print Friendly, PDF & Email

ከደብረዘይቱ (ቢሾፍቱ) ኢሬቻ እስከ ወልድያው ጥምቀት በዓል የዘለቀውና ዛሬ ደግሞ ወደ ለየለት የዘር ማጥፋት (Genocide) የተሸጋገረው የትግራይ ፋሽስቶች ፍጅት

ር 21 ቀን 2010 ዓ.ም. (29th of January 2018)

በዶክተር አሰፋ ነጋሽ – (ሆላንድ ሀገር ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ)
Email address: Debesso@gmail.com

ክፍል አንድ (፩) –

ይህንን ጽሁፍ የጻፍኩት በሰሜን ወሎ ዋና ከተማ በወልዲያ የቃና ዘገሊላ በዓል በተከበረበት ወቅት የፋሽስቱ የወያኔ ትግሬዎች መንግስት የፈጸመውንና በሌሎችም የኢትዮጵያ ክፍሎች እየፈጸመ ያለውን ፍጅትና ህዝብ የማፈናቀል ድርጊት የተሰማኝን ለአንባቢዎች ለማካፈል ነው። የወልዲያን ፍጅት ተከትሎ ወራሪው የትግሬ ፋሽስታዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ህዝብ ላይ የከፈተው በእኔ እይታ የዘር ማጥፋት (genocidal war directed against the people of northern Wello by the Tigrean fascist army) ሲሆን በደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ በሚኖሩት ወገኖቻችን የሆኑ የኦሮሞ ተወላጆችም ላይ የከፈተው የፍጅትና የማፈናቀል ድርጊት በአንድ ፋሽስት መንግስት የሚካሄድ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው።

የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ዘንድ እጅግ ታላቅ መንፈሳዊ በዓል ነው። በዚህ በዓል ላይ የወልድያ ወጣቶች ታቦት አጅበው፤ የቀድሞዎን የኢትዮጵያ ባንዲራ ይዘው እየዘፈኑና እየጨፈሩ ኮከብ የሌለበትን የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ ይዘው ይሄዱ ነበር። ለወያኔ ሥርዓት ያላቸውንም ተቃውሞ ሰላማዊ በሆነ መንገድ በመናገር ይገልጹ ነበር። በዚህ ወቅት ትንኮሳ (ህዝብን ተንኩሶ ጠብ በማስነሳትና በዚህም ሳቢያ መልሶ ህዝብን ጥፋተኛ አድርጎ መኮነንና መፍጀት ፋሽስቶች ከሚታወቁባቸው ዓይነተኛ ባህርያት አንዱ ነው። ይህ የወያኔ ድርጊት የጀርመን ናዚዎች እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1933 ዓ.ም. የጀርመንን ፓርላማ አቃጥለው ኋላ ላይ የጀርመን ኮሚኒስቶችን ለድርጊቱ ተጠያቂ አድርጎ በመወንጀል ኮሚኒስቶችን ሰብስበው ያሰሩበትንና የፈጁበትን ድርጊት ያስታውሰኛል) በመፈጸም ጠብ ማንሳት ባህርያቸው የሆኑት በትግሬ ወታደሮች የተደራጀው የአጋዚ ጦር ወጣቶቹ የያዙትን የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ ለመቀማት ሞከሩ። የቀድሞውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ለመንጠቅ የአጋዚ የትግሬ ወታደሮች ባደረጉት ትንኮሳና በጀመሩት በዚህ ግጭት አሳበው ተኩስ በመክፈት አስራ ሁሉት ሰዎችን መግደላቸውንና አስራ አምስት ሰዎችን ማቁሰላቸው ታውቋል (ቁጥሩ ከዚህ በእጅጉ ሊበዛ ይችላል)። ሌላው አስገራሚው ነገር በዚህ ህዝቡ ታቦት ተሸክመው በሚሄዱት ሰዎች መካከል ቀደም ብሎ በተጠና መልክ የመለስ ዜናዊን ፎቶግራፍ የያዙ የህወሃት ሰዎች ህዝቡ መካከል በመግባት ህዝቡን ሆን ብለው ለመተንኮስ ሞክረዋል። ታቦት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ እጅግ የተከበረ የኃይማኖታቸው አንድ መገለጫ መሆኑ ቢታወቅም በይሉኝታ-ቢስነታቸው በሚታወቁት የትላንትናዎቹ የትግራይ ጦረኞችም ሆነ የዛሬዎች የወያኔ ትግራይ ተጋዳላዮች ዘንድ ታቦት አክብሮት የሚቸረው ነገር አይደለም። በጦርነትም ውስጥ እንኳን የሃይማኖት ተቋማት ሆን ተብለው የጥይትና የቦምብ ዒላማ አይደረጉም። ታቦት ተሸክመው የሚጓዙ ቀሳውስት ላይም አስለቃሽ ጢስ የሚተፋ ጥይት አይተኮስም።በኢትዮጵያ ታሪክ የቅርብ ዘመን ታሪክ ውስጥ ቤተክርስቲያኖችና ታቦታት የጦርነት ሰለባ የሆኑት በጣሊያን የፋሽስት አገዛዝ ዘመን (1928-1933 ዓ.ም.) እና በዛሬው …… (Read more, pdf)