መልስ ለበዕውቀቱ ዘኢትዮጵያ:- ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ

Print Friendly, PDF & Email

መልስ ለበዕውቀቱ ዘኢትዮጵያ:- ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ

ጌታቸው ረዳ

ኢትዮጵያ ሐገሬ ስንቱን ደንቆሮ ነው ተሸክመሽ ያማጥሺው? መጥኔ ይስጥሽ ይላሉ የአማራ ሊቃውንቶች። ውጭ አገር ያለው ደንቆሮማ በሰለጠ አገር እየኖረ ከመሰልጠን ይልቅ ድሮ ታሽጎ እንነበረባት ዓለም ውስጥ እራሱን አስገብቶ መልሶ ሲደነቁር ስመለከት ከዚህ ስልጡን ዓለም ሌላ ወዴት ቢሄድ እንደሚሰለጥን ለኔ መልሱ የማላገኝለት ጥያቄ ነው። አቶ በዕውቀቱ ዘኢትዮጵያ ጽሑፉክን ያገኘሁት በወልቃይት.ካም ውስጥ የተለጠፈ ሲሆን ምንጩ እዛው ወልቃይት ይሁን አይሁን አላወቅኩም። መጀመሪያ ነገር ለእንዲህ ያለ ጸሑፍ መልስ ለመስጠት ከልጆች ጋር የመነታረክ ያህል ስለምቆጥረው መልስ ልጽፍ አልፈለግኩም ነበር፡ ሆኖም ዘረኛነትን የተሞረኮዘ ጽሑፍ ስለሆነ ፖለቲካውን እያስታከኩ ትግሬነቴን ለመጐነታታል የሚቃጣቸው እንደ “በዕውቀቱ ዘኢትዮጵያ” ፤ እና እንዲሁም እንደ “የኢሕአፓ ካልቶች” የመሳሰሉ በድርጅትም ሆነ በግለሰብ የሚጽፉ ጎሰኞችን ባይበዛም መልስ መስጠት ስላለብኝ ‘ለምን ናቅከኝ እንዳይል መልሴም ይኼው ባጭሩ።

በመጀመሪያ አንባቢዎቼን ለማስገንዘብ የምፈልገው፤ ስማቸውን የሚደብቁ፤ ፎቶግራፋቸውን ለሕዝብ የማያሳዩ፤ ማንነታቸውን ላለመግለጽ የሚፈሩ ፈሪዎች ጋር መልስ መሰጣጣት ፈሪና ጎበዝ አብሮ እንደማይሄድ እንድታውቁልኝ ሁሌም የማስገነዝባችሁ ጉዳይ ነው። ይህ ሰውም ሆነ በርካታ ጸሐፊዎች ለምን ትክክለኛ ስማቸው ከነ ፎቶግራፋቸው ከአንባቢዎቻቸው ጋር ለመተዋወቅ እንደሚፈሩ ብትጠይቁ፤ አንድ የምትረዱት ነገር “የሚፈሩት ነገር ስላለ ድፍት ያጣሉ”። ድፍረት የሚያጡ ደግሞ እንደ ዓይጥ ተሸሽጎ መጮሕ ለፍርሃታቸው እንደድፍርት የሚተኩበት ዘዴ ነው። እራሱን ለአደባባይ ማሳያት ያልፈቀደ ደግሞ ‘ታማኝ’ አይደለም። ከትግሉም መራቅ አለበት። ተንኮለኛ ነው፤ ፈሪ ነው ማለት ነው። እንዲህ ያሉ ዜጎች ደግሞ መጥፎ ነገር ከመስራት አይቆጠቡም። ከራሳቸው ጋር ግንኙነት የላቸውም፤ ከራሳቸው ጋር አምነትና ውል አላደረጉም።ባጭሩ ከራሳቸው ጋር ያልተማማኑ በውጭ አምነት ሊያሳድሩ ከቶ ባሕሪያቸው አይፈቅድላቸውም። ስለዚህ እባካችሁ በይፋ ማንነታችሁን ማሳየትን ተለማመዱ፡ የሚያስፈራ ዓለም አድርጋችሁ አትዩ። ፍርሃትን ከሰበራችሁ ማንነታችሁ ኩራትን ያጎናጽፋል እና ከፍርሃት ቆፈን ሰብራችሁ ውጡ። ወንጀል የሰራችሁ የድሮ <ባለጌ ፖለቲከኞች> ካላችሁም ፖለቲካው ውስጥ አትግቡ። በድብቅ በሌላ ስም መዋሸት ይቻላል ፤ መድረኩ ግን ለናንተ አይመችም። …. (Read more, pdf)