አማራ ክልል ተወላጆች በመሆናቸው ብቻ በህወሃት ትዕዛዝ በግፍ ዜጎች ተፈናቀሉ!

Print Friendly, PDF & Email

(By Ethio Sun)

ጥር 20 ቀን 2010 ዓ.ም የአማራ ክልል ተወላጆች ከአላማጣ እና ራያ፣ በህወሓት አጋዚ እና የደህንነት አባሎች ድንገተኛ ጥቃት ተፈፅሞባቸው። ምንም ነገር ዛይዙ ሕፃናት፣ አዋቂዎች፣ ሴቶች፣ የጤና ችግር ያለባቸው ቁጥራቸው በርከት ያሉ ሀብትና ንብረታቸውን ጥለው፣ ከ2 ቀን ጉዞ በኋላ ደቡብ ጎንደር ዞን ሊቦከምከም ወረዳ አዲስ ዘመን ከተማ ገብተዋል።

በግፍ ከተፈናቀሉት ውስጥ የመንግስት ሰራተኞች፣ መምህራን እና በሌላ ተቋማት የሚሰሩ ይገኙበታል። ይህን ግፍ ያዩ አንዳንድ የአላማጣና የራያ ሕዝብ እነዚህ ሰዎች ለምንድን ነው በግፍ የሚባረሩት፣ እናንተ አባራሪዎች የመከላከያ ልብስ ለብሳችሁ ዘርን እየላያቹሁ ማባረሩ ጥሩ ስራ አይደለም በኃላ ዋጋ ያስከፍላችኋል በማለት ተናግረዋል።

ይህ ዓይነቱ ግፍ በዜጎች ሲፈፀም “የአማራ ክልልን አስተዳድራለሁ” የሚለው ብአዴን የባሪያነቱን ተግባር በቃል አቀባዩ አማካኝነት አሳፋሪ መግለጫ ሰጥታል። ይሄን የማፈናቀል ተግባርንም አላወገዘም። በመሆኑም ብአዴን ከሕዝብ ወገን ተነጥሎ ለአሳዳሪው ህወሓት ሎሊነቱን አስመስክራል።

በመሆኑም አንዳንድ አድርባይ የሆኑ ከፍተኛ የብአዴን አመራሮች የቆሙበትን ሁኔታ በመመልከት ሌሎች የድርጅቱ አባሎች አሰላለፋችሁን እንድታስተካክሉ ጥሪያችንን እያቀረብን ሕዝብን በጅምላ እየጨፈጨፋቹሁ እና በግፍ እያፈናቀላችሁ ያላችሁ የህወሓት ዘረኞች ዋጋችሁን ታገኛላቹሁ።

ድል ለሕዝብ!
ከፋኝ ዘመቻ ነፃ ትውልድ!!