ለአቶ ዳኛቸው ተሾመ እና ለአሜሪካ ድምጽ አማርኛ ራዲዮ አዘጋጅ ሰለሞን ክፍሌ

Print Friendly, PDF & Email

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)

ባለፈው ሰሞን “የአለም አቀፍ ትበብር ለኢትዮጵያዉያን መብት (Global alliance for the right of Ethiopians) የቦርድ አባል ነኝ ብለው በአማርኛ ድምጽ ራዲዮ በ1/25/2018 (ፈረንጅ አቆጣጠር) በሳይንስና ቴክኖሎጂ ክ/ጊዜ የተጋበዙት አቶ ዳኛቸው ተሾመ የተባሉት ‘የሰውን ማንነት’ (እሳቸው በሳይንሳዊ ጥበብ የታገዘ ሰዎችን በድምፅ የመለየት ጥበብ ተመርቄበታለሁ ይላሉ) ድምጽን የመለየት ጥበብ (ሳይንሳዊ ኢንቬንሸን) የተማርኩበትና የፈጠራ ውጤትም አድርጌአለሁ በማለት በዚህ ቴክኖሎጂ በማስተዋወቅ ስራ እንዳሉ ይናገራሉ። ለዚህ መስክ እንዲሰለፉ ምን አነሳሳዎት ተብለው ሲጠየቁ፤ ሕዝባችን እያሰቃዩ ወደ እዚህ ዓለም የሚመጡትን ወንጀለኞች ፎቶግራፍ፤ የመሳሰሉት “የመረጃ ማከማቻ” ውስጥ በማስቀመጥ ተፈላጊ ሰው ሲኖር በቀላሉ ማስያዝ እንዲቻል በበኩሌ አስተዋጽኦ ለማድረግ ነው፡ ይላሉ።

ለመሆኑ እንናተ እነማን ናችሁ? ተብለው ሲጠየቁ “የኢትዮጵያዉያንን በደል ለማስቆም” የተቋቋምን፤“የአለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዉያን መብት (Global alliance for the right of Ethiopians) የቦርድ አባል ነኝ” ሲሉ ለጋዜጠኛ ሰለሞን ክፍሌ ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል። ግሎባል አላያንስም ይህንን ጥናት እንዳደርግ ታዝዤ ነው፤ በዛ መሰረት ነው ይህን ለማድረግ የገባሁት እና ይህንን ለማስታወስ እፈልጋለሁ” በማለት ተናግረዋል። እኚህ ሰውየ ……የቦርድ አባል ነኝ እያሉን ያሉት ድርጅት የተፈናቀሉት ወገኖችን ለመርዳት ያደረገው በጎ ተግባር እንደሰራ ባውቅም፡ ያንን በጎ ጐኑ እንዳለ ሆኖ፤ “የአለም አቀፍ ትበብር ለኢትዮጵያዉያን መብት (Global alliance for the right of Ethiopians የተባለው ድርጅት ሊያደርጋቸው የሚፈልገውን የድርጅቱ ተልዕኮ http://www.defendethiopians.org/about/ የሚለው ድረገጹን ስንጐበኝ የሚነግረን የመጻፍ፤ የመናገር፤ የመከራከር የተነፈገው የዜጋችን መብት እንዲከበር በጽናት ይሠራል ይላል። ይህንን ሳነብ ትንሽ “ያዝ አደረገኝ”። ሦስት ምክንያቶችን ላቅረብ (በጥቂቱ ማለት ነው)

“የአለም አቀፍ ትበብር ለኢትዮጵያዉያን መብት (Global alliance for the right of Ethiopians (GARE)” የተባለው ድርጅቱን በግምባር ቀደም የሚያንቀሳቅሱት ደግሞ “የግንቦት7 አባሎች እና ከግንቦት 7 በጎ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ” እነ ንአምን ዘለቀ፤ታማኝ በየነ፤ ሉሊት፤ እነ ሜሮን…………እንዲሁም እነ አክሎግ ቢራራ፤ እነ አል ማርያም…….ወዘተ የመሳሰሉ ናቸው። ግንቦት 7 የተባለው ድርጅት ደግሞ በሰብአዊ መብት ጥሰት በታጋዮቹ በኩል ብዙ አቤቱታ እና ቅሬታ የደረሰበት ድርጅት መሆኑን ጋዜጠኛ ሰለሞን ክፍሌም ሆነ አቶ ዳኛቸው ተሾመ አያውቁም ተብሎ አይገመትም። ለዚህ ነው አቶ ሰለሞን ክፍሌ ጠለቅ ብሎ ስለ ድርጅቱ ምንነትና እነማን እንደሚመሩት፤ ድርጅቱ በሰብአዊ መብትም ሆነ በመናገር ነፃነት ያላቸው ማሕደር ምን እንደሚመስል አልወጠራቸውም ብየ ይህ የቅሬታ ደብዳቤ እንደጽፍ የተገደድኩት። ይህ ድርጅት ስለ መናገር፤ስለመከራከር፤ስለመጻፍ ነጻነት አምናለሁ ለዚህም የቆምኩኝ ነኝ፤ የሚለን ድርጅት በመሪነት የሚመሩት ሰዎች አነ ታማኝ በየነ፤ እነ ንአማን ዘለቀ….ናቸው። ንአምን እነ ሉሊት….ወዘተ ተወቃሽ የድርጅት አባሎች ስለሆኑ እዚህ አልጠቅሰውም። ታማኝ ጋር ነው የማተኩረው። ይህ አቶ ዳኛቸው በቦርድ አባልነት አለሁበት የሚሉትንም ጭምር በጥቂት ማስረጃ ልተች። ….. (Read more, pdf)