ሕዝብን በመግደልና በማፈን ሰላም አይመጣም! – ከኢሕአግ የተሰጠ መግለጫ

Print Friendly, PDF & Email

ሕዝብን በመግደልና በማፈን ሰላም አይመጣም!!

ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የተሰጠ መግለጫ
ታህሳስ 18/2010

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በአማራ ክልል፣በኦሮሚያና በኢትዮ ሶማሌ ክልል በአንባገነኑ የወያኔ መንግስት አገልጋይ አጋዚ ጦር እየተፈጸመ ያለውን ግድያና አፈና እንዲሁም እስራት የተጀመረውን ትግል ያጠብቀዋል እንጂ ቅንጣት ታህል አያበርደውም።

በሃገራችን ኢትዮጵያ እየተቀጣጠለ ያለው የመናገር ፣የመጻፍ ፣ የመሰብሰብ ነጻነት እና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ህዝባችን ተገፎ መሪዎቹና ጦማሪዎቹ በሃሰት ውንጀላ ተከሰው ለበርካታ ዓመታትና ወራት በእስር እየተሰቃዩ ለመሆኑ የአደባባይ ሚስጢር ነው።

ህዝባችን ጦም ውሎና ጦም አድሮ ያሳደገውን ልጁን ተናገረ ተብሎ የሚገደልበት፣እናት ልጇ እሬሳ ላይ እንድትቀመጥ ተገዳ የምታለቅስበት፣ ቁስለኞች በቤተሰባቸው ፊት በጥይት ተደብድበው የሚገደሉበት ፣ህግ አልባው መንግስት ዜጎችን በመሳሪያ አስገድዶ አስሮና አዋርዶ ወደ ማሰቃያ እስር ቤት የሚልክበት ሃገር ቢባል ከዓለማችን ቢፈለግ በደረጃ ውስጥ የምትገኘው ኢትዮጵያ ናት። … (Read more, pdf)