ሀዘናችሁ ሀዘናችን ነው – አንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ ጋዜጣዊ መግለጫ

Print Friendly, PDF & Email


ሀዘናችሁ ሀዘናችን ነው! (ጥር 12 ቀን 2010 ዓ.ም. በወልዲያ ለተገደሉ ወገኖችን)

አንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ ጋዜጣዊ መግለጫ

ቀን ፡ ጥር ፲፭ ቀን ፪ ሺህ ፲ ዓ.ም. (January 23 2018)

ደም አልጠግብ ያለው ወያኔ እስር ቤት እዘጋለሁ ያለው ምላሱ ሳይደርቅ ወልድያን በደም አጠባት። ወያኔ ከማሰር ይልቅ በየአደባባዩ መግደሉ፣ የንፁሃንን ደም ማፍሰሱ ዕድሜ እንደማይቀጥልለት ቢረዳውም ደግመን ደጋግመን እንዳልነው አረመኔያዊ፣ አውሬያዊ ባህሪውን እጅጉን እየገፋበት እንደሆነ ይስተዋል።

እባብ ጭንቅላቱን ካልተመታ መርዛማነቱን አይተውምና ወያኔና አጃቢዎቹን የሚከፈለው መስዋዕትነት ተከፍሎ ባፈሰሱት ደም እንደ ጲላጦስ ሳይሆን እንደ ዲያብሎስ ፍርዳቸውን ማግኘት ይኖርባቸዋል። ዛሬ በመላዋ የሀገሪቱ አካባቢ እየተቀጣጠለ ያለው ሕዝባዊ ዓመጽ ማቆሚያው ወያኔ መቃብር ላይ መሆን ይገባዋል ስንል ርህራሄ የሌለው ገዳይ አገዛዝ ነውና ነው። የሚፈሰው የሕፃናትና የወጣቶች ደም በመካሄድ ላይ ያለውን ሕዝባዊ ትግል ይበልጥ ጉልበትና ኃይል ሰጥቶት በሀገራችንና በሕዝባችን ላይ ለ27 ዓመት የጨፈረው ፋሽስታዊና ዘረኛ አገዛዝ ፍርዱን እንዲያገኝ ሁላችንም በምንችለው አቅምና ጥረት የትግሉ ሙሉ ተካፋይና አጋር መሆን ይገባናል ስንል “አንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ” ድምጻችንን እናሰማለን። (Read more, pdf)