ዶ/ር ሃይሉ አርአያ ማዕከላዊ ውስጥ ያጋጠማቸውን እንዲህ ሲሉ ነበር የገለጹት

Print Friendly, PDF & Email

ዶ/ር ሃይሉ አርአያ

ዶ/ር ሃይሉ አርአያ ማዕከላዊ ውስጥ ያጋጠማቸውን እንዲህ ሲሉ ነበር የገለጹት

“ከቤቴ እየደበደቡና እየተሳደቡ የወሰዱኝ የትግራይ ልጆች ነበሩ። ማዕከላዊ እንደደረስኩ ቀበቶዬን ያስፈታኝ የትግራይ ሰው ነው። ከእርሱ ተቀብሎ አንድ የፍሪጅ ያህል የሚቀዘቅዝ ክፍል አስገብቶ የቆለፈብኝ የትግራይ ሰው ነው። ሲመሽ ሽንት ቤት ወስዶ ያሸናኝ ሰው የትግራይ ሰው ነው። እየተሳደበ ቃሌን የተቀበለኝ የትግራይ ሰው ነው። በእርግጥ እኔ የትግራይ ሰው ሆኜ ከአንድ አካባቢ በወጡ ሰዎች ጥቃት እየደረሰብኝ እንደሆነ ከተሰማኝ ሌላው ሰው ምን ሊሰማው እንደሚችል አስቤ ለትግራይ ህዝብ ከልቤ አዘንኩለት። ይሄ ሁሉ የሚደረገው ለትግራይ ህዝብ ሲባል ነው መባሉ ደግሞ የበለጠ ሰላሜን ነሳው።”