ሁለት ከፍተኛ የህወሃት ባለስልጣናት ከ9 ሚልዮን ብር በላይ ያጭበረበሩበት ሰነድ ተጋለጠ

Print Friendly, PDF & Email

የህወሃት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የትግራይ ጤና ቢሮ ሃላፊ የሆነው ዶ/ር ሃጎስ ጎድፋት ከፌድራል የኤዲስ መቆጣጠሪያና መከላከያ ምክትል ዳርሬክተር ጀንራል ከሆነው ከአቶ አብረሃም ገብረመድን ጋር በመተባባር በGlobal Fund’s NFM Programme ለኢትዮጵያ በርዳታ ከተሰጠው ብር ውስጥ ከ9 ሚልዮን ብር በላይ የሆነውን ገንዘብ በትግራይ ጤና ቢሮ ስም አጭበርብረው ሊወስዱ እንደነበር የተጻጻፉበትና አሁን ሕዝብ እጅ ውስጥ የገባው ደብዳቤ ያስረዳል።

ሁለቱ የህወሃት ባልስልጣናት ገንዘቡን ለማጭበርበር የተጠቀሙበት ዘዴና መንገድ እንደሚከተለው ነው። ለትግራይ ክልል በብር (Birr ) የተጠተየቀውን በጀት በአሜሪካ ዶላር (USD) በመላክ ነው።

የህወሃት የማ/ኮሚቴ አባል እና የትግራይ ጤና ቢሮ ሃላፊ የሆነው ዶ/ር ሃጎስ ጎድፋት የሆነው ሰው የፌድራል የኤዲስ መቆጣጠሪያና መከላከያ ምክትል ዳርሬክተር ጀንራል የሆነው ከአቶ አብረሃም ገብረመድንን ለትግራይ ክልል አገልግሎት የሚሆን 340,063 ብር በጀት ይጠይቃል። የፌድራሉ የጤና ሃላፊ አቶ አብረሃም ለትግራይ ክልል በዶ/ር ሃጎስ የተጠየቀውን 340,063 ብር መላክ ሲገባው 340,063 የአሜሪካን ዶላር ወይም 9,243,116 /ዘጠኝ ሚልዮን ሁለት መቶ አርባ ሶስት ሺህ አንድ መቶ አስራ ስድስት / ብር እንዲላክ ያደረጋል።

ሁለቱ የህወሃት ባላስልጣናት ያጨበረበሩት ገንዝብ ድምጣቸውን አጥፍተው በመብላት ላይ ሳሉ አንድ የፌድራል ኤች አይቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠያ ጽ/ቤት (HAAPCO ) ሰራተኛ ሲጋለጡ ባንኩ የተጠየቀውን ገንዘብ በብር መላክ ሲገባው በአሜሪካን ዶላር በመላኩ የተፈጠረ “ስህተት” ነው ብለው ለማስተባበል ሞክረዋል።

ለማንኛውም ሁለቱ የህወሃት ባለስልጣናት ለማጭበርበር የሞከሩትን 9,243,116 /ዘጠኝ ሚልዮን ሁለት መቶ አርባ ሶስት ሺህ አንድ መቶ አስራ ስድስት / ብር የሚያጋልጠውን ሰነድ ከዚህ በታች ያንብቡ።

በዘመነ ትግሬ ትግራይ ከፌድራል መንግስት በጀት በብር ትጠይቃለች የተጠየቀችን ያክል ገንዘብ በአሜሪካን ዶላር ይላክላታል!!

(ዘጠኝ ሚልዮን ሁለት መቶ አርባ ሶስት ሺህ አንድ መቶ አስራ ስድስት ብር ለማጭበርበር የተሞከረበትን ሰነድ ለማንበብ ከዚህ ላይ ይጫኑ)