አረመኔው የትግሬ ወያኔ ያፈሰሰው የወጣት ደም የጥምቀት ደም ነው! – መቅደላ – የዐኅኢአድ ልሳን

Print Friendly, PDF & Email

አረመኔው የትግሬ ወያኔ ያፈሰሰው የወጣት ደም የጥምቀት ደም ነው!

የትግሬ ወያኔ በወልድያ አደባባይ ላይ የወጣት ደም አፍሷል። ይህ እምነት የለሽ አረመኔ ባንዳ ያፈሰሰው የወጣቶች ደም የክርስቲያን ኢትዮጵያን ደም ነው ። ትናንት በሀረር ጨለንቆ፣ በሲዳሞ ሻሸመኔ፣ በኤሉባቦር በደሌ፣ በሸዋ አምቦ፣ በበጌምድር ጎንደር፣ በጎጃም ባህርዳር፣ በወሎ ወልድያና የተለያዩ ከተማዎች በወያኔ ባንዳ የደረሰውና በመድረስ ላይ ያለው እልቂት ኢትዮጵያውያን ለነጻነት የሚከፍሉት ዋጋ ነው። ይህ የትግላቸውን መሰባሰብ ያሳየና በጋራ ለነገ የጋራ ሀገራቸው በመክፈል ላይ ያሉት መስዋእትነት ነው። ወጣቱ የሚመራው ትግል በመሆኑ ያንዱ መስዋእት መሆን ለተከታይ ወንድሙ በቀል ቀስቃሽ ነውና ባንዳው እንደሚያልመው ትግሉ በጭፍጨፋ የሚቆም ሳይሆን ይበልጥ ይነዳል። ይበልጥ የትግል አድማሱን ያሰፋል። አዳዲስ ታጋይ ወጣቶችን በትግሉ ሜዳ ላይ እንዲሰለፉ ጥሪውን ያስተላልፋል።

በወጣት ደም የጨቀየች የወሎ፣ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የሸዋ፣ የሀረር፣ የወለጋ፣ የሲዳሞና የኤሉባቦር መሬት እምቡጥ ታጋዮችን ነው የምታፈራ። የትግሬ ወያኔን ድባቅ ሳይመታና ኢትዮጵያ ሀግሩን ነጻ ሳያደርግ ላይመለስ እጅ ለጅ የተያያዘ አዲስ ትውልድ ከመድረኩ ላይ ወጥቷል። ከእንግዲህ ነጻነትን ለራሱ፣ አንድነትን ለህዝቡና ሉዐላዊነትን ለሀገሩ እውን ሳያደርግ ላይመለስ የተነሳ ጠላት ከወያኔ ፈት ቁሟል። ይህንን የነደደ የወጣት ኃይል ምንም ኃይል የሚያቆመው አይሆንም። የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት በነዚህ ቅዱሳን ወጣት ኢትዮጵያውያን ላይ በባንዳ የትግሬ ወያኔ የደረሰን ጭፍጨፋ በቁጭትና በመጠቃት መንፈስ በአክብሮት ያስበዋል። ….  (Read more, pdf)