ትግራይ ተጠቃሚ አይደለም ለሚሉ መልሴ ይኼው ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ ክፍል 1

Print Friendly, PDF & Email

ትግራይ ተጠቃሚ አይደለም ለሚሉ መልሴ ይኼው

ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ

ክፍል 1

ጌታቸው ረዳ

በመጀመሪያ ሰሞኑን የጥምቀት በዓል ለማክበር በወጡ የወልድያ ኗሪዎች በወያኔ ትግራይ ፋሺሰት ስርዓት ጥይት ለተገደሉ ዜጎቻችን ጽናቱን እና ብርታቱን እንዲሰጣቸው ለሟቾቹ ቤተሰቦች እና ለከተማው ማሕበረሰብ ጽናቱን ይስጣችሁ እላለሁ። ይህ ሃዘንና ግጭት በአማራ አካባቢ መድረሱን የሚያሳየን ለርዕሴ ይነተኛ ግልጽ የመከርያ ማስረጃ ነው። ስለሆነም በርዕሱ ላይ በጥልቀት እንመለከታለን። ርዕሱ በ2 ክፍል አቀርባለሁ። ይህ ክፍል 1 እንደመግቢያ ስለሆነ ዝርዝሩን በክፍል 2 ይቀርባል። በድረገጾች ትግራይ በዘመነ ወያኔ ተጠቃሚ ነው አይደለም የሚሉ ክርክሮች ወሩን በሙሉ ሲያከራክር መኖሩ ተመልክቻለሁ።በሌሎች ጉዳዮች ተጠምጄ ስለነበር ቀልብ አላደረግኩበትም ነበርና ዛሬ እተችበታለሁ።

ኢትዮ-ሚዲያ የሚባለው ድረገጽ ብዙውን ጊዜ አልጎበኘውም፤ ዛሬ፤ ዛሬ አንድ ድረገጽ ከጎበኘህ ሁሉንም ማየት አያስፈልግህም። ምክንያቱም ሁሉም የሚለጥፉዋቸው ጉዳዮች ከአገር ውስጥ የሚያገኙዋቸው ጋዜጦች ከሚያወጡዋቸው ዜናዎች እየኮረጁ ስለሚለጥፏቸው ተመሳሳይነት ስላላቸው አንድ ድረግጽ በቂ ነው። እንዳውም ስንቶቻችሁ ታውቁ እንደሆነ አላወቅኩም እንጂ “Ethioexplorer.com” የተባለ ድረገጽ በየድረገጹና ራዲዮን ጣቢያዎች የተለጠፉት ሁሉ ሰብስቦ ባንድ ገጽ ርዕስ ርዕሶቹን ብቻ በማቅረብ መክፈቻ ቁልፎቹን በመጦቆም ወደ ኢመይልህ ስለሚልክ እየዞርክ ድረገጾችን ለማየት ጊዜ ከማጥፋት ያዳነኝ ይህ ታምረኛ ድረገጽ ዜናዎቹን በሙሉ ሰብስቦ ስለሚልክልኝ የምፈልገውን ብቻ እያነበብኩ ድረገጾችን ብዙውን ጊዜ ከመጎብኘት ስላዳነኝ Ethioexplorer.com” ካልዘገየኝ በስተቀር ኢትዮሚዲያም ሆነ ሌሎቹ አዘውትሬ አልጎበኛቸውም።

ይህ ካልኩኝ ዘንድ፤ ሰሞኑን ኢትዮ-ሜዲዮ ስጎበኝ አብርሃ በላይ በሚያካሂደው በዚያ ድረገጽ ውስጥ ዶ/ር አወል አሎ (ካሳሁን ከተባለ የኢሳት ጋዜጠኛ ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ) እና አቤ ተኩቻ (ፌስ ቡክ/ብሎግ ይመስለኛል) ሁለቱም “የትግራይ ሕዝብ ተጠቃሚ አይደለም”፤ወይንም “ያለው ስርዓት የትግሬዎች መንግሥት ሥርዓት አይደለም” ብለው ስለሚከራከሩ፡ አብርሃ በላይ የህችን የሚል ሰው ሲያገኝ “ደስታው የሰማይን ጣራ ስለሚነካ” የድረገጹ ማሸብረቂያ በማድረግ ሞቅ ባለ የትግርኛ ዘፈን በማጀብ Activist warns against danger of lumping the Tigrai people with the ruling TPLF regime (By Ethiomedia January 15, 2018)

እና ሌላው ሁለተኛ ለመከራከሪያ ድጋፍ ያቀረበው ቪዲዮም Separate the wheat from the chaff: Tigrai people are no TPLF substitute! By Ethiomedia January 12, 2018 የሚል ርዕስ አበጅቶለት ቪዲዮውን አስደምጦናል። ተቃራኒ ያላቸው ሃሳቦች ግን ቢሞት አያስተናግደም። ጋዜጠኛ ብሎ ዝም!!!!

የነዚህ ወገኖች እምነታቸው የተጠበቀ መብት ሆኖ፤ መከራከሪያ ነጥባቸው ግን ልክ አብርሃ እንዳስቀመጠው ‘እህሉ ከገለባው’ መለየት አለብን ሲለን ዶ/ር አወል የተባለው ወጣት ደግሞ “ሊሂቁ ከሕዝቡ ለይተን ማየት አለብን ሲል ተከራክሯል። የክርክራቸው ጭብጥ በዚህ ያጠነጠነ ነው። ጥልቅ መከራከሪያ ነጥብ አላስቀመጡም።

በዚህ ምዕራፍ 1 ጽሑፌ ኢትዮሜዲያ ባለቤት የሆነው የአቶ አብርሃ በላይ የጋዜጠኛነት ወገንተኛ ባሕሪ ሳልገልጽ ወደ ክርክር አላልፍም (የብዙዎቹ ውጭ አገር ያሉ ጋዜጠኞች ተብየ ድረገጾች ባሕሪ ተመሳሳይ ቢሆንም…)። የአብርሃ በላይ ለየት የሚያደርገው “ትግራይ ሕዝብ በዘመነ ወያኔ ተጠቃሚ ነው፤ ወይንም ትግሬዎች በሥልጣን ላይ ናቸው”፤ ወይንም “ትግሬዎች እንደተቀሩት ማሕበረሰቦች ተመሳሳይ ግፍ እየደረሰበት አይደለም”፤ ወዘተ… የሚል ተከራካሪ የጻፈውን መከራከሪያ “ቢሞት” ድረገጹ ላይ አይለጥፈውም። የነዚህ ሁለት ወገኖች ግን አሸብርቆ ለጥፎላቸዋል። ይህንን በምሳሌ አስደግፌ ወደ ክርክር ልለፍ (ስንነጋገር ሕዝቡና የታሪክ ማሕደር እንዲያውቀው ማድረግ የግድ ስለሆነ አብርሃ በላይ በልምድ ያገኘው ጋዜጠኛነት ሙያው ለተጠቃሚው ሕዝብ ከተጻራሪ ክፍል የሚሰጡ አስተያየቶች እና አስተምህሮዎች ለድርገጹ ጎብኚዎች እኩል ያስተናግዳል ወይስ እንደ ወያኔዎች ወገንተኛ አገልግሎት ብቻ የተመረኮዘ አሰራር? የሚለውን በማስረጃ እንናንተ ግንዛቤ እንዲኖራችሁ ታሪክም አብሮ እንዲዘግበው ላቅርብ።

አብርሃ በላይ የማይወዳቸው (እራሱም ሆነ ሌሎች እንዲከራከሩበት የማይፈቅድ) ነጥቦችን ላስጨብጥ። “የትግራይ ሕዝብ ተጠቃሚ ነው” ወይንም “ስርዓቱ የትግሬዎች መንግሥት ነው” የሚሉ ወይንም “ኦሮሞዎች የድሮ ስማቸው “ጋላዎች” ይባሉ ነበር፤ ስለሆነም “ጋላ” ማለት ስድብ አይደለም። ስድብ ነው ብለው ያለ ምንም ማስረጃ ሕዝቡን የሰበኩትና ያወናበዱት “የኦሮሞ ሊሂቃኖች/መኢሶን እና ኦነጎች” ናቸው”፤ “ጋሎች” በ16ኛው ክፍለዘመን የዛሬትዋን ኢትዮጵያን ወርረው የብዙዎቹ ነባር ከተሞችና አካባቢዎች ስም ሰርዘው የኦሮሞ ስም ሰጥተው ዝርያቸው አሁንም በተጠቀሱት አካባቢዎች ዛሬም ይገኛሉ፡፡” የሚሉ ተከራካሪዎች፤ ወይንም የሚሉ የታሪክ ጸሐፍትን እና ጽሑፎችን በድረግጹ አያስተናግድም። ይህንን በማስረጃ ለዶ/ር አሰፋ እና ለ ዶ/ር ጌታቸው ሃይሌ ምን ብሎ እንደጻፈላቸው በማስረጃ ላቅርብ። ….. (Read more, pdf)