ከትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ውድቀት በኋላ ወዴት? – መቅደላ የዐኅኢአድ ልሳስን – ልዩ ዕትም

Print Friendly, PDF & Email


ይድረስ ለኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ!

ጥሪ – ከትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ውድቀት በኋላ ወዴት?

ጥር ፯ ቀን ፪ሺ፲ ዓ.ም(January 15,2018)

ወያኔ እንዴት ይወድቃል? መቼ ይወድቃል? የሚሉት የሕዝባችን የ27 ዓመታት መሠረታዊ ጥያቄዎች ሆነው የዘለቁ መሆናቸው ይታወቃል። የመውደቂያ ቀኑ ይህ ነው ተብሎ በግልጽ ተለይቶ አይታወቅ እንጂ፣ የትግሬ ወያኔ አገዛዝ እንደማነኛውም አምባገነን አገዛዝ በሕዝብ አመጽ መውደቁ የማይቀር እንደሆነ ከታሪክና ከኅብረተሰብ ዕድገት ተመክሮ የሚታወቅ ነው። የአወዳደቁ ሁኔታም አገዛዙ በሕዝቡ ላይ በሚያደርሰው በደልና ግፍ የሚፈጥረው የሕዝብ ምሬትና ቁጣ፣ ከተናጠል ወደ ተደራጀ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ መለወጥ የሚያስከትለው ግፊት እንደሆነ ይታመናል። ከዚህ አንፃር፣ የትግሬ-ወያኔን አገዛዝ ለመጣል ሕዝባችን በተናጠል መታገል የጀመረው ገና ከወያኔ ጽንሰት ጀምሮ ቢሆንም፣ የተቃውሞ እንቅስቃሴው ከግለሰብ ወደ ማኅበረሰብ ለማሸጋገር ጊዜ በመፍጀቱ፣ ኢትዮጵያዊው ዜጋ አምረው በሚጠሉት የፋሽስት ጣሊያን ባንዳ ልጆች፣ የትግሬ-ወያኔ አናሳ ቡድን ለ27 ዓመታት፣ ለያይተውና ከፋፍለው፣ አጥፊና ጠፊ አድርገው አቧድነው፣ የዜግነት መብትና ጥቅሙን አሳጥተው እንዲገዙት ዕድል የሰጠ መሆኑን ያለፈባቸው የመከራ ዓመታት ያሳያሉ።

ያም ሆኖ፣ የግፉ ጽዋ ሞልቶ መፍሰስ በመጀመሩ፣ ሕዝባችን ላለፉት 3 ተከታታይ ዓመታት እንደሕዝብ ከመሃል እስከ ዳር፣ ከከተማ እስከ ገጠር ያለው በአንድ ድምፅ፣ «ወያኔ ይወገድ!»፣«የትግሬ-ወያኔ ዘረኛና ከፋፋይ አገዛዝ ይብቃ!» በማለት ከአፋኙና ገዳዩ የአጋዚ ሠራዊት አፈሙዝ ፊት በመቆም የተቃውሞ ድምፁን የሕይዎት ዋጋ እየከፈለ ማሰማቱን በስፋት በመቀጠሉ፣ የአናሳዎቹ ቡድን አገዛዝ እንደድሮው አስፈራርቶና አስገድዶ ለመግዛት ከማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ከሚያወጣቸው መግለጫዎችና በሕዝቡ የተቃውሞ መጠን መሥፋት በግልጽ እየተስተዋለ ነው። ይህም ወያኔ መቼ ይወድቃል? የሚለው የጊዜ ጥያቄ አሁን! ወይም ዛሬ የሚሉ መልሶችን በማያሻማ ሁኔታ እያረጋገጠ እንደሚገኝ አገሪቱና ሕዝቡ የሚገኙበት ነባራዊ ሁኔታ ያሳይል። የአወዳደቁ ሁኔታም በተባበረ ሕዝብ ትግል እንደሆነ በተጨባጭ እየታየ ነው። … (Read more, pdf)