የትግራይ ወያኔ በወልደያ ከተማ በጥምቀት በዓል ላይ በከፈተው ጦርነት 21 ሰዎችን ሲገድል ከ200 በላይ አቆሰለ

Print Friendly, PDF & Email

(Miky Amhara)

ህወሃት የሚባል የትግራይ ቡድን ገና ሰላም ባስ ላይ ድንጋይ ሊወረወር ይችላልና እንዲሁም ወያኔ ሌባ የሚል ጭፈራ ሊጨፈር ይችላል ብሎ ከባለፈዉ ሁለት ሳምንት ጀምሮ ከ 2500 በላይ አማራኛ የማይችሉ አጋዚዎች መቀሌ አካባቢ ከሚገኘዉ ካምፕ ወልድያና አካባቢዋ አምጥቶ ሲደፋ ሰንብቷል፡፡ እኒህ ወታደሮች ሞራል የሌላቸዉ አማራኛ ሲወራ ሲሰሙ የሚያቅለሸልሻቸዉ ትናንት ከሰአት በጅምላ ታቦት ወደሚሸኘዉ ህዝብ በመተኮስ እስካሁን በለሊቱ ብቻ ተቆጥረዉ የታወቁ 21 ሰወች የሞቱ ሲሆን፡፡ ከ 200 በላይ ቁስለኛ በሆስፒታሉና በክሊኒኮች ህክምና እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ ብአዴን የሚባል አተላ ደግሞ በቂ የክልሉ ፖሊስ እያለ ግማሽ አማራን (ምስራቅ አማራን) ጸጥታዉንም ፖለቲካዊ አስተዳደሩንም በስምምነት ለህወሃት አስረክቦ እሱ ባህረዳር እና ጎንደር ላይ ይተራመሳል፡፡ የህወሃት ወታደር ላደረሰዉ ጭፍጨፋ ብአዴን ቀንደኛ ተዋናይ ነዉ፡፡ እንዴት የሚያስተዳድረዉን ክልል ግማሹን በአደራነት ለህወሃት ይሰጣል፡፡ ህወሃት እኮ ዉስጡ በአምሮ በሽተኛ የተሞላ ፤ማመዛዘን የማይችሉ፤ የአእምሮ በሽታቸዉ እረፍት የሚያገኝላቸዉ ጅምላ ግድያ በማካሄድ ነዉ፡፡ ህወሃትን እንዴት አምኖ ሰዉ ጥሎ ይሄዳል፡፡ የአእምሮ በሽተኞች እኮ የቅርብ ክትትል ያስፈልጋቸዋል፡፡

ወያኔ ትግሬ የክልሉ ህዝብ ከሶስት አመት የኢኮኖሚ ድቀትና የፖለቲካ አለመረጋጋት በኋላ ንግዱና ከተሞች በትንሹም ቢሆን ጥምቀትን አስታከዉ መነቃቃት ሲታይባቸዉ ይሄዉ ህዝብ በጅምላ በመግደል እንደገና የክልሉን ህዝብ ማቅ አልብሶታል፡፡ ቱሪዝምና ኢንቨስትመንት ወደ ክልሉ ዝር እንዳይል በየጊዜዉ እየጠበቀ የክልሉን ሰላም ያደፈርሳል፤ ለፈረንጆች ክልሉ ጸጥታ የሌለዉ አድርጎ በመሳል የቱሪዝም እንቅስቃሴዉን በማዳከም ወደራሱ ክልል ሁሉንም ነገር ማዞር ይፈልጋል፡፡ ከዛም በላይ የአማራ ህዝብ እጅግ የሚመካበትን በህላዊና ሃይማኖታዊዉን የጥምቀት በአል በጥቁር መዝገብ እንዲያየዉ በየአመቱ ሰዉ ይገልበታል፡፡ አምና በዚህ ሰአት ጭልጋ ላይ 5 ሰወችንና 2 ታቦት የተሸከሙ ቄሶችን አጋዚ ተኩሶ መግደሉ እናስታዉሳለን፡፡ ከሁሉም በላይ ግን የአማራ ደም የሚያሰክረዉ ህወሃት አጸፋዊ እርምጃ ካልተሰጠዉ ቀጣይም ሌላ የጅምላ ግድያ ያካሂዳል፡፡

የአማራ ህዝብ እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝብ ይሄን የጅምላ ግድያ በነቂስ ሊያወግዘዉ ይገባል፡፡ ለትግሬ ደህንነቶችና ወታደሮች የምግብና ሌሎች አገልግሎቶች እንዲሁም መረጃ ሲሰጡ የነበሩ ሰወችና ቢዝነስ ሴንተርስ በከፊል ደርሰዉናል፡፡ አስፈላጊዉን ማጣሪያ ካደረግን በኋላ ይፋ እናደርጋቸዋልን፡፡ የማያዳግም እርምጃ ይወሰዳል፡፡