የኢትዮጵያ የሽግግር ጊዜ መተዳደሪያ ደንብ! – ከትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ውድቀት በኋላ ወዴት? (በዐኅኢአድ የተዘጋጀ)

Print Friendly, PDF & Email

የኢትዮጵያ የሽግግር ጊዜ መተዳደሪያ ደንብ! – ከትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ውድቀት በኋላ ወዴት?

የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (ዐኅኢአድ) ጥር ፯ ቀን ፪ሺ፲ ዓ.ም

የኢትዮጵያ የሽግግር ጊዜ መተዳደሪያ ደንብ!

የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (ዐኅኢአድ) ጥር ፯ ቀን ፪ሺ፲ ዓ.ም

መግቢያ:-

ኢትዮጵያ ሀገራችን ከሩቅ ታሪክ ከመጡ ጥቂት የዓለማችን ሀገራት አንዷ ናት። በጥንቱ ዘመን የነበረ ተጓዥ፣ አቅጣጫውን እንደሚያመላክትበት የሰሜን ኮከብ ሁሉ፣ ኢትዮጵያም በዚያ ሩቅ ዘመን የሰው ልጅ በተፈጥሮ ተጽዕኖ ከፍተኛ ቁጥጥር ሥር በነበረበት ዘመን ውስጥ፣ ስታበራ የኖረች ሀገር ናት። ኢትዮጵያን ከሁሉም ሀገራት ልዩ የሚያደርጋት ደግሞ በአንድ ትልቅ፣ደግሞ በተለያዩ የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች ቁጥጥር ሥር ወድቆ የእርሱነቱ መገለጫ የሆኑ ዕሴቶቹን በተነጠቀ አህጉር ዉስጥ ብቻዋን የራሷን ታሪክ ስትሠራ የመጣች፣ ከሷ የተጎራበተና ሥልጣኔውን የሚያቋድሳት ሀገር እምብዛም በሆነበት ሁኔታ ውስጥ፣ የራሷ የሆነ ድንቅና ልዩ ሕዝባዊ ትሥሥርን ስትፈጥር የመጣችና የራሷን ነፃነት ጠብቃ ዛሬ ለደረሰችበት የዕድገት ደረጃ የበቃች ሀገር ናት። ዛሬ በዉስጧ የተገነቡ የመንግሥት ተቋማት፣ ከተማዎች፣ የኢንዱስትሪ፣ የባህል፣ የሃይማኖት፣ የትምህርት ተቋማትና የመገናኛ አውታሮች በሕዝቧ የጋራ ጥረት የተገኙ በመሆናቸው አንድ ኢትዮጵያዊነት ዜጋ ማንነትን ሊፈጥሩ የቻሉ ናቸው። ከዚህ በተቃራኒው በመላው ዓለም ላይ የተገኙ ሥልጣኔዎች፣ ከሞላ ጎደል የተመሠረቱት የሰው ልጅ ዕድገቶች ባስመዘገቡት ውጤት አንዱ ከሌላው ጎረቤቱ ባጋኘው የቴክኖሎጂ ማጋባት ሆኖ እናገኘዋለን።

ኢትዮጵያ ረጅሙን የታሪክ ጉዞዋን አብዛኛውን ያሳለፈችው፣በማኅበረሰብ ዕድገት ታሪክ ውስጥ የፊዉዳል ሥልተ- ምርት በተሰኘው የመሆኑ ምስጢርም፣ ይህ ራሷን ከወረራ የመከላከልና ድንበሯን አጥራ የመቆየቷ የብቸኝነት ታሪኳና ለነፃነቷ ስትል የከፈለችው ተከታታይና ያላቋረጠ ኅልውና እና ማንነትን የማስጠበቅ ተጋድሎ ውጤት ነው። ለኋላ ቀርነቷ መሠረታዊ ምክንያቱም ይህ ነው። በነዚህ ምክንያቶች የማዕከላዊ መንግሥት አመሠራረት ጥረት ረጅምና ደም አፋሳሽ ሆኖ በመዝለቅ፣ እስከ 20ኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ ሊደርስ እንደቻለ በግልጽ ይታያል። እርግጥ ነዉ፣ ኢትዮጵያ በዚያ ጥንት ዘመን እጅግ በጣም በሚገርም ሁኔታ የራሷ የሆነ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ለመመሥረት የቻለች እንደነበረች፣ በዐፄ ይኩኖአምላክ ሥረወ-መንግሥት በ13ተኛዉ ክፍለ ዘመን ተጀምሮ፣ የመንግሥት አስተዳደር፣ የሃይማኖት፣ አመራርና የሕዝብ ግንኙነት ምን መልክ እንደነበረው «ክብረ መንግሥትና ፍትሓ-ነገሥት» የተሰኙት ሰነዶች ቋሚ ማስረጃዎች ናቸው። በኋላም በዐፄ ሚናስና ዐፄ ሠርጸድንግል ሥረወ- መንግሥት ጊዜ በወቅቱ እጅግ በጣም ዘመናዊ የሚባል የማዕከላዊ መንግሥት ምሥረታ ቀመሮች ከዘመን ዘመን ተሻጋሪ ጅምሮች ነበሩ:: ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች፣ “የመጀመሪያዉ የኋለኛ ሆነ” እንዲሉ ኢትዮጵያ ሀገራችን በተለያዩ የዉጭ ተስፋፊዎችና ቅኝ ገዥዎች እንዲሁም የእርስ በእርስ የዉስጥ ፍትጊያዎች የተነሳ፣ በታሰበዉ መልካም ጅምር ተረጋግቶ በብልጽግና መዝለቅ እንዳልተቻለ ሀገራችንና ሕዝባችን የሚገኙበት ሁኔታ በግልጽ ያሳያል:: … (Read more, pdf) ( የዐኅኢአድ የሽግግር ጊዜ ሰንድ ጥር 3 ቀን 2010 ዓ.ም ) || (የዐኅኢአድ የሽግግር ጊዜ ሰነድ መሸኛ ጥር 3 ቀን 2010 ዓ.ም)