“ብሔሮች ተገንጥለው የራሳቸው ነፃ መንግሥት እስከ ማቋቋም ማስተማርና መተታገል አለብን” – የኢሕአፓ መጋቢት 1976 ዓ.ም ፕሮግራም

Print Friendly, PDF & Email

ኢሕአፓ መጋቢት 1976/ዓ.ም ፕሮግራሙ “ብሔሮች ተገንጥለው የራሳቸው ነፃ መንግሥት እስከ ማቋቋም ማስተማርና መተታገል አለብን ብሏል”

ለኢሕአፓ መልስ “ክፍል 3”

ጌታቸው ረዳ ዘብሔረ አክሱም (ኢትዮ ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)

ከላይ የሚታዩት ተዋጊዎች ‘ጀብሃ’ የተባለው የሽምቅ ተዋጊ ሰልጣኞች ሲሆኑ “ዔን ኣልሳሕብ” በተባለ የፍልስጢኤም ማሰልጠኛ ጣቢያ ከዓረብ አስልጣኞቻቸው የተነሱት ፎቶግራፍ ሲሆን፤አሰልጣኞቹ ኢህአፓዎችንም ጭምር በዚህ መልክ አሰልጥነው “ዓረባዊ አጀንዳን” እውን ላመድረግ ወደ ኤርትራ እንዲሻገሩ በይሩት ድረስ ሄደው ሳላሕ ሳበን ተማጽነውት ነበር። የኤርትራን ነፃነት እውን እንዲሆን ታግለናል የሚለውን ፕሮግራማቸው እንመለከታለን።

 

ኢሕአፓ የሚባል ነገር እያደር የሚገርም ነገር እየያዘ ብቅ ሲል ይብልጥ የዚህ ድርጅት ምንነት ለማወቅ ፍላጎት እያደረብኝ መጥቷል። ችግሩ ግን ቀልባችን ወደ ወያኔ እንዳናደርግ በትርኪ ምርኪ ውሸት ተጠምዶ እኛንም ወደ ንትርኩ እየሳበ፤ ሕዝብ እንዳናስተምር፤ ‘እቤት እንደዋለች አሮጊት ባልቴት’ በየፓልቶኩ እየገባ ኢሕአፓ ስለ አንድነትና ሉዓላዊነት ክብር የተዋደቀ “ዓባይ ኢትዮጵያ’ የሚል ስም በወየኔ (በነገራችን ላይ ኤርትራኖች ናቸው ይህንን ቃል ለኢሕአፓ ያወጡት)

የተሰጠኝ……እያለ አስቂኝ የሆነ ከንቱ ውዳሴ በድረገጹም ድርጅቱ እራሱ ያጸደቀው የራሱን ፕሮግራም ሲክድ፤እራሱን ሲያመጻድቅ ማየት ‘ጉደኛ’ ድርጅት ነው ያስብላል። ዛሬ ደግሞ መገንጠልን ደግፌ አለውቅም የተጨቆኑ ብሔር እና ብሔረሰቦች ስለነበሩ ”ራስን በራስ እስከ መገንጠል… ወዘተ..” መፍትሄ ነው ብለን አስተምረናል እያለ ፕሮግራሙ እየነገረን፤ “እስከ መገንጠልን” አላስተማርኩም ሲል ለመሸሽ ይሞክራል።

ኢሕአፓ ‘ለኔ’ መልስ ይሆናል ብሎ በራሱ “ካልቶች” የሚዘወር አሲምባ በተባለ ድረገጽ አዘጋጅ በብዕር ስም “አቶ ሰውየው” የተባለ ግለሰብ ለኔ መልስ ይሆናል ብሎ የመኖጫጨረው የላብ አደር ኮሚኒሰት አስተዳደር አስተዋዋቂ የነበረው “ያ ትውልድ” በመባል የሚታወቀው የኢሕአፓው ቅርንጫፍ “ማን ይናገር የነበረ” ሲል በጻፈው የድርጅቱ መልስ (ምናልባትም በኢያሱ አለማዮሕ መሪነት የተጻፈ) ኢሕአፓ እንደ ወያኔ “መገንጠልን” በፕሮግራሙ አቀንቅኖ አያውቅም ሲል “ ይህኑን” ዓይኑን በጨው አጥቦ እንደገና ለሁተኛ ጊዜ ሲዋሽ ማየት ይህ ድርጅት እውነትም መታከም የሚያስፈልገው “የበወዘ በሽተኛ” ድርጅት ነው። …. ( Read more, pdf)