የህወሃት ዓላማ መንግስታዊ ካፒታሊዝም በትግራይ እና ብልሹ ካፒታሊዝም በተቀረው ኢትዮጵያ ነው

Print Friendly, PDF & Email

(ከአማራና ኦሮሞ ትብብር ይለምልም ፕሮጀክት – አኦትይፕ)

የህወሃት የቅርብና የሩቅ ዓላማ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በበላይነትና በሰፊው በመቆጣጠር ለትግራይ ያደላ የካፒታሊስት ሥርዓት በመፍጠር እስከተቻለ ድረስ በበላይነት አብሮ ለመኖር ካልሆነም ኢትዮጵያን አደህይቶ፣ አዳክሞ ወይንም አድቅቆ ለመለየት ነው። ለዚህም ዓላማው ማስፈፀሚ አንደኛው ዋና መንገድ መንግስታዊ ካፒታሊዝም በትግራይ እና ክሮኒ ካፒታሊዝም ወይም ብልሹ ካፒታሊዝም በተቀረው በኢትዮጵያ መመስረት ነው። በትግራይ ክልል ላይ እየተገበረ ያለው የመንግስታዊ ካፒታሊዝም አካሄድ የቻይናን አካሄድ የሚመስል ሲሆን፤ ዓላማው አብዛኛው የክልሉን ሕዝብ የልማቱ ተጠቃሚ በማድረግ ክልሉን የመሀከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ለማሰለፍ የታለመ ነው። በተቀረው ኢትዮጵያ እየተገበረ ያለው የክሮኒ ወይም ብልሹ ካፒታሊዝም አካሄድ ዓላማው ለዘረፋና ለምዝበራ አመቺ የሆነ የኢኮኖሚ ሥርዓት በተቀረው ኢትዮጵያ በመዘርጋት የወያኔ ድርጅቶችና ግለሰቦች በሕገ ወጥ መንገድ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በበላይነት በመቆጣጠር የትግራይ ክልልን የልማት ጉዞ የሚያግዝ ካፒታል እንደ ድርጅትም፤ እንደ ቡድንም፣ እንደ ግለሰብም ማግበስበስ ነው። ይህ እንግዲ ወያኔዎች የሚያመልኩት የመለስ ዜናዊ እኩይ አእምሮ የነደፈው የዘረፋ ራዕይና ዕቅድ ነው።

የመለስ ዜናዊ ቡድንና አንዳንድ የትግራይ የፓለቲካ ልዒቃን አለመግባባት የተፈጠረው የዚህ ዕቅድና ራዕይ የአተገባበር ዘዴና ይህ ፕላን ኤርትራዊያንን ይጨምር ወይስ አይጨምር በሚለው ነው። የመለስ ዜናዊ ቡድን ፍላጎትና ድሮም እንደሚያምኑበት የትግራይ የረዥም ጊዜ ግብ ከኤርትራ ጋር የተቆራኘ መሆኑን ነበር። እንደ መለስ ቡድን አስተሳሰብ ትግራይ በኤርትራ ተቀባይነት ሊኖራት የሚችለው የትግራይ ኢኮኖሚ ወደ መሀከለኛ ገቢ ደረጃ ሲደርስ ብቻ ነው። ደሀ ትግራይ ኤርትራን አታጓጓም። እንደ መለስ ዜናዊ ትንታኔ የትግራይ ዋናው ችግር ድህነት ነው። በተቀረው ኢትዮጵያ ያለው ዋናው ችግር ግን የድህነት ሳይሆን የአስተዳደር ጉዳይ ነው። ስለዚህ ትግራይን ከድህነት አውጥቶ ወደ መሀከለኛ ገቢ ለማድረግ በኢትዮጵያ የተበላሸ አስተዳደር በማስፋፋት ያለውን ሀብት በሰፊውና በፍጥነት መበዝበዝ ነው። በተቀረው ኢትዮጵያ ያለው ብልሹ አስተዳደር በህወሃት ሆን ተብሎ የሚተገበርና የሚፈለግ ነው። በስፋትና በጥልቀት ለመዝረፍ በተቀረው ኢትዮጵያ ውስጥ ለዘረፋ አመቺ ሆኔታዎችን መፍጠር ያስፈልጋል። በህወሃት ትንታኔ በትግራይ ያለው ልማት በተቀረው ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚደረገው ዝርፍያ ጋር መርእ ያለው ቁርኝት አለው። ትግራይን ለማልማት ካስፈለገ የተቀረው ኢትዮጵያን መዝረፍ ያስፈልጋል። ህወሃት የሚሰራው ለትግራይ ነው በዚህ ላይ ብዥታ ያለበት ሰው ካለ እውነታውን ለማየት ያልቻለ፣ የማይፈልግ ወይም አውቆ የሚክድ ሰው ነው። በግለሰብ ደረጃም ቢሆን የትግራይ ተወላጆችን በተቀረው ኢትዮጵያ ውስጥ በአድሎና በዘረፋ ሀብታም እንዲሆኑ ማድረግ ህወሃት ትግራይን ወደ መካከለኛ ገቢ ለማድረስ የሚያስፈልገውን ሀብት ለመዝረፍ የሚጠቀምበት አንዱ መንገድ ነው። ዘረፋው የሚካሄደው እንደ መንግስትም፣ እነድ ድርጅትም፣ እንደ ቡድንም፣ እንደ ግለሰብም ነው። እንደ መለስ ዜናዊ እምነት ከድህነት ለመውጣት ከዚህም ከዛም የሚገኘውን ጥቅም በማንኛውም መልኩ በፍጥነት መለቃቀም ያስፈልጋል። የመለስ ዜናዊ ራእይ ትግራይን በኢኮኖሚም ሆነ በወታደራዊ አቅም እንደ እስራኤል ማድረግ ነው ለዚህም የትግራይ ምሁራኖችን ከፍተኛ ትብብር እንዲያደርጉ በግልፅ ይማፀን ነበር። ለዚህም ይመስላል አብዛኛው የትግራይ ምሁራኖች የህወሃት ደጋፊ የሆኑት።  ….  (Read more, pdf)