የታሪክ ሽሚያ! ታጥቦ ጭቃ! – መቅደላ የዐኅኢአ ድ ልሳን

Print Friendly, PDF & Email

ዘመናዊው የፖለቲካ ትውልድ ብለን ልንጠራው የምንችለው የኛው ትውልድ፣ የፖለቲካ ዕድሜው ከ60 ዓመታት አያልፍም። ከተግባራዊ እርምጃው ዘንድ እንነሳ ካልን ደግሞ ፣ በእርግጠኝነት ከታህሳስ 1953 ዓም በትውልዱ የተወሰደው የመፈንቅለ ንግሥና እርምጃው ዘንድ ይጀምራል። በብዙው የትውልዱ ምሑራን ዘንድ የወታደሩን ክፍል እንቅስቃሴ የትውልዱ አካል አድርጎ ያለመመልከት አባዜ እንዳለ እግረመንገዳችንንም መጥቀስ ተገቢ ይሆናል።

ይህ የኛው የፖለቲካ ትውልድ ፣ ከበስተኋላው የነበር ቅርሱ የሚያወላዳ አለመሆን፣ ለዛሬው አካሄዳችን ዛሬም ከፍተኛውን ሚና ሲጫወት እንመለከታለን። ከየት ጀመረ የሚለውን ለመዳሰስ ትንሽ ወደኋላ መመልከት የግድ ይላል። ከኛ በስተኋላ የነበረውን ጠመዝማዛውን ታሪክ ስንመለከት እኛን ወደፊት የሚገፋ አልነበርም። የመዘመን ትግሉ የተጀመረው ከዐደዋ ድል በኋላ ወዴት ነው አቅጣጫችን ከሚለው ጥያቄ ተነሳ። ለዚህ ሀሳብ መነሳት ያደረሰው የውጭ ወረራ ሥጋትና የኤርትራ በአቅኚው እጅ መቆየት ፣ ለእንደገና ጦርነት አይቀሬነት ፍንትው ብሎ መታየት ነበር። በዚህ ምን ይድረግ? ዙሪያ ሁለት ክርክሮች ተነሱ። አንዱ በንጉሠ ነገሥቱ አመለካከት ዙሪያ በቆሙ ተራማጅ አሳቢዎችና በሌላው ጎን በእቴጌይቱና በቤተክህነት ዙሪያ በቆሙት መሀል የተንጸባረቀው ልዩነት ነበር። በንጉሡ አመለካከት የነበረው አስተሳሰብ ኢትዮጵያ ቶሎ ካልዘመነች በሥልጣኔ እየታገዘ የሚመጣውን የአቅኚዎችን በትር መቋቋም አይቻልም የሚል ነበር። በተቃራኒው በእቴጌቱ፣ በቤተክህነትና ባላባቶች በኩል የተያዘው አቋም፣ የውጪ ኃይል ዋና የመግቢያ በር ፣ከውጪ የሚገባ ሥልጣኔ ይዞት የሚመጣው መዘዝ ነው የሚል ነበር። ይህ ትግል ለትውልድ አልፎ በተከተለው ትውልድ በአልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንንና በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱና በደጋፊዎቻቸው መሀል ተመሳሳይ ትግል ተካሂዶበታል። …..  (Read more, pdf)