የሰሞኑ ዜናዎች ትግራይ Vs አማራ

Print Friendly, PDF & Email

የሰሞኑ ዜናዎች ትግራይ Vs አማራ

(Miky Amhara)

ትግራይ
————–
1. የእንግሊዙ ኢንትሬድ ኩባንያ በመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ዘርፍ ሊሰማራ ነው (ታህሳስ 30፣2010 ፋና)

2. መሰቦ ሲሚንቶ የ70 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈራረመ (ታኅሳስ 29-2010 ሪፖርተር)

3. ኤፈርት በ745 ሚሊየን ብር ያስገነባው የመሊ የወርቅ ማምረቻ ፋብሪካ ወደ መደበኛ ምርት ገባ (ታህሳስ 24፣ 2010 ፋና)

4. በ75 ሚሊየን ብር በአዲስ መልክ የተገነባው የአፄ ዮሃንስ አራተኛ መሰናዶ ትምህርት ቤት ተመረቀ (ታህሳስ 20፣ 2009 ፋና)

5. የአድዋ ፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ምስረታ ሃገር አቀፍ ጉባኤ የፊታችን ሰኞ በአዲስ አበባ ይጀመራል። (ጥር 2፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ)

6. በአማራ እና ትግራይ ክልሎች በተያዘው ዓመት በጥናት በተለዩ 45 ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ላይ የከርሰ ምድር ውሃ መገኛ አከባቢያዊ ካርታ ሊዘጋጅ መሆኑን የእርሻ እና ተፈጥሮ ሃብት ሚኒስቴር አስታወቀ። (ጥር 1፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ)

7. ሽሬ አካባቢ ከ 3 ሽህ አመት በፊት የነበረ ከተማ በቁፋሮ ተገኘ (ፋና)

አማራ
————–
1. በባህር ዳር ፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል የወሊድ አገልግሎት ለማግኘት ብንመጣም በአልጋ እጥረት እየተቸገርን ነው፡፡እናት ወልዳ አስፓልት ላይ ከእነ ህጻኗ እንድትተኛ ይደረጋል:: (ጥር 02 /2010 ዓ/ም(አብመድ)

2. በከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል የህክምና መሳሪያና የባለሙያዎች እጥረት በመኖሩ በቂ አገልግሎት እያገኘን አይደለም- ተገልጋዮች (ታህሳስ 24፣ 2010 አብመድ)

3. በደብረታቦር ከተማ የሚገነቡት መንገዶች ጥራት የላቸዉም፡፡ በተገነቡ በሳምንቱ ይፈራርሳሉ (ጥር 02 /2010 ዓ/ም(አብመድ)

4. በማእከላዊ ጎንደር ዞን ጣቁሳ ወረዳ ከ68 ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ የብር ኖቶች መያዛቸዉን የወረዳዉ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል ፡፡(ታህሳስ 24 /2010 አብመድ)

5. በማዕከላዊ ጐንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ በሚገኙ ት/ቤቶች ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ የተገጠሙ ፕላዝማዎች እስከ አሁን ለአገልግሎት ክፍት ባለመሆናቸው የመማር ማስተማር ሂደቱ ችግር ገጥሞታል ሲሉ ተማሪዎችና መምህራን ገጸዋል::(ታህሳስ 23/2010 አብመድ)

6. ለድህነት እና ልመና የተዳረግነው መንግስት የላከው እርዳታ በአግባቡ ስለማይደርሰን ነው ሲሉ የዋግ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡(ታህሳስ 23/2010 አብመድ)

7. ለወጣቶች በርካታ የስራ መስኮች መከፈት አለባቸው ሲሉ የከሚሴ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ታህሳስ 21/2010 አብመድ)

8. ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ፡፡በአማራ ክልል ባለፉት ወራት ከ38 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ተችሏል::(ታህሳስ 21/2010 አብመድ) ANRS Communication Affairs Office

9. በጭልጋ ወረዳ በከርሰ ምድር ምርምር ቁፋሮ የተገኙ ታሪካዊ ቅርሶች ጥቅም ላይ ሳይውሉ ለጉዳት ተጋልጠዋል— ጽህፈት ቤቱ፡፡ (ጥር 01 /2010 ዓ/ም(አብመድ) )

10. ደቡብ ወሎ ላይ አንዲት እናት 4 ልጆችን በአንድ ጊዜ ተገላገለች (ታህሳስ 27/2010 ዓ/ም(አብመድ)

11. በባህር ዳር የኢንቨስትመንት ቦታ ወስደው ባላለሙ 171 ባለሃብቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ (ታህሳስ 29፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ)

12. ከበርካታ ሚልዮን ብር በላይ ወጪ ሆነበት የተባለውና ሁለት ጊዜ የተመረቀው የጎንደር የውሃ ፕሮጀክት ስራ ተቋረጠ!! (ኢሳት ዲሲ–ጥር 2/2010)