የ2018 የአመቱ 2 ምርጥ ኢትዮጵያውያን ዮሴፍ ገብሬ (ጆሲ- ኢን ዘ ሃውስ) እና የዙሪክ ስዊዘርላንድ ኢትዮጵያውያን እስፖርት ፌደረሽን

Print Friendly, PDF & Email

የ2018 የአመቱ ሁለት ምርጥ ኢትዮጵያውያን ዮሴፍ ገብሬ (ጆሲ- ኢን ዘ ሃውስ) እና የዙሪክ ስዊዘርላንድ ኢትዮጵያውያን እስፖርት ፌደረሽን

በኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ የተመረጡ (ጌታቸው ረዳ)

ዮሴፍ ገብሬ (ጆሲ) ህመምተኛውና የተቸገረው የኮ/ል መንግሥቱ ኃይለማርያምን ከአገር መውጣት መንግሥታዊ መግለጫን በራዲዮን ያነበበው ታሪክ የማይረሳው እወቁ ጋዜጠኛ ዳርዮስ ሙዲ Journalist Darios

 

Tedros Teklegiorgis ethio zurik swizerlabd sport spokesperson የዙሪክ ስዊዘርላንድ ኢትዮጵያውያን ስፖርት ማሕበር (ፌዴሬሽን) አመራር አባል አንዱ ቴድሮስ ተክለግዮርግስ የፌደሬሽኑ ቃል አቀባይ።

መግቢያ ፡
ይህ ሰነድ ለብዙዎቹ የተቃዋሚ ድረገጾች ልኬአለሁ። አንዳንዶቻችሁ ለምን ይተቸናል ብላችሁ ከዚህ ጸሐፊ ጋር ያላችሁ ለተለመደው የፖለቲካ አለመስማማት ስትሉ “ቂምን እያኘካችሁ” ይህንን ታላቅ ታሪካዊ ስራ ለሕዝብ እንዳይዳረስ በድረገጾቻችሁ ላለማውጣት ስትሉ እንደዘወትሩ ወደ ቆሻሻ መጣያችሁ ብትጥሉት፤ እኔን ሳይሆን የነዚህ አርበኞች ስራ እና ታሪክ እንደጣላችሁ ስለሚቆጠር፤“ወደ ኋሊት” እየተጎተተ ያለው ወገናዊ የሚዲያ አገልግሎታችሁን ወደ ጎን አኑሩትና” ይህንን ሰነድ በድረገጾቻችሁ ብትለጥፉት ብዙ ዜጎችን ስለሚያስተምር እናንተም ከአድሎአዊ ስራ ከመወቀስ ‘ነጻ’ ከማድረግ አልፎ፤ ጋዜጠኝነት የምትሉትን ሞያችሁን ያስመሰግናል እንጂ በታሪክ አያስወቅሳችሁም። ይህ ሰነድ የተላከላቸው ድረገጾች ያወጡት መሆናቸው እና አለመሆናቸው ሕዝቡ እንድያገናዝበው አድራሻቸው ከወደ መጨረሻው ይታያል። አድራሻችሁን ያላገኘሁ ካለሁ፤ ከተለጠፉት ድረገጾች በማግኘት መለጠፍ ትችላላችሁ። …… (Read more)