የአማራ ወጣቶች ንቅናቄ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

Print Friendly, PDF & Email

የአማራ ወጣቶች ንቅናቄ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

ቀን ታሕሳስ 28/2010
የ.መ.ቁ 001/06/2017

ሃገራችን በቀውስ ተወጥራ ሰላምና ጸጥታዋ መስቀለኛ መንገድ ላይ ደርሷል። ወገናችን የአማራው ሕዝብ ከባድ የህልውና አደጋ ተደቅኖበት በእልህ አስጨራሽ ተጋድሎ ላይ ይገኛል። ይህን በሃገራችንና በሕዝባችን ላይ የዘመተውን ፋሽስት የወያኔ ቡድን ከላያችን ተወግዶ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ በሃገር ውስጥ የሚካሄደውን ሁለገብ ትግል ለመርዳትና በተለይም ወጣቱን ትውልድ በነቃና በተደራጀ ሁኔታ በጠላቶቹ ላይ የተቀናጀ ትግል እንዲያደርግ በውጪና በሃገር ውስጥ ያለውን ለማስተባበር የወገን ዋይታና መከራ እንቅልፍ የነሳን ወጣቶች በመሰባሰብ ህልዉናችንን ለማስጠበቅ የአማራ ወጣቶች ንቅናቄን መስርተናል። ንቅናቄያችን የአማራውን ሕዝብ ትግል ለማገዝ ሲነሳ መነሻና መሰረት ያደረገው የአባቶቹን የጀግንነት ባህል ጨዋነትና በጎ ስነምግባርን ትጥቅ አድርጎ በመሆኑ ከማንኛውም ወገን ጋር በወዳጅነትና በመከባበር ላይ የተመሰረተ ግንኙነትና ስልጡን የፖለቲካ ባህልን በመከተል ነው። የአማራ ወጣቶች ንቅናቄ የተቋቋመበት ምክያቶች በርካታ ቢሆኑም ዋናወቹ የሚከተሉት ናቸው።

1. ገዥው መደብ ህወሃት አማራው ላይ እየፈጸመ ያለውን እልቂት ለመከላከል፤ እንዲሁም የአማራውን ውድቀት ለሚምኙ ታሪካዊ ጠላቶቻችንን ለመከላከል እና ህልውናችንን ለማስጠበቅ።

2. በሃገራችን ላይ ባለው ፖለቲካ የጎላ ተሳትፎ በማድረግ አማራውን የሃገራችን ወሳኝ አካል እንዲሆን ተገቢውን ትግል ለማድረግ።

3. አማርኛ ቋንቋ በሰፊዉ የኢትዮጵያ ህዝብ መነገሩ የሚያኮራ ታሪክ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ቋንቋዉን የሚናገሩ አማራ ባልሆኑ ሰወችና ቡድኖች በአማራ ብሄርተኝነት ስም በመደራጀት የአማራ ባህልና ስነ ልቦና በማይፈቅደዉ መልኩ መሰባሰብ ከአማራ ማህበራዊ ማንነቶች ጋር ተፃራሪ በመሆኑ ወጣቱን በአማራ ማንነትና ግብረ ገብነት መገንባትና ለሃገራችን ህልዉና ገንቢ አማራዊ ወጣት መፍጠር ነው።

ንቅናቄችን ከተቋቋመ አጭር ጊዚያት ቢሆነውም በቀላሉ በአማራ ወጣት ልብና ውስጥ ለመግባት ችሏል። በመሆኑም ትግላችንን
በቀጣይነት የበለጠ አይሎ የአማራን ህልውና የሚቋቋም ሃይል እንደሚሆን ተስፋችን ምልዑ ነው። አማራ ከሚታወቅበት የጀግነትና የመንፈሳዊነት ባህሉ ባሻገር ስድብን እጅግ የሚጠየፍና ተሳዳቢን የሚንቅ ብሎም የማያዳግም እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ነው። ለዚህም ነው ሃገራችንን ለመውጋት በተደጋጋሚ የሞከሩትን የቅርብና የሩቅ ጠላቶቻችንን አይቀጡ ቅጣት እየቀጣ መተኪያ የለሽ ሕይወቱን እየሰዋ የተሰለፈው ውርደትን የማይሻ በመሆኑ ነው።

አማራ በሻከረ መዳፉና በጠንካራ ክንዶቹን ጠላቶቹን ሲቀጣ የኖረ ታላቅ ህዝብ የሃገራችን ኢትዮጵያም ባለውለታም ነው። ይህ ሃያል ማህበረሰብ የራሱ ባህል ፥ እሳቤና ስነ-ልቡና ያለው በመሆኑ ስድብንና ጸያፍ ቃላትን የሚጠየፍ አልፎም መሳሪያ የሚያማዝዝ ጉዳይ ነውና ይህን እኩይ መጤ ባህል ይዘው በአማራ ወጣቶች ንቅናቄ ስምና አርማ በመጠቀም በማንኛውም ወገን ጋር የሚካሄድ አላስፈላጊ የቃላት ልውውጥ እንደ ድርጅት የማንቀበለውና ይህን በሚያድርግ አካል ጋር ቆሞ መታየት እንኳ የማንፈልግ መሆኑን ለሁሉም ወገኖች በትህትና ማሳወቅ እንፈልጋለን።

የአማራ ወጣቶች ንቅናቄ የአማራውን ህልውና ተከብሮ፤ የህግ የበላይነት የሰፈነባትና፤ አማራው እኩል ተጠቃሚ የሚያደርግ ስረኣት ለመገንባትና ጠላቶቻችንን በክንዶቻችን ለመመከት አበክረን እንሰራለ። በሃሳብ ጥራትና በመርህ ላይ ለተመሰረተ ውይይት ከማኛውም ወገን ጋር በማንኛውም ግዜና ቦታ ለመነጋገር ወደሗላ አንልም። ለአዋቂዎች ምክርና ተግሣጽ ቦታ የምንሰጥ ፥ ያላወቅንውን ጠይቀን ለመረዳት ሞራል ያለን ወጣቶች ነን። ከፀሐይ በታች የምንፈራው ሃሳብ የሌለ በመሆኑ እንደ አማራ ባህላችን ያልሆነው የስድብ ተግባር ፈጽሞ የምንቀበለው አይደለም። እውነተኛ የአማራ ወገን የሆነም ሁሉ አውቆም ይሁን ሳያውቅ ከዚህ በተቃራኒ ለቆሙት ሁሉ የአበውን ባህልና ወግ ቆም ብለው እንዲይስተውሉት እንመክራለን።

እውነተኛ አማራ አይደልም ተነጋግሮ ተያይቶም ይግባባል!
አያቶቻችን በደማቸው በገነቧት ኢትዮጵያ ሃገራችን ላይ አማራነት ያብባል።
የአማራ ወጣቶች ንቅናቄ

amharayouthmovement@gmail.com