የአክብሮት ምስጋናየ ለኢትዮጵያውያን ማኅበር ጥናትን ምርምር ዘርፍ

Print Friendly, PDF & Email

ጌታቸው ረዳ (የኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ)

የተከበራችሁ ውድ ሊቀ ሊቃውንቶች ወገኖቼ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ጥናትና ምርምር ዘርፍ አባሎች ውድ ገብሬ ጉልቱ ውድ ክብርት እህቴ ወ/ሮ የውብዳር ዘለቀ፤ ውድ ወገኔ ገሞራው ማን ያዘዋል፤ውድ ወገኔ ገለበው ሰንጎጎ ውድ ወገኔ ተከስተ ሐጎስ ውድ ወገኔ አውዴ በዳዳ፤ውድ ወገኔ አዩ ይስማን፤ውድ ወገኔ ኃይለ ልዑል ይርጋ፡ ባላችሁበት ምድር የሰላምና የፍስሃ ልደት እንዲሆንላችሁ እየተመኘሁ፤ ከወዲሁ የቀረን አንድ ቀን ስለሆነ ከነ መላው ቤተሰቦቻችሁ እንኳን ለጌታችን መድሃኒታችን ብርሃነ ልደቱ በዓል አደራሳችሁ እላለሁ። ስለ አደረጋችሁልኝ ድጋፍና ማበረታቻ እጅግ፤በጣም እጅግ ከልቤ አመሰግናለሁ እያልኩ ይህችን ማስታወሻ ለሕዝብ ልኬአለሁ ።

ውድ ሊቀሊቃውንቶች ወገኖቼ ሆይ። ‘ለዑንቁ ደ/ር ጌታቸው ረዳ ዘብሔረ አክሱም’ በሚል የድጋፍና ማበረታቻ ሕዝብ እንዲያውቀው በማድረገችሁ እውነተኛ አገራውያን ዜጎች ከጎኔ መሰለፋቸውን ሳይ ትግሌን ይበልጥ እንድቀጥል አድርጎኛል።

በእያሱ አለማዮህ (ሃማ ቱማ) የሚመሩ ጥቂት የኢሕአፓ አባሎችና ከትግሉ ወጥተናል የሚሉ “የኢሕአፓ-ነበር አባሎች” ድርጅቱን ወይንም መሪዎቻቸውን ስለተቸሁ የሚይዙት የሚጨብጡት በማጣት በኔ ላይም ሆነ በበርካታ ተቺዎች ላይ የስም ማጥፋት እና ዘለፋ በማድረግ ሲረባረቡብኝ አይታችሁ በዜጋዊ እና በፍትሓዊ ሚዛን ተነሳስታችሁ በኔ ጎን ቆማችሁ የስም ማጥፋት ዘለፋቸውን በመመከት በቆምኩበት የዘወትር ኢትዮጵያዊነት መመሪያየ እንድቆም ላበረታታችሁኝ ወገኖቼ እጅግ አመሰግናለሁ።ስለ ኢሕአፓዎች ጉዳይ ትንሽ ልበል፦ ……. (ሙሉውን ለማንበብ ከዚህ በላይ ይጫኑ)