ዐማራን ለማጥፋት የሚጥሩ፣ዐማራ ከመጥፋቱ በፊት ይጠፋሉ! – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

Print Friendly, PDF & Email

ዐማራን ለማጥፋት የሚጥሩ፣ዐማራ ከመጥፋቱ በፊት ይጠፋሉ!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ታህሳስ ፳፫ ቀን ፪ሺህ፲ ዓ.ም. ቅፅ፮፣ ቁጥር ፫

የተለያዩ ፀረ-ኢትዮጵያ አንድነት የሆኑ ሁሉ፣ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ማጥፋት የሚቻለው፣ዐማራውን ቀድሞ በማጥፋ ነው ብለው ያምናሉ። ለዚህ አባባል ዋቢውም፣ የፋሽስቱ ሞሶሎኒን ወረራን በዓይኑ የተመከለተውና በግብር ያየው፣አዶልፍ ፓርለሳክ የተባለው ፀሐፊ የጻፈውና በተጫኔ ጆብሬ መኮንን፣ «የሃበሻ ጀብዱ» ሲል ወደ አማርኛ የተተረጎመው መጽሐፍ በግልጽ ያስረዳናል።

የፋሽስቱ ውልድ እና የባንዳ ልጆች የሆኑት የትግሬ-ወያኔዎችም ኢትዮጵያን ለማጥፋት አቅደው ሲነሱ፣ በአውራ ጠላትነት ፈርጀው ፈጽሞ ለማጥፋት የተነሱት ዐማራውን መሆኑን፣ በ1968ዓም ያወጡት ፕሮግራማቸው ገጽ 18 ላይ የትግራይ ሕዝብ ጠላት ዐማራው እንደሆነ በይፋ አውጀዋል። ሞሶሎኒን ዐማራውን ለማጥፋት ላቀደው ዕቅድ ተግባራዊነት ከ800,000 (ከስምንት መቶ ሺ) በላይ ዐማራን «ጋላ-ሲዳማ» እና «ሐረርጌ» ብሎ ከከለለው ክልል የዘር ማጽዳት ወንጀል መፈጸሙን ታሪክ ቁልጭ አድርጎ ይነግረናል። ከማፈናቀሉ ጎን ለጎንም አያሌ ዐማሮች፣ዐማራ በመሆናቸው ብቻ ከመገደል፣ ከመታሰርና ከመጋዝ የተረፉት ለሥራ አጥነትና ለተዋራጅነት ተዳርገው እንደነበር ታሪካችን በግልጽ ያሳያል።

በተመሳሳይ ሁኔታ፣ የትግሬ-ወያኔ ባለፉት 26 ዓመታት የአገዛዝ ዘመኑ ከአምስት ሚሊዮን ዐማራ በላይ ከኢትዮጵያ ምድረ-ገጽ እንዲጠፋ አድርጓል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዐማሮች፣ ዐማራ በመሆናቸው ብቻ፣ ከመሀል፣ ደቡብ፣ ምሥራቅ፣ ምዕራብና ሰሜን ኢትዮጵያ አገራችሁ አይደለም፤ ውጡ ተብለው፣ ሀብት ንብረታቸውን ተነጥቀው፣ከወራሪና ከጠላት በከፋ ሁኔታ እንዲባረሩ መደረጉን የኢትዮጵያ ሕዝብ በትዝብት፣ ዐማራው በእልክና በቁጭት መመልከቱን እናስታውሳለን። ……  (Read more, pdf)