በትግሬ-ወያኔ የቅንጥብጣቦሽ መደለያ ከተነሳንበት ግብ ሳንደርስ ትግሉን አናቆምም! – ከዐኅኢአድ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ

Print Friendly, PDF & Email

በትግሬ-ወያኔ የቅንጥብጣቦሽ መደለያ ከተነሳንበት ግብ ሳንደርስ ትግሉን አናቆምም!!!

ከዐኅኢአድ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ- ቁጥር ፪/፲ ዓም

በህዝባዊው ያላቋረጠ ትግል መሄጃ አጥቶ ግድግዳ ተጠግቶ ያለ የሰው አውሬ የሆነው ወያኔ የመጨረሻ የግዛት ዕድሜው ውስጥ ገብቷል። በዚህ ባለቀ ሰዓት የኛን ትግል ለማጨናገፍ የማይጥለው ማባበያ፣ የማያደርገው ማደናገሪያ፣ የማይሠራው የማለያያ ሤራና አዳምሮም የማይፈጽመው እልቂት አይኖርም። ይህ ወያኔ ዛሬ ፀሐዩ ጠልቃ ሲመሽበት የነገዋን ፀሐይ ደግሞ ለማየት ሲል የሚያደርገው የቀቢጸ ተስፋ መወራጨት ከሱ በፊት የነበሩት ፋሺሽቶች ሁሉ ያደረጉት ነው። አይቀሬው እውነት ግን የመሸበት ቀን ዳግም እንዳይነጋለት ታሪክ ውሳኔዋን የምትሰጥበት ቀን እጅግ የተቃረበ መሆኑ ነው። እኛም ይህንን በሚገባ እናውቃለን። በመሆኑም በወያኔ የአልጋ ላይ የጣረሞት የማታለያው ጨዋታ የምንደለል አንሆንም።

ይህንን ጨዋታ አስመልክቶ ወያኔ በዛሬው ቀን ቀድሞውኑም መታሰር ያልነበርባቸውን ታጋይ የኢትዮጵያን ልጆች እፈታለሁ በሚል እንደማማለጃ አድሮጎ አቅርቧል። እነዚህ በትግሉ ሜዳ ላይ ከሕዝባቸው የትግል አደባባይ በግንባር ቁመው ሲታገሉ በግፍ የተገደሉና የተሰደዱ ወገኖቻችን ወንድምና እህቶች ናቸው።

እነዚህ የትግሉ ጀግኖች ከተሰዉት ጓዶቻቸው የተለዩ የሚያደርጋቸው በሕይዎት በወያኔ የሰቆቃ እስር ቤት ውስጥ በስቃይ መኖራቸው ብቻ ነው። ወያኔ ሀርነት ትግሬ በነዚ ወገኖቻችን ላይ ኅሊና ሊያስበው የማይፈቅድ ሰቆቃ ፈጽሟል። ….. (Read more, pdf)