የትግሬ-ወያኔ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የወጀውን የጥፋት አዋጅ፣ ሕዝቡ በትግሉ ያከሽፈዋል! – ከዐኅኢአድ የተሰጠ መግለጫ

Print Friendly, PDF & Email


የትግሬ-ወያኔ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የወጀውን የጥፋት አዋጅ፣ ሕዝቡ በትግሉ ያከሽፈዋል! ከዐኅኢአድ የተሰጠ መግለጫ

ቅጽ ፪ ቁጥር ፭ ሰኞ ታህሳስ ፳፫ ቀን ፪ሺ፲ዓ.ም

የትግሬ-ወያኔ፣ በትግራይ ክፍለ-ሀገር የራሱን ትንሽነት ያወጀበትንና በዐድዋ የበላይነት የቋጨውን ስብሰባ ጨርሶ ያወጣው የትንሽነቱ ማረጋገጫ መግለጫ የተጻፈበት ቀለም ሳይደርቅ፣ እንደገና ትንሽነቱን አጉልቶ የሚያሳይ በሕዝባችን ፊት ያወጀበትን የሀገር አቀፍ የጭምብል ስብሰባውን ማጠናቀቁንና በሕዝብ ላይ መጠነ ሠፊ ዕልቂ ለመፈጸም ለ17 ቀን መከርኩበት ያለውን የስብሰባ ማጠቃለያ የጥፋት ማረጋገጫ መግለጫ ይፋ አድርጓል። የትግሬ-ወያኔ የበላይነት ጭንብል የሆነው የአሁኑ የኢሕአዴግ ስብሰባ ውጤት ከመቀሌው የሕወሓት መግለጫ ልዩ የሚያደርገው፣ የትግሬ-ወያኔን መኖር ወይም አለመኖር ሊያረጋግጥ የሚችል የአጥፍቶ መጥፋት የመጨረሻ ዝግጅቱ ማሳያ ሆኖ ሊያሳይ የሚችል መሆኑ ብቻ ነው።

ለትግሬ-ወያኔ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የበላይነቱን አስጠብቆ እንዲቀጥል ፍላጎት ያላቸው ጥቂት የማይባሉ አድር ባይ የሆኑና አንዳንድ የተስፋ ደግ ነገርን ለመስማት የሚጓጉ ቅን ኢትዮጵያውያን፣ ወያኔ ይህን አጋጣሚ ተጠቅሞ ወደ ኅሊናው እንዲመለስ የኅሊና ጸሎት የተማጸኑ እንዳሉ መገመት ይቻላል። አድርባዮቹ ከጸሎት አልፈው፣ ልቡን ለማማለል የሽግግር ሂደቱ አባል መሆን የሚችልበትን መንገድ እንዳመላከቱት ታዝበናል። በተጓዳኝም የሕዝቡን ትግል በመጥለፍ የነሱንም የሥልጣን ቦታን ለማመቻቸት የሚያስችል «የእከከኝ ልከክልህ› ፖለቲካ መሥመር መከተላቸውንም አንዘነጋም።
እነዚህ ሁለት አመለካከቶች የሳቱት ትልቅ ነገር ቢኖር፣ የወያኔ-ትግሬ ከሥረ-መሠረቱ ቢያጥቡት የማይጠራ ዘረ-ባንዳ መሆኑን አለመረዳታቸው ነው። በአገራችን የተቀጣጠለው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ዋናና መሠረታዊ ጥያቄ የባንዳ ልጆች ብቻ ሳይሆን፣ አናሳው ቡድን ሠፊውንና የአርበኞቹን ልጆች በበላይነት ሊገዛ አይገባውም የሚል ነው። ሕዝቡ ያነሳቸው መፍክሮች «የወያኔ የበላይነት ይወገድ!»፣ «አድልዖና ዘረኝነት ይቁሙ!»፣ «አትነጣጥሉን!»፣ ዐማራውና ኦሮሞው ሊነጣጠሉ አይችሉም ወዘተ የሚሉ መሆናቸው ግልጽ ነው። ጥያቄዎቹ፣ አብሮነታችንና አገራዊ አንድነታችን ወደነበሩበት ይመለሱ የሚሉ የማያሻሙና ግልጽ ጥያቄዎች ናቸው። ለእነዚህ ትክክለኛ ሕዝባዊ ጥያቄዎች የወያኔውን ጭምብል ኢሕአዴግ የሰጠው መልስ ፣የችግሮቹ ሁሉ ቋጠሮ የሆነው በልዩነት ላይ የተመሠረተው የፌደላዊ አስተዳደር፣ በአገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ፣ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ሕይዎት ውስጥ የትግሬ የበላይነት ሠፍቶና ዳብሮ ይቀጥል፣ ይህን በሚቃወሙት ላይ የመከላከያውና የፀጥታው ኃይል የአፈናና የግድያ ተግባሩ አጠናክሮ እንዲቀጥል የአጥፍቶ መጥፋት ተልዕኮውን እንዲወጣ ቀጭን ትዕዛዝ የሰጠበት ነው። ባንድ ቃል መልሱ፣ ኢሕአዴግ የቆመበት የዘር ሥርዓት ትክክልና የማይነቃነቅ ነው የሚልነው። የተፈጠሩት ችግሮችም በሥርዓቱ ፈጣን ዕድገት የተነሳ የተፈጠሩ በመሆኑ፣ ችግሮቹ የሚጠበቁ እና የማይታለፉ የዕድገት ችግሮች ናቸው፤ እነዚህንም ችግሮች እንዳለፉት ሁሉ ታግየ የማሸንፋቸው ናቸው የሚል ነው።

ለትግሬ-ወያኔ ዘረፋ ፣ ሙሰኝነት፣ ግድያ፣ የዘር ምንጠራ፣ የመሬት ቅርምትና የዘር ፍጅት፣ የትግሬ ነገድ የሀገሪቱን ሥልጣንና ሀብት ጠቅልሎ መያዝ የሚባሉት ድርጊቶች የአገሪቱ ችግሮች እንዳልሆኑና በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ የተፈጸሙ ወንጀሎች እንዳልሆኑ፣ሆነው ቢገኙም በይቅርታ የሚታለፉ እንደሆኑ በመቁጠር፣ የሕዝቡን መሠረታዊ የለውጥ ጥያቄዎች አጣጥሎታል። በኢሕአዴግ ውስጥም የወያኔ የበላይነት የለም፤ የተዘረጋው የፌደራል ሥርዓት ለዚህ ዓይነቱ የበላይነት ቦታ አይሰጥም በማለት ተጨፈኑ ላሞኛችሁ ሲል ተደምጧል። ይልቁንም ይህ ኢሕአዴግ ተብየው መግለጫ፣ የተከሰቱት ችግሮች ሁሉም፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመሆናቸው፣ በድርጅቱ ታርመው፣ የትግሬ-ወያኔን በሁሉም ዘርፎች የበላይነት አስጠብቆ በሁሉም ነገሮች እንደቀድሞው እንዲቀጥሉ፣ ለዚህ አሻፈረኝ ያሉ ኃይሎችና ቡድኖች፣ «በሕዝበኛነት፣ እና በመርሕ አልባ ግንኙነት» ስም ተጠልፈው እንዲቀጡ ለማድረግ አልሞ የተነሳ እንደሆነ መግለጫው በግልጽ ያስረዳል። ….. (Read more, pdf)