ንግሥት ዘውዲቱ፤ ልዕልት መነን እና ቀ/ ሃ/ሥላሴ የሰው ጉበት ይበሉ ነበር? ክፍል -2- መልስ ለኢሕአፓ

Print Friendly, PDF & Email

ጌታቸው ረዳ ኢትዮ ሰማይ

ለኢሕአፓዎች ‘ክፍል 2’ መልስ ለመመለስ አልፈለግኩም ነበር። ሆኖም ዛሬ ቀን አንድ የስድብ ኢመይል ደርሶኛል። ከስቶክሆልም ከሚተላለፈው ከኢትዮጵያ አንድነት ራዲዮ ጣቢያ ጋር ያደረግኩትን ቃለ መጠይቅ አስመልክቶ ከአንድ ሰው/ ወይንም ከአንዲት ሴት ያገኘሁት መልእክት እንዲህ ይላል።

እኛን “ኢሕአፓን” አትልከፈን፤ ኢሕአፓዎች ለከፍካቸው እውነታቸውን ነው። በባህላችን ሰውን የሰው ሥጋ በልቶ አያውቅም፤ ተደርጎም ተሰምቶም አያውቅም፤ ኢትዮጵያዊ የሆነ ዜጋም እንዲህ ያለ ዜና ወይንም ጽሑፍ የጻፈ ዜጋ ተሰምቶም አይታወቅም፤ አንተ እና መሰል ‘አማራዎች ነን ባዮች’ ናችሁ ከባህላችን ውጭ ሕዝባችንን ለማዋረድ “አማራዎች በሰው ታርደው ተበሉ” የምትሉ “ሃሰተኞች” ብሎ በአምስት ዘለላ መስመር የተሞላ የስድብ ናዳ ሲያወርድብኝ፡ ልተወው ያሰብኩትን ትችቴ መቀጠል እንደለብኝና እራሴንም በማስረጃ መደገፍ ስላለብኝ ይህንን ሰነድ ለንባብ ይኼው።

የኢሕአፓ ተከታዮች የሚከተሉትን ድርጅት ምንነት እንውቀዋለን ሲሉ ይደመጣሉ። ካወቁት ችግር የለኝም። ግን ኢሕአፓን አትንካ፤ዋለልኝን አትንካ ካለዚያ…ካለዚያ…..የሚል ዛቻ እያስፈራሩን ከናታችን ሆድ ገብተን እንድንደበቅ ይወዉቱናል። ዛሬም ከስድባቸው እና ውንጀላቸው ነፃ ቢያወጡኝ በማስረጃ አስደግፌ ላሳስባቸው እና እኔን ከስድባችሁ እባካችሁ ነጻ ልቀቁኝ እያልኩ ይህንን የሚሞላቀቀው ብዕራችሁን እንድትፈትሹት ይህንን ሰነድ እነሆ መርምሩት።

ሁላችሁም አንባቢዎቼ እንደምታውቁኝ ያለ አንዳች ማስረጃ ሰውን/ድርጅትን አልነካም። ሲነኩኝ ግን በማስረጃ አስደግፌ መልስ መስጠቴን ይታወቃል። ስለሆነም ኢሕአፓዎች ከጌታቸው ረዳ ጋር መላከፍ የባሰውኑ ማንነታችሁን ስለሚያጋልጥ ይህንን የእምየ ኢትዮጵያ ልጅ ጌታቸው ረዳን ለቀቅ ማድረግ ይመረጣል! ሲሉ ብዙ ወገኖች መክረዋችሗል። ግን ትዕቢት መከራ ነው። ስለሆነም እየተማማርን እንጓዝ። …. (Read more, pdf)