የወሎ ኦፓልና የአለም ባንክ ሪፖርት

Print Friendly, PDF & Email

(By Miky Amhara)

በአማራ ምድር በወገልጠና/ደላንታ አካባቢ ስለሚገኘዉ የኦፓል ምርትና የህወሃት ደላሎች ዘረፋ አንስተን ነበር፡፡ ስለ ኦፓል ወሎ ድረስ በመሄድ የአለም ባንክ ያጠናቀረዉን ጥናትና የዚህ የከበረ ማእድን ሚሊየኖችን የሚቀይር ሃብት ቢሆንም ህገወጥ በሆነ መንገድ ስለሚደረገዉ የንግድ እንቅስቃሴና የአካባቢዉ ሰወች ምንም እንዳልተጠቀሙ ያትታል፡፡

በአማራ ክልል በወሎ ውስጥ የሚመረተው የኦፓል ምርት

ኦፓል መጀመሪያ የተገኘዉ በሽዋ አካባቢ በ 1990ወቹ ነዉ፡፡ ነገር ግን በዚህ አካባቢ የተገኘዉ ኦፓል ጥሩ ኳሊቲ ያለዉ ሆኖ አልተገኘም፡፡ እንደገና በፈረንጆች አቆጣጠር በ 2008 አካባቢ በሰሜን ወሎ ደላንታ አካባቢ ከፍተኛ የኦፓል ክምችት ተገኘ፡፡ በአለም በጥራት የሚታወቀዉ የአዉስትራሊያ ኦፓል ሲሆን ወሎ የተገኘዉ ኦፓል ከአዉስትራሊያዉ እጅግ የላቀ ሁኖ ስለተገኘ በአለም ገቢያ ተቀባይነቱ ከፍተኛ ሆነ፡፡ የኢትዮጵያ ኦፓል በስፋት ከሚላክባቸዉ አገሮች ዉስጥ አሜሪካ፤ቻይናና ህንድ ይገኙበታል፡፡

የአለም ባንክ ሪፖርት እንደሚያሳየዉ በደላንታ አካባቢ ወጣቶች ተደራጅተዉ ሲቆፍሩ ይዉላሉ ይሄም በመሳሪያና በቴክኒክ ያልታገዘ ሲሆን፡፡ አንድ አካባቢ ላይ የሚቆፍሩት ጉድጓድ ቢይነስ 15 ሺህ ብር ያስወጣቸዋል ይላል፡፡ ነገር ግን ለነዚህ ወጣቶች ብድር እንደማይመቻች፤ሙያዊ ድጋፍ እንደማይደረግላቸዉና እንዲሁም በተለያየ ምክንያት ወጣቶቹ ከስራዉ እንዲወጡ ይደረጋል ይላል፡፡ ስራዉን ለመጀመርም 15 ሺህ ብር ወጣቶቹ ለማግነት የሚቸገሩ ሲሆን፡፡ ስራዉን ጀምረዉ ያገኙትን ኦፓል ደላሎች (የህወሃት ኮንትሮባንዲስት) በግራም 90 ብር ብቻ ይገዟቸዋል ፡፡ ደላሎቹ አዲስ አበባ ላይ በግራም አስከ 5 ሺህ ብር ይሸጡታል ይላል፡፡

ሪፖርቱ ኢትዮጵያ በአለም ሁለተኛ የኦፓል አምራችና ላኪ ሀገር እንደሆነች ያትታል ከአዉስትራሊያ በመቀጠል፡፡ ለምሳሌ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት እንዳመለከተዉ በ 2012 ኢትዮጵያ 14 ሺህ ኪሎ ግራም በ 2011, 13, 839 ኪሎግራም ወደ ዉጪ ልካለች ይላል፡፡ ከአሜሪካን ኤምባሲ በተገኘዉ መረጃ ደግሞ በ 2016 ወደ 18 ሺህ ኪሎ ግራም እንዲሁም በ 2017 ወደ 20 ሺህ ኪሎ ግራም ኦፓል ከኢትዪጵያ ወቷል ብሎ ያምናል፡፡ እንግዲህ የአለም ባንክና የአሜሪካ ጂኦሎጊካል ሰርቨይ የሚያሳየዉ ይሄን ነዉ፡፡

ችግሩ የት ላይ ነዉ ታዲያ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት በማእድን ሚኒስቴር አማክኝነት ያቀረበዉ ሪፖርት እንዲህ ይላል በፈረንጆች 2014-15 ኢትዮጵያ 4545 ኪሎግራም ኦፓል ወደ ዉጪ ልካለች ይላል፡፡ የአለም ባንክ ሪፓርት እንዲህ ሲል ይኮንነዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት 2/3ተኛዉን የኦፓል ምርትን ያላግባብ/illegal በሆነ መንገድ ካገር እንዲወጣ አድርጓል ቁጥጥር አላደረገም ይላል (world Bank report page 3). ይህም ማለት ቢያን ከ 14 ሺህ ኪሎ ግራም ዉስጥ 10 ሺህ የሚሆነዉ በህገወጥ መንገድ በህወሃት ነጋዴዎች ተልኳል ማለት ነዉ፡፡

ከታች የተያያዘዉ ሰንጠረዥ ከአለም ባንክ ሪፓርት የወሰድኩት ሲሆን፡፡ ለምሳሌ polished Opal (ተቆርጦ የተዘጋጀ) 114 ኪሎ ግራም (አንድ ኬሻ ማለት ነዉ) 2.49 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ተሽጧል ይላል፡፡ ይህ ማለት አንድ መቶ ኪሎ ኦፓል 70 ሚሊየን ብር ማለት ነዉ፡፡ ባንኩ እንዳሰፈረዉ 14 ሺህ ኪሎገራም ኦፓል በ2012 ተሽጣል ብሏል፡፡ ስለዚህም ዋጋዉን ማባዛት ነዉ መቶ ኪሎ 70 ሚሊየን ብር ከሆነ 14 ሺህ ኪሎ ግራም 9.8 ቢሊየን ብር ሆነ ማለት ነዉ፡፡ በ 2016 እና በ2017 የተላከዉ እራሱ ብዙ ነዉ፡፡

አሁን ጥያቄዉ ይሄን ያህል ቢሊየን ብር ገቢ እየተገኘበት የወሎ አማራ ተጠቅሟል ወይ፡፡ ህብረተሰቡ አስፓልት መንገድ ተሰርቶለታል ወይ፤ ሆስፒታል ተገንብቶለታል ወይ፤ ትምህርት ቤት፡፡ ይሄ በጭራሽ አልሆነም፡፡ የህወሃት ቱጃሮች ብቻ ህብት እያጋበሱበት ነዉ፡፡ ማድረግ ያለብን ወጣቱ ስለ ምርቱና ገቢያዉ መረጃ የለዉም ለዛም ነዉ ለግራም በ90 ብር የሚሸጠዉ፡፡ አሁን ለአካባቢዉ ወጣት የምናስተምርበትና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ መፈለግ አለብን፡፡ ይሄም በማንቃት ነዉ፡፡ የህወሃት ደላሎችን አስወግዶ የአካባቢዉ አምራች ቀጥታ ከገቢያ ጋር ትስስር የሚፈጥርበትን መንገድ እንዲፈለግ ማድረግ አለብን፡፡ ጎበዝ 9.8 ቢሊየን ብር እጅግ ብዙ ገንዘብ ነዉ፡፡

የአለም ባንክ ሪፖርቱን ሊንክ እዚሁ ላይ አለላችሁ፡፡ ሁሉም በገባዉ መጠን እየጻፈ የአካባቢዉን ወጣት በማንቃት ከነዚህ ሰዉ በላ ቀማኞች በመንጠቅ ህዝባችን ተጠቃሚ እንዲሆን እናድርግ፡፡

http://documents.worldbank.org/curated/en/386891474020338559/pdf/107146-REVISED-PUBLIC-20160921-ELL-FINAL-Ethiopia-report.pdf

በወሎ በወያኔ እና በአጋሮቹ በህገወጥ መንገድ እየተዘረፈ ስላለው የኦፓል ምርት ተጨማሪ ዘገባ

ዐማራን ሃብትህን ጠብቅ በሉልኝ !! (በአማራ ክልል በወሎ ውስጥ የሚመረተው የኦፓል ምርት) ዝርዝሩን ከዚህ ላይ ያንብቡ