የኢህአዴግ ኑዛዜ ወይንስ የለውጥ አቅጣጫ? – አማራጩ ሕዝብን የስልጣኑ ባለቤት ማድረግ ብቻ ነው!

Print Friendly, PDF & Email

አክሎግ ቢራራ (ዶር)

በህወሓት የበላይነት የሚገዛው የኢህአዴግ የስራ አስኪያጅና አስፈጻሚ ኮሚቴ፤ የሕዝብን ባጀት ተጠቅሞ፤ ለሶስት ሳምንታት ያህል የኢትዮጵያን ሕዝብ ችግሮች ካላዘነ በኋላ መግለጫ አውጥቶ ሕዝብን እያነጋገረ ነው። ይህ የምስጢር ጉባኤ የተካሄደው የህወሓት የስራ አስፈጻሚ ቡድን ለሳምንታት በመቀሌ የዝግ ችሎት አድርጎ ራሱን በአዲስ መልክ አወቃቅሬአለሁ ካለ በኋላ ነው። ቡድኑ አጠናክሮ የወጣው አሁንም ራሱን የስልጣን መአከል አድርጎ እንዴት የበላይ ሆኘ እገዛለሁ በሚል የህወሓቶችን ቀጣይነት የሚያሳይ ስልት መሆኑን ማስታወስ አስፈላጊ ነው። የኢህአዴግ አመራር ክብደት የሰጠው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ስልጣን ሳይሆን ለአዲሱ የህወሓት አመራር የበላይነት መሆኑ በግልጽ ይታያል።

ኢህአዴግ፤ ሕዝብን ላስቆጡትና ለአስነሱት፤ ለእልቂቶች፤ ለፖለቲካ እስረኞች፤ ለፍልሰቶች፤ ለስደት፤ ለአገሪቱ በውጭ ኃይሎች መከበብ፤ ለማህበረሰባዊና ለሰብ አዊ መብቶች መታፈን፤ ለኑሮ ውድነት፤ ለፍጽሙ ድህነት፤ ለስራ አጥነት፤ ለሕዝብ የፖለቲካ ስልጣን አለመኖር ወዘተ ምንም አይነት አጥጋቢ መልስ አልተሰጠም። The root causes that prompted popular resistance for the past two years remain intact. ችግሮቹ ካልተፈቱ በስተቀር ሕዝባዊው አመጽ በኃይል ቢታፈንም አያቆምም። ችግሮቹን የፈጠረው የኢህአዴግ አመራር ራሱ ነው። የፈጠረውን ችግር ራሱ ፈትሾና ተችቶ ራሱ ሊፈታቸው አይችልም። የፍላጎት አለመኖር ክፍተት ብቻ ሳይሆን አቅምና ጥበብ ይጎድለዋል።

ብዙ የአገር ውስጥና የውጭ ተመልካቾች ተስፋ አድርገውት የነበረው ሂደት፤ የኢህአዴግ የስራ አስኪያጅና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፤ በመላው ኢትዮጵያ የተከሰተውን ህውከት፤ የእርስ በርስ ግጭት፤ የንጹሃን ዜጎች እልቂት፤ የንብረት መውደም ተመልክቶ የሕዝብን እሮሮ ይሰማል፤ ከሕዝብ ጋር፤ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር፤ ከምሁራንና ከሌሎች ማህበረሰባዊ ክፍሎች ጋር በመከካር፤ የጋራችን የሆነችውን ኢትዮጵያን ከመፈራረስና ሕዝቧን ከእርስ በርስ እልቂት ሊታደግ ይሞክራል የሚል ተስፋና ምኞት ነበር። አስተማማኝ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የፖለቲካ እስረኞችን ይፈታል የሚል ተስፋ ነበር። የጸረ-ሽብርተኛውን አዋጅ ይስበዋል፤ ቢያንስ ያሻሽለዋል የሚል ተስፋም ነበር ወዘተ፤ ወዘተ።

ገዢው ፓርቲ ኢህአዲግ፤ የኢህአዲግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባውን ሲጀምር “ወሳኝ ውሳኔዎች ይተላለፉበታል ብሎ” የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማዘናጋት ሞክሮ ነበር። አንድ ሰዓት የፈጀውን መግለጫ ሳዳምጥ ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን ብሎ ኢህአዴግን ይተቸው ይሆን? ከማለት ውጭ የኢትዮጵያን 105 ሚሊየን ሕዝብ ተስፋ የሚሰጥ፤ የሕዝብን አመኔታ የሚያረጋግጥ፤ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ አቅጣጫ የሚያስኬድ አላየሁም፤ አልሰማሁም። በእኔ እምነት፤ ይህ መግለጫ ያጠናከረው የህወሓትን የበላይነትና ቀጣይነት ነው ለማስባል የሚያስችሉ ሁኔታዎች አሉ። ፋይዳ ቢስ መሆኑ ነው። አሁንም በሕዝብ ስም የሚነግዱት ኃይሎች የበላይነቱን ይዘዋል። …. (Read more, pdf)