“አማራው ያሬድ አይቼህ” ደግሞ ምን ፍጠሩ እያለን ይሆን?

Print Friendly, PDF & Email

በብሥራት ደረሰ

article-amአፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል፡፡ የወደቀም ግንድ ምሣር ይበዛበታል፡፡ ኢትዮጵያም ቀን ጣላትና፣ ቀን ጣላትናም በጠላቶቿ እጅ ወደቀችና፣ በጠላቶቿ እጅ ወድቀችናም የድፍን ስድና መረን ያደገ ዋልጌ ሁለ የስድብና የዘለፋአፋ አፍ ማሟሻ የመሆን ዕጣ ደረሳትና ይሄውላችሁ በየቀኑ ተነግሮ የማንሰማው ተጽፍም የማናነበው ነገር የለለን ሆነን አረፍነው፡፡ የገዛ ልጆቿም እየከዷት አንደ ወግጂልኝ ይላታል:: ሌ ላው ለርሷ ለመሞት ቆርጦ ተሰልፎላታል:: ደርግ ጥሩ አማርኛ ነበረችው፡- #የእናት ጡት ነካሽ› የምትል፡፡ ዛሬ ዛሬማ የእናት ጡት ነካሽ ብቻ ሳይሆን ባት ቆራጭም፣ ማጅራት ገትርም ማለቴ ማጅራት መቺም፤ አነጣጥሮ አናት በርቋሽም ልጅ ሞልቶናሌ – የሌጅ በያይነቱና ማኅበራዊ በብፌ መልክ በሽበሽ ብሎ ፊታችን ላይ ተዘርግቶልናል (የምግብ ስሞች ናቸው)፡፡ የበዓሉ ግርማ የምናብ ፍጡር የሆነው የካድማስ ባሻገሩ አበራ፣ ገነት ሆቴሌ የፋሲካ ዋዛማ የጦፈ ዳንስ ላይ የአምቦዋ ሳዱላ ሉሌት ታደሰ ስሟን እንዴትነግረው ሦስቴ ጨቅጭቆ ላለመንገር ደጅ ስታስጠናው ‹ከነስምሽ ገደል ልትገቢ ትችያለሽ› እንዳላት ዓይነት ጃዋር ሲራጅን ዓይነቱ ወያኔ ሰራሽ ጎረምሳ በ‹ጤፍ ብዴር ሳይቸግር› እንዲያው ከሜዳ ይነሣና ‹ኦሮሞነቴን ካልተቀበላችሁ ከነኢትዮጵያችሁ ገደል ልትገቡ ትችላላችሁ› እያለ ይዝትብናል – ከነገር አባቶቹና አሰለጣኞቹ (አሰይጣኞቹ ብልም ያው ነው) ከነሌንጮ ለታ የቀሰመውን እንጂ እርሱማ በጥቂቶች ጥፋት የተነሣ ያን በክፉነት የሚታማውን ዘመን የት ደርሶበት፡፡ እኛ የኢትዮጵያዊነትን መቁነን የምንሰጥ ወይ የምንነሣ ይመስል በማናውቀው ነገር በትዝታና በታሪክ ዋሻ ውስጥ መሽገውና በአስተሳሰብ ላለማደግ ምለው ትናንትም ዛሬም እዚያው የሚኖሩ በሽተኞች ይነተርኩናል፡፡ ‹ጌታውን ቢፈሩ ገበር ገበሩን› ይባላል፡፡ አሁን ኢትዮጵያን ቀጥቅጦ እየገዛት ያለው አማራ ሳይሆን ወያኔ/ኢሕአዳግ መሆኑ እየታወቀ ‹ሞቶ መቃብር ውስጥ የገባ›ን አማራ መጨቅጨቅ ያስፈለገበት ምክንያት እንኳንስ ለሰው ዘር ለእግዜሩም ዕንቆቅሌሽ ሣይሆንበት የሚቀር አይመስለኝም፤ ‹የሞተን› መውቀስ ደግሞ ከፈሪና ከባለጌ እንጂ ከጤናማ ሰው በጭራሽ አይጠበቅም፡፡ ጉደኛ ዘመን ውስጥ ነው ያለነው፡፡ ይሄ የበታችነትም በሉት የበላይነት የሚባል ምስቅልቅል ስሜት እንዳት ያለ መጥፍ በሽታ መሰላችሁ!…..   (ሙሉን ከዚህ ላይ ያንብቡ)