ይህ አቋም የአዳነች ፍሥሐዬ ብቻ ወይስ የቪኦኤም ነው?

Print Friendly, PDF & Email

(በድንበሩ ደግነቱ)

ኢትዮጵያ ቀውጢ ሠዓት ላይ ነች። በሠላም ተኝተን የምናድርበት ቀን እየቸገረን ነው። በየቀኑ የምንሰማቸው የሞት ቁጥሮች ስታቲስቲክስና ዜና ሳይሆኑ ለኛ ህመማችን፥ ስቃያችን፥ ሥጋታችንና እንደኅብረተሰብ የውርደት ሞታችን ናቸው። በዚህ ወቅት አቅሙ ያለን ኢትዮጵያውያን ሁሉ ኢትዮጵያውያንን ለማትረፍ ግድ የሚል ከሆነ፥ የሙያ ሥነምግባር ጥሰን ቢሆን እንኩዋን መረባረብ የሚጠበቅብን ጊዜ ነው። የልዩነት መንገድ ለዚህ አደረሰን። የዕውነትና የአንድነትን መንገድ መስበክን እንጀምር፤ በተለይ መገናኛ ብዙኃን በእጃችን ያሉ ኢትዮጵውያን።

በ12/23/2017 ቪኦኤ ባቀረበው ቃለ መጥይቅ፥ ቃለመጠይቅ አቅራቢ:- አዳነች ፍሥሐዬ

https://av.voanews.com/clips/VAM/2017/12/23/20171223-180000-VAM068-program_48k.mp3

የቃለ መጠይቁ እንግዶች:-
አቶ ልደቱ አያሌው፥
ዶር መሐሪ ረዳኢ፥
አቶ ሙላቱ ገመቹ

አዳነች በክፍል አንድ ማጠቃለያ ላይ የወረወረችውን ጥያቄ በሚከተለው ዐርፍተ ነገር አጀበችው። “ዋለልኝ የአማራ ብሔረሰብ አባል ነው። ያኔ እንግዲህ የአማራ የገዢ መደብ የነበረበት ጊዜ ነው።……”

  1. አዎ ዋለልኝ የወሎ ክሐገር ተወላጅ ነው። ወሎዬዎች ባብዛኛው አማርኛ ተናጋሪዎች ናቸው። ”አማራ ማለት የኀይማኖት ፍረጃን የሚያሳይ እንጂ ዘርን አይደለም።” ከሚል ክርክር አንስቶ “አማራ የሚባል ብሔር ቢያንስ ህወሀት ሥልጣን ላይ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ አልነበረም” የሚል ክርክር ይነሳል። ዋለልኝ ወሎዬ መሆኑን እርግጠኛ ነን። ኢትዮጵያዊ መሆኑንም እርግጠኛ ነን። ምናልባት ባይሞትና እስካሁን ቢቆይ አማራ ሊሆን ይችል ይሆናል። በዚህ ክርክር ውስጥ ተዘፍቆ የከፋፋዮቹን አቋም መደገፍ ከቪኦኤ ጋዜጠኛ የሚጠበቅ ነው?
  2. ህወሀት ትግራይን እስኪቆጣጠር ድረስ አማራ ለሚለው የፈጠራ ጠላት፥ ጅራትና ቀንድ አበጅቶ የትግራይን ወጣቶች አጭበርብሮና አስታጥቆ ኢትዮጵያን ወጋ። “የአማራ የገዢ መደብ” ወያኔ ትግራይ አልበቃ ብላው ወደ ደቡብ ሲያቀና፥ ጠላት ተብሎ የተሳለው አማራ የተባለው ሕዝብ ጭራም ቀንድም የሌለው ከነሱም የባሰ ጉስቁል ሆኖ ቢያዩት ጊዜ፥ ታጋዮቹ ላነሱት ጥያቄ መልስ ሲያጥረው የፈጠረው ነገር ነው ። የኃይለ ሥላሤም ሆነ የደርግ መንግሥታት በኦፊሺያል ራሣቸውን እንደዚህ ብለው አይጠሩም። ከጠላቶቻቸው በቀር እንደዚህ ብሎ የጠራቸውም የለም። በተለይ በዚህ ጉዳይ ላይ ኢሣት በተደጋጋሚ ሥራዬ ብሎ የመንግሥታቱን አወቃቀር አሳይቶዋል። ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥትን ነጥብ በነጥብ ጉድፉን እየነቀሱ ለአንድ ዘር ያደላ ሥርዓት መመስረቱን በተጨባጭ አሳይተዋል። እውነትን ለማየት ለሚችል ዐይንና ለሚናገር አንደበት ማስረጃዎቹ ግልፅና ከበቂም በላይ ናቸው። ግን አንድም የቪኦኤ ጋዜጠኛ “የትግሬ የገዢ መደብ” ሲል አልተደመጠም። እንደዛ እንዲልም እኔ አልጠብቅም። ታዲያ አዳነች “የአማራ የገዢ መደብ” ብላ እውነትን ለማዛባትና ለመወገን ለምንና እንዴት ተፈቀደላት?