ዶጋሊ ላይ የአሉላን ሃውልት በቦምብ አፍርሶ በጣሊያኖች የመታሰቢያ ሓውልት ላይ የጣሊያኞችን ባንዴራ ያውለበለብ ትግሬው ኢሳያስ አፈውርቂ …

Print Friendly, PDF & Email

ዶጋሊ ላይ የአሉላን ሃውልት በቦምብ አፍርሶ በጣሊያኖች የመታሰቢያ ሓውልት ላይ የጣሊያኞችን ባንዴራ እንድውለበለብ ያደረገ ትግሬው ኢሳያስ አፈውርቂ “ፒያሳ ዴ ቺንኩዌ ቼንቶ” አደባባይ ላይ ጣሊያኞችን ያራወጠ ጀግናው ኤርትራዊው ዘርአይ ደረስ ከመቃብር ተነስቶ ቢያየው ምን ይለው ነበር?

(ጌታቸው ረዳ)


ራስ አሉላ እና ደጃዝማች ዘርአይ ደረስ (የፎቶውን ምንጭ ያገኘሁት ክቡር ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም ስለ ግል ህይወታቸው በጻፉት ማስታወሻ መጽሐፍ ከወዳጅ የተላከልኝ::

ወደ ርዕሱ ከመግባቴ በፊት ለዚህ ትችት መነሻ ሊሆነኝ የቻለ የኔን ጽሁፎች የሚከታተሉ አንባቢዬ ወዳጄ አቶ ዳኜ ታደሰ ከሚኖሩት አገር የሚከለተውን መልእክት በደብዳቤ ስለላኩልኝ መነሻ ሆኖኛል። እንዲህ ሲሉ ባጭሩ ቁጭታቸውን ይገልጻሉ። ሰላም ውድ አርበኛው ጌታቸው ረዳ ሰላምታዬና ምስጋናዬ ይድረስህ። ዛሬ የምልክልህ አንጀቴ ያሳረረኝ እና ሁሌም ዕረፍት የነሳኝ ነገር የኢትዮጵያ ጀግኖች፤ የአፍሪካ ሕዝብ መመኪያ የሆነው የዶጋሊ ጦርነትና ታሪክ በማንኳሰስ ለጣሊያኖች አድሮ የራሱን ማንነት ያራከሰ ወራዳውና ባንዳው ኢሳያስ አፈወርቂ “ዶጋሊ” ላይ ወራሪ ጣሊያኖችን ድል የነሱበትን የራስ አሉላን ሃውልት መታሰቢያ በቦምብ አፍርሶ በምትኩ የጣሊያኖችን መታሰቢያ ሃውልት ላይ የጣሊያን ባንዴራ እንዲውለበለብ ያደረገው ፎቶ ስመለከት መላ ሰውነቴ በንዴት ይቃጠላል፡ ይኸው እስኪ ይህንን ንደቴን አብረህ ተካፈለኝ። ብለው ከላይ የሚታየው የጣሊያኖች ሃውልት በዶጋሊ ልከውልኝ ስመለከት ንደቴ እኔንም ስለቀሰቀሰብኝ አንባቢዎቼም አብራችሁን እንድትመለከቱት እና በጣም አስገራሚ ቅጥረኛነትና ራስን የመክዳት በሽታ ምንነት እያሰቃየው ያለው መነሻው ምክንያቱን ለመፈለግ የአእምሮ ሃኪሞች በኢሳያስ አፈወርቂ ባሕሪና ሕሊና ላይ ጥናት እንዲያካሂዱበት ይህ መልእክት እያስተላለፍኩ፤ እውነት ሃኪሞች የዚህ ሰው በሽታ ቢመራመሩ ትልቅ “ሪሰርች’ ግኝት ይሆናል ብየ እገምታለሁ። አንደኛው ፎቶ “ከረን” ውስጥ የሚገኘው የጣሊያኖች መካነ መቃብር ነው። ኢሳያስ ይህንን መካነ መቃብር አትክልቶችን በመትከል፤ውሃ እያጣጣ ሰራተኞች ተቀጥረውበት በእንክብካቤ እየተጠበቀ ያለው የወራሪዎች መካነ መቃብር ነው። ከላይ አናቱ ላይ ያለው ደግሞ 500 ጣልያኖች አሉላ የፈጁዋቸው የወራሪዎቹ የጣሊያኖች መካነ መቃበር ነው። በስተግራ በኩል የጣሊያን ባንዴራ ሲውለበለብ፤በቀኝ በኩል ደግሞ የሻዕቢያ ባንዴራ አማክለውታል። አካባቢው ዙርያ ሃውልቱ ንጣፍ በኢሳያስ ትእዘዝ የገንዘብ ወጪ ተደርጎ ኤርትራዉያን የህንጻ ሥራ ባለሞያዎች ተመድበው አስፈላጊው እድሳት እና አንክብካቤ ተደርጎለታል። እግዚኦ ተሳሃለነ ክርስቶስ!!!

ፈረንጆች “ባድ ኣፕል” የሚሉት ነገር አላቸው። ወላጆቻችን “የተረገመ ሽንት” እንደሚሉት አባባል። ኢሳያስ ትግሬ ነው። ራስ አሉላም ትግሬ ናቸው። ያውም የኢሳያስ አባት ከሚወለዱበት አውራጃ “ተምቤን”። ሮማ ፒያሳ ዴ ቺንኩዌ ቼንቶ የአምስት መቶዎቹ አደባባይ በተባለው ዶጋሊ ላለቁት የኢጣልያ ወታደሮች መታሰቢያ በተሰየመው አደባባይ ላይ ሦስት የጣሊያን ከፍተኛ ወታደራዊ ባለ ማዕረጎችን አንገት አንገታቸውን ቀልቶ “በዓለም ውስ ፍጹም ያለተደረገ፤ዓለም ያስገረመ ታሪክ” የሰራ በኢትዮጵያዊነቱ እየፎከረ በሕዝቡ ፊት ቆሞ ጎራዴው ሲያወዛውዝ የጣሊያን ሕዝብን ወታደሮች በየቦታው እገሬ አውጭን እያለ ሲሸሽ አንድ ፈሪ ጣሊያን ከሩቅ አነጣጥሮ በጥይት ቶኩሶ እግሩ ያቆሰለውን ሌላው አራተኛውን ጣሊያናዊው ሲጠጋው በጎራዴው ቀልቶ የራስ አሉላን ጅብዱ በጣሊያን 2ኛው ዶጋሊ አደባባይ ላይ የተቀዳጀው የ21 አመቱ ጎልማሳ ወጣት ኤርትራዊው ደጃዝማች “ዘርአይ ደረስ” መካካል ያለውን ልዩነት ላጤነ ተመራማሪ “ኢሳያስ አፈወርቂን” የተረገሙ ሽንቶች” ብለው ወላጆቻችን ከሚጠሩዋቸው ፍጡራን አንዱ እና ግምባር ቀደም ተጠቃሽ ሰው ነው። ይህ ባህሪ እንዴት ሊከሰት ቻለ? የሚለው ለአአምሮ ሓኪሞችና የልቦና ተመራማሪዎች ሊነግሩን የሚገባ ይመስለኛል። በዚህ ሙያ ያሉ ምሁራን ይህ የኔን ርዕስ መነሻ አድርገው እንደያብራሩልን ጥሪ አደርጋለሁ። ….  (Read more, pdf)