የትግሬ ወያኔ ወደ እውነተኛ ቁመናው ሲመለስ! – መቅደላ የ ዐኅ.ኢ.አ.ድ ልሳን

Print Friendly, PDF & Email

የትግሬ ወያኔ ወደ እውነተኛ ቁመናው ሲመለስ!

የግለስብ ሁለንተናዊ ቁመናው የሚገለጥ ከሚመጣበት መህበረሰብ አኳያ ነው። ግለስቦቹ ተቧድነው የሚፈጥሩትም ማህበርና ድርጂትም ላይ የዚያው ማህበረሰብ አሻራ አብሯቸው ይኖራል። ለምሳሌ በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ማህበረሰቦችን በዚህ አኳያ መዳሰስ ይቻላል። ይህን ማህበራዊ እይታ ያፍሪካ ቀንድ ወስጥ የሰፈሩ የተለያዩ ማህበረሰቦች የሚጋሩት ቢሆንም በሱማሌ፣ በኤርትራና በትግሬ ማህበረሰቦች መሀል ባያሌው የሚታየው በቤተሰባዊ (ክላን) አመለካከት ዙሪያ የሚታይ ማህበረሰባዊ መከፋፈል የላቀ ነው።

በዚህ ረገድ ዛሬ ለነጻዪቱ ሱማሌ መበታትን ከፍተኛውን ሚና የተጫወተ የህዝቧ በክላን ዙሪያ ያጠነጠነ አመለካከት በማደግ ላይ የነበረውን ሀገራዊ አመለካከት ስለደፈጠጠው ነው። ዚያድ ባሬ የኦክቶበር አብዮት ብሎ የሰየመውን የ1962ዓም የመፈንቅ ለመንግስት ሲመሰርት ዋና የአገዛዙ መመሪያ አድርጎ ያስቀመጠው የሱማሊያን አምስት የተለያዩ ግዛቶችን በአንድ የተጠቃለለች ታላቅ ሱማሌ ስር የማምጣትን ህልም ነበር። ዚያድ ባሬ ይህንን መመሪያ ዋናው የአገዛዙ ርእዮት ሲያደርግ ኢላማው የማህበረሰቡ ዋና ድክመት የሆነውን የቤተሰባዊ(የክላን) አመለካከትን በአንድ ሱማሊያ ተብላ በምትጠራ አዲስ ሀገር ዙሪያ ለማሰለፍ ነበር። እንዳለውም ፊደል ላልነበረው ቋንቋ የላቲን ፊደልን እንዲይዝ አደረገ። የሀገሪቱን የአስተዳደር አይነት ሶሻሊዝም ነው ብሎ አወጀ። ሀገራዊ ታላቅነቱን እውን የሚያደርግለት ጦሩን ገነባ። …. (Read more pdf)