ተተኪውን ትውልድ ከሞትና ከመርዛሙ የዘር ፖለቲካ እንታደግ! – የኢ.ሕ.አ.ግ. መግለጫ

Print Friendly, PDF & Email

ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የተሰጠ መግለጫ
ቀን ፡ – ታህሳስ 5/2010

ተተኪውን ትውልድ ከሞትና ከመርዛሙ የዘር ፖለቲካ እንታደግ (pdf)

ኢትዮጵያን ስር እየሰደደ ካለው የዘረኝነት ግጭት ለማውጣት የሁሉንም ተሳትፎ ይሻል!

የሃገራችን ወቅታዊ ሁኔታ አሁን ባለበት ሁኔታ ከማንወጣው ወይም ልንመልሰው ከማንችለው የዘር ግጭት እና የእርስ በእርስ ጦርነት እየገባን ነው።

ይህ መቋጫ የሌለው የዘር አጀንዳ ሃገሪቱንና ሕዝቧን ለሞትና ለስደት መዳረጉ ሳያንስ የአንድ ቡድንተኛ ብሄር አምባ ገነንነት ተጨምሮበት ሃይ ባይ በሌለበት በዘር በመከፋፈል ከትውልድ መንደራቸው ርቀው የሄዱ ተማሪዎችን እያሳደዱ መግደል፣ የሃገሪቱ ዕጣ ፈንታ እንደ ሩዋንዳና ካምቦዲያ የዘር ዕልቂት ጎራ እየከተታት ለመሆኑ አይናችን እያየ፣ ጆሯችን እየሰማና በተቀጣጠለው የዘረኝነት እሳት ላይ ቤንዚን እየተረጨ ይገኛል።

ለ26 ዓመታት የአምባ ገነኑ ወያኔ ኢሃዴግ ከፋፍለህ ግዛው የዘር ፖለቲካ አካሄድ ኢትዮጵያን በኢኮኖሚ፣በማህበራዊና በፖለቲካው ረገድ ያደረሰው ውድቀት የበርካቶችን ሕይወት ሲቀጥፍ በሚሊዪን የሚቆጠሩ ዜጎቻንን ለስደት መዳረጉ የአደባባይ ሚስጢር ነው።
በአሁን ሰዓት በርካታ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ብሔራቸው እየተጠራ እየተገደሉና ከትምህርት ገበታቸው እየተባረሩ ይገኛል።

የፊደራል መንግስት ነኝ የሚለው ቡድን በአጋዚ ወታደር በተገደለው ወጣት እናት በልጇ እሪሳ ላይ እንድትቀመጥ የሚያስገድደው ባለሟል በዜጎች ላይ በየክልልሉ የሚፈጸመውን ግድያ ተመልክቶ ወንጀለኞችን ለፍርድ እንደማቅረብ የገዳዮቹ አጋዥ ሆኑ በየተማሪዎች መኝታ ቤት እየገባ መደብደብ ሽሸተው ሲወጡ መግደል ተባብሶና ቂም አዝሎ በሃገሪቱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተዛምቶ ሃገር ተረካቢው ተማሪ የድረሱልኝ ጥሪው እያሰማ ይገኛል።

ወላጅ እናትና አባት እህትና ወንድም እንዲሁም ቤተዘመድ ልጆቼ ይማሩልኛል በማለት ንብረቱን ሸጦ ለትምህርት የላከውን ልጁን እሬሳ ተረክቦ መቅበር የጥቂቶች ዕጣ ፈንታ ሲሆን ለዛም ያልታደሉ ወላጅ እናትና አባት በርካቶች ናቸው።

ውድ የሃገራችን ሕዝቦችና የተቃዋሚ ድርጅቶችበታህሳስ ወር ብቻ በተለያዩ ትላልቅ የትምህርት ተቋማት በርካታ ተማሪዎች በዚሁ የዘር ቁማር የተገደሉና ይኸው ድርጊት በሃገሪቱ ባሉ ተቋሞች እየተሰራጨ ወደ ማይቆመው የእርስ በእርስ ግጭት እየተንደረደርን እንገኛለን ! ይህ እስከ መቼ ይቀጥላል ? እንዴት ሊቆምስ ይችላል ? ማንስ ያቆመዋል? ጎበዝ ይህንን ሽብራዊ ተግባር ከፈጣሪ ቀጥሎ ሊያቆመው የሚችለው የእኛ ህብረት እና የዘረኞችን ገመድ መበጣጠስ ብቻ ነው።

የሃገራችንና የሕዝባችን ጠላት አንድ ነው ! ይህም የዘር ፖለቲካና አምባገነናዊ የአንድ ጎሳ በዘር ተደራጅቶ፣ተቧድኖና አቧድኖ የሚያጫርሰን ወያኔ ኢሃዴግ በቃህ ልንለው ይገባል።

በመሆኑም በመሃላችን ያለውን የጎንዮሽ ትግል አቁመን ወጣት ሽማግሌ ልጅ አዋቂ ሳይለይ እንደ ከዚህ ቀደሙ ስረዓት አስከባሪው ፖሊስ ፣ ወታደሩ ፣ተማሪው ፣ሰራተኛው እና ገበሬው እየተገደለ ያለው ወገንህን ለመታደግ በአራቱም አቅጣጫ በመነሳት አዲስ የለውጥ የትግል አቅጣጫ በመጀመር ሃገርህን ከግድያ፣የእስራት፣የስደትና አፈና መረብ ነጻ ለማውጣት በጋራ ተነስ!!

አንድነት ሃይል ነው
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር