ወያኔ vs ኦህዴድ vs ብአዴን vs ትግራይ ትግርኛ vs የዲያስፖራ የሽግግር ሰነድ vs የአማራ ሕዝብ

Print Friendly, PDF & Email

(ቬሮኒካ መላኩ)

ኦህዴድ

ወያኔ እና ኦህዴድ የጨዋታ ሜዳው ላይ ተፋጠዋል! ብአዴን እና ደህዴን አሁን ባለው ሁኔታ ጆከር ናቸው

ቲም ለማ ወደ ስልጣን የመጣው በቅርቡ በመሆኑ ከወያኔ ጋር የለየለት open conflict ውስጥ መግባት አልፈለገም። የራሱን ኃይል ለማደራጀት የተወሰነ ግዜ እንደፈለገ ግልፅ ነው። ትግሬ ወያኔ ነገሮች በከፍተኛ ፍጥነት ከቁጥትሩዋ ውጪ እየወጣ እራሱዋ ባሳደገቻቸው ልጆች እየተበላች እንደሆነ ገብቱዋታል። ”An entire sea of water can’t sink a ship unless it gets inside the ship.” የለውጡ ማዕበል ራሱዋ ውስጥ ገብቶ ሊያሰጥማት ከጫፍ ድርሱዋል። በ ፖለቲክስ timing የሚባል ነገር አለ። አሁን እርምጃ ካልወሰደች ሙሉ በሙሉ እንደሚያከትምላትም ግብቱዋታል። ችግሩ አሁን እርምጃም ብትወስድ ሊመጣ የሚችለው ነገር unpredictable ስለሆነ መወሰን አቅቱዋታል ። ትግሬ ወያኔዎች ቲም ለማን ወጥመድ ውስጥ ለማስገባት የተለያዩ provocations በጨለንቆ እና አሁን ደግሞ Daro Labu እና Hawi Gudina ላይ እያደረጉ ነው። በዚህ ፍጥጫ who blinks first የሚለው በመጭዎቹ ጥቂት ቀናት ወይም ሳምንታት የሚታይ ይሆናል።

ትግራይ ትግርኛ ?

ትግሬ ወያኔዎች ነገሮች ወደ ፍፃሜ እየተቃረቡ መሆናቸው ገብቱዋቸዋል ። ችግር የሆነባቸው exit strategy ሳያዘጋጁ የለውጡ ማዕበል በከፍተኛ ፍጥነት መምጣቱ ነው።ጭቃ ውስጥ የገባ መኪና ሹፌር ከገባበት ለመውጣት መኪናውን በተጫነው ቁጥር እየሰጠመ ይሄዳል። ወያኔ እየሰጠመ ያለ መርከብ ነው። የጨነቀው እርጉዝ ያገባል ነውና አዲስ አበባ ላይ በፃድቃን ወልድተንሳይ ሰብሳቢነት አዲስ ከ ኤርትራውያን ጋር የህዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለመጀመር ደፋ ቀና እያለ ነው። እዚህ ላይ ፃድቃን ለምን ከ ህውሃት እንደተባረረ ሁሉ የዘነጋው ይመስላል (የአድዋ ትግሬዎች ፃድቃንን እንደ proper tigre አያዩትም )። የ ኤርትራን ብሄረ ትግርኛ ሕዝብ በቅስቀሳ አሳምኖ የ ትግራይ ትግርኛን ለመመስረት ማሰብ fantasy ብቻ ሳይሆን የሌለ ነገር ነው። አሁን ትግርኛ ተናጋሪ የሆኑት ኤርትራውያን ራሳቸውን identify የሚያደርጉት ከፍ ሲል ኤርትራዊ ዝቅ ሲል ሐማሴን አካለ ጉዛይ ሰራዬ እያሉ ነው። ኤርትራዊነት የሚለውን ማንነት በመገንባቱ ሂደት ወሳኝ ሚና ስለተጫወቱ ራሳቸው የገነቡትን ኤርትራዊ ማንነት አፍርሰው አዲስ የ ትግራይ ትግርኛ የሚባል ሀገር ለመመስረት ፍላጎቱም ስሜቱም እንደሌላቸው እሙን ነው። በመሰረቱ አብዛኛዎቹ ትግርኛ የሚናገሩት ኤርትራውያን(ሐማሴን) በ አፄ ሰርፀድንግል ግዜ ኦቶማን ቱርኮችን ለመመከት ከ ጎንደር(ደንቢያ) እና አካባቢው የሄዱ ወታደሮች ናቸው። የተወሰኑት በ ንጉስ ላሊበላ ግዜም ቀድም የሄዱ ነበሩ። ሃማሴኖች ወደ ቀደመ ስረ መሰረታቸው መመለስ ከፈለጉ ጎንደር እና ላሊበላ ነው የሚቀርባቸው። አሁን ባለው ሁኔታ ግን አብዛኛው ሐማሴን፣ አካለ ጉዛይ፣ እና ሰራየዎች የ ኤርትራዊ ማንነት የገነቡ ናቸው። የብሔረ ትግርኛ ማንነታቸውንም ከ ትግሬዎች ጋር የማዛመድ ፍላጎትም ሲያሳዩ አይታዩም። በአንፃሩ ግን ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ትግሬዎች(አድዋዎች) ግን ኤርትራዊ የመሆን ፍላጎት እንዳላቸው ግልፅ ነው። በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ የሆነ የበታችነት እና የተስፋቢስነት ስሜት በአብዛኛዎቹ ትግሬዎች ዘንድ ይንፀባረቃል። insecurity ደግሞ ፍርሃትን ይወልዳል። ከልክ በላይ የሆነ ፍርሃት ምክንያታዊነትን ያሳጣል። በዚህ የተነሳ ትግሬ ወያኔዎች በስልጣን ላይ ለቆየት የማይፈነቅሉት ድንጋይ አይኖረም። የትግራይ ትግርኛው ነገር በድፕሎማችይ የማይሆን ከሆነ በኃይል ሊያስቡ ይችላሉ። ከእንግዲህ ትግሬ ወያኔዎች ኢሳያስ ሳይሞት ኤርትራ ውስጥ መፈንቅል መንግስት ወይም አሉላ እንዳደረገው ወረራ ለመሞከር አሁን ያለው የፖለቲካ ድባብ አይፈቅድላቸውም። አቅምም የላቸውም። ከዚያድባሬ ትምህርት አለመውሰድ ነው። ትግሬ ወያኔዎች የሰሩት ወደፊትም hunt እያደረጋቸው የሚኖር ሁለት ትልቅ ስህተት አለ። አንዱ አማራን በጠላትነት ፈርጀው በ ወልካይት እና በመላው አማራ ላይ ላለፉት 26 አመታት የሰሩት ግፍ ሲሆን ሁለተኛው ትልቁ ስህተታቸው ከ ኤርትራ ጋር ጦርነት ማድረጋቸው ነው። በነዚህ ሁለት fatal mistakes ምክንያት በአፍሪካ ቀንድ ከታሪክ ከባህል፣ ከኢኮኖሚ ከ ፖለቲካ እና ከ ህዝቦች የእርስበርስ ግኑኘት አንፃር ለነሱ ዘላቂ አጋር እና ቅርብ ከነበሩት ሁለት ህዝቦች ጋር ላንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ ተቆራርጠዋል።

ብአዴን እና የ አማራ ሁኔታ 

አሁን ባለው ፍጥጫ ውስጥ የ አማራ ወኪል ነኝ የሚለው ብአዴን (ትግሬዎችንም በአመራርነት ያቀፈ ቡድን ነው) እርስበርሱ መተማመን አቅቶት እና የራሱን አጀንዳ ማውጣት ተስኖት የተወሰነው ቡድን ለኦህዴድ ሌላው ደግሞ ለወያኔ የጆከርነት ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የደቡብ ሕዝብ የሚባል መሬት የሌለ ማንነት ተወካይ ነኝ የሚለው ደህዴንም አሁን ባለው ሁኔታ የወያኔ ታዛዝነቱን እንደቀጠለ ነው። በዚህ ሁኔታ ውስጥ አማራው ምን ማድረግ አለበት? እንደኔ እምነት ብአዴንን እንደ OPDO ማድረግ የሚቻል አይመስለኝም። የአማራውን ትግል መራር የሚያደርገውም ይህ እውነት ነው። በብአዴን ውስጥ አንዳንድ የአማራነት ስሜት ያላቸው ግለሰቦች ቢኖሩም በሌሎች አደርባዮች ተሸማቀው የሚኖሩ ናቸው። የቤት ስራችንን ቢያበዛብንም የ አማራ ህዝብን ከ ትግሬ ወያኔ ቀንበር ለማላቀቅ በየደረጃው ያለውን የብአዴን መዋቅር ማፈራረስ የተሻለ አማራጭ ነው። ብአዴን/ኢህድን ከአመሰራረቱ ጀምሮ እንደምናውቀው የኢሕአፓ፣ የሻቢያ እና የወያኔ ትራፊዎች ስብስብ ነው። ይህ ስብስብ ከ ቲም ለማ Opdo ጋር በምንም አይነት መልኩ ሊነፃፀር የሚችል አይደለም። ይህ የ አማራውን ፈተና ብቸምረውም አማራው ነፍጠኛ ሕዝብ መሆኑ ደግሞ በሚገባ ከተደራጀ ይህንን ፈተና ለመወጣት የሚያስችል ስንልቦና እና አቅም በቀላሉ መገንባት እንደሚችል ነው። በ ጎንደር በ ጎጃም በላኮመልዛ እና በ ሸዋ በቅርቡ የታየው የአማራ ሕዝብ ነፍጠኝነት ያረጋገጠልን ነገር ቢኖር የአማራ ሕዝብ አምርሮ ከተነሳ ምንም አይነት ምድራዊ ኃይል ሊመልሰው እንደማይችል ነው።

የ ኤርትራ ሕዝብ ትግል በጀብሃ ከዛም በ ሻቢያ፣ የትግሬዎች በወያኔ፣ የ ኦሮሞዎች በኦነግ (ባይሳካም) እንደተመራው ሁሉ አማራውን በገጠር በከተማ አደራጅቶ ታግሎ እና አታግሎ ለድል የሚያበቃ አንድ አውራ ድርጅት ያስፈልገዋል። የ ጥቁር አፍሪካውያንን ትግል በደቡብ አፍሪካ የመራው ANC ነበር ፣ ዙምባቤዎችም በ ZANU PF እየተመሩ ነው ነፃ የወጡት፣ እነ ማህተመ ጋንዲ የነበሩበት የህንድ የነፃነት ትግል የተመራው በ Indian National Congress ነው፣ የያሲን አራፍት Fatah/PLO የፍልስጤሞች አውራ ድርጅት ነበር፣ አሁን በቅርቡ እንኩዋን የ ግብፅ ተነስቶ የነበረው አመፅ በ Muslim brotherhood የተመራ ነበር። የአማራ ህዝብን ሕዝቡን አደራጅቶ፣ አስታጥቆ፣ ታግሎ እና አታግሎ ለድል የሚያበቃ አውራ ድርጅት አሁኑኑ ያስፈልጋል።

የዲያስፖራ የሽግግር መንግስት ሰነድ?

ከተማሪዎች እንቅስቃሴ ጀምሮ ብናይ የተወሰኑ እርትራውያን በ ኢትዮጵያ ስም በተመሰረቱ ድርጅቶች ውስጥ ቢንቀሳቀሱም አብዛኛው ኤርትራዊ አስቀድሞ በ ጀብሃ ከዛም በ ሻቢያ ውስጥ ሁኖ ነው የታገለው። የተወሰኑ የትግራይ ተወላጆች በ ኢትዮጵያ ድርጅቶች ውስጥ ቢንቀሳቀሱም አብዛኛው ትግሬ በ ወያኔ ስር ታቅፎ ነው የታገለው። አንዳንድ ኦሮሞዎችም በ ኢትዮጵያ ስም በሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ውስጥ ቢኖሩም አብዛኛው ኦሮሞ በ ኦነግ ውስጥ ሁኖ ነው ይታገል የነበረው። ወደ አማራው ስንመጣ ኢትዮጵያ በተባሉ ድርጅቶች ሁሉ ውስጥ ተበታትኖ ሰብሳቤ እረኛ እንዳጣ መንጋ ተበትኖ ነው የነበረው። በደርግ ውስጥ በአመራር ደረጃ የነበሩት አብዛኛዎቹ ኦሮሞዎች እና ትግሬዎች እንዲሁም ኤርትራውያን ነበሩ። አብዛኛው ተራ ካድሬ እና ወታደር ደግሞ አማራው እና ኦሮሞው ነበር። በኢሕአፓ ውስጥ አብዛኛው አባል አማራ ሲሆን መሪዎቹ ግን ባብዛኛው ትግሬዎች ነበሩ። አማራው ራሱን በዘር መነፅር አይቶ ስለማያውቅ የሌሎች አጀንዳ አስፈፃሚ ሁኖ ቆይቱዋል። አሁንም በውጭ እንቀሳቀሳለን የሚሉ ድርጅቶች አማራውን ለአዝማሪነት እና ለአዳማቂነት ከመፈለግ ውጭ ወሳኝ በሆኑ ቁልፍ ቦታዎች ውስጥ አያስጠጉትም። ታሪክ ለአማራዎች ሁለተኛ ዕድል አይሰጠንም። የ1983ቱ አይነት አሻጥር እንዲደገም መፍቀድ የለብንም። የአንድነት ፖለቲካው አብዛኛው ደጋፊ አማራው ነው። የአንድነት ትግሉንም ይሁን አጀንዳ በፊታውራሪነት መቅረፅ እና መምራት ያለበት አማራው ነው። በነገራችን ላይ አማራውን ለማደንዝዝ በብዛት የሚጠቀሙት tactic የጎንዮሽ እርግጫ አያስፈልግም የሚል ነው። አማራውን እና የአማራውን ዘላቂ ጥቅም በአደባባይ ፊት ለፊት እየረገጡ የጎንዮሽ እርግጫ ይቁም ማለት ጩሀቴን ቀሙኝ ነው ነገሩ። አማራው እንደ አንበሳ አስፈሪ እንደ ተኩላ ብልህ መሆን አለበት። በመፅሐፍ ቅዱስም እንደ እርግብ የዋህ እንደ እባብ ልባም ሁኑ ተብሉዋል።

ቴዎድሮስን እና የበላይ ዘለቀን አይነት ጀግንነት እና አርበኝነት ከ ምኒልክ እና ጣይቱ አርቆ አሳቢነት እና ብልህነት ጋር ማስተባበር ያስፈልጋል። ይህ አሁን በአማራ ላይ የተንሸዋረረ አቁዋም ባላቸው የዲያስፖራ ፖለቲከኞች ስብስብ ለአውሮፓ ፓርላማ (ወሳኝ የሆነ አካል አይደለም ) የቀረበ አማራውን ያገለለ ብቻ ሳይሆን የአማራን ሕዝብ መሰረታዊ ጥያቄ እና ጥቅም የሚጋፋ ሃሳብ ነገ ውሎ አድሮ በሌሎች ወሳኝ አካላት ዘንድ እንደመፍትሄ አማራጭ ሊታይ የሚችል ይሆናል። ነገሩ በቀላሉ የሚታይ መሆን የለበትም። መፍትሄውም በፌስ ቡክ ላይ የድርጅቶቹን ስም እና መሪዎች እየጠሩ መሳደብ ሳይሆን አንድ የ አማራ እና አማራ ወዳድ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን ያካተተ ግብረሃይል ተመስርቶ አማራጭ የሽግግር ሰነድ ማዘጋጀት እና ለሚመለከታቸው አካላት ማሳወቅ ነው። ከዚሁ ጎን ለጎን አንድ ጠንካራ የአማራ ሕዝብ አውራ ድርጅት መኖር ይኖርበታል። ጠንካራ የአማራ ሕዝብ መሪ ድርጅት ከዜሮ ተነስተን መመስረት አይጠበቅብንም ። አሁን ያሉት ትንንሽ የአማራ ድርጅቶች እና ማህበራት ልዩነታቸውን ወደ ጎን ትተው የ አብዛኛውን የአማራ ሕዝብ እና elite ሊማርክ የሚችል mainstream የሆነ የፖለቲካ መስመር የሚከተል አንድ የአማራ ግንባር መፍጠር ይኖርባቸዋል። ታሪክ ለአማራ ሕዝብ ሁለተኛ ዕድል አይሰጠውም!